03/05/2026
ኢትዮጵያዊ ባህላችን "ጉርሻ" ከምግብነትም በላይ የፍቅር፣ የአክብሮት እና የጠለቀ ወንድማማችነት ማህተም ነው! 🇪🇹❤️
የMMA ተጋጣሚዎቹ ንቃተ ህሊና እና ዩሀንስ ከቦንጋ ተነስተው አዲስ አበባ ሲገቡ ያሳዩን ድንቅ ድርጊት የብዙዎችን ልብ እያሞቀ ይገኛል።
በኢትዮጵያዊ ባህላችን "ጉርሻ" ከምግብነትም በላይ የፍቅር፣ የአክብሮት እና የጠለቀ ወንድማማችነት ማህተም ነው። በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት... እነዚህ ጥንካሬያቸውን በኦክታጎን ውስጥ ሊፈትኑ የተዘጋጁ ወጣቶች፣ ማዕድ ላይ ተቀምጠው በፍቅር ሲጎራረሱ ማየት ስፖርታዊ ፉክክር ሰብዓዊነትን እንደማያደበዝዝ በተግባር ያሳየናል።
አዎ! መፎካከር ጠላትነት አይደለም! ይህ አስደናቂ የመተጋገዝ እና የመተሳሰብ መንፈሳቸው ክብር ይገባዋል።
🗣 ከነዚህ ድንቅ ወጣቶች እናንተስ ምን ተማራችሁ❓