FEAR MY BLUE PEN

FEAR MY BLUE PEN FREE TO SPEAK AND WRITE HUMAN BEING IS FREE NATURALLY

13/03/2024
23/12/2021

Like and share it.

18/08/2021

Clear writing is clear thinking!!

24/07/2021

God is good!

የአሜሪካ ኮንግረስ የትራንስፖርት ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ የአሜሪካ መንግስት ተቆጣጣሪ አካል ግድፈት፣ የአውሮፕላን ዲዛይን ች...
16/09/2020

የአሜሪካ ኮንግረስ የትራንስፖርት ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ለደረሰው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ የአሜሪካ መንግስት ተቆጣጣሪ አካል ግድፈት፣ የአውሮፕላን ዲዛይን ችግር እንዲሁም የቦይንግ ኩባንያ አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት እያወቀ እርምጃ አለመውሰዱ ያስከተለው መሆኑን ዛሬ አስታውቀዋል።
የኮሚቴው አጥኚ ቡድን ቦይንግ MCAS ስለተባለው ሶፍትዌር በተደጋጋሚ መረጃዎችን ከአሜሪካው የበረራ መቆጣጠርያ መምሪያ እና ከአየር መንገዶች እንደደበቀ ይፋ አርጓል።
የ246 ገፅ ሪፖርቱ ከዚህ በፊት በተለያዩ ሚድያዎች ሲፃፍ የነበረውን የፓይለቶች ግድፈት ለአደጋው መንስኤ ሊሆን ይችላል የሚለውን ግምት እንደ ምክንያት አላቀረበም።

A House committee issued a scathing report Wednesday questioning whether Boeing and government regulators have recognized the problems that caused two deadly 737 Max jet crashes and whether either...

የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ከ10 ቀናት በኋላ ይጀመራል-የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን*****************በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር ወጪ ህዳር 2008 ዓ.ም የተጀመረው ...
12/11/2019

የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ከ10 ቀናት በኋላ ይጀመራል-የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን
*****************
በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር ወጪ ህዳር 2008 ዓ.ም የተጀመረው የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ከአስር ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከ62 ሺህ በላይ ተመልካቾች የሚይዘው ይህ ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 99 በመቶ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ስታዲየሙ ግንባታ ሲጀመር ከተያዘው ጊዜ ውጭ ተጨማሪ ስድስት ወራት ወስዶ አሁን 99 በመቶ ደርሷል ሲሉ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካኝነት እየተገነባ ያለው ፕሮጀክቱ 2 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለመጀመሪያው ምእራፍ ግንባታ መፈጸሙን ኃላፊው ተናግረዋል።

እንደ አቶ ናስር ገለፃ፣ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች መዘግየት፣ የብረት ዋጋ መናር ፣የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ ተጨማሪ ስድስት ወር አስፈልጎታል።

የአደይ አበባ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ የጨረታ ሂደት 11 ወራትን ፈጅቷል ያሉት አቶ ናስር ጨረታው ሶስት ጊዜ ወጥቶ በመጨረሻ አሁን ላይ ስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

በመጪዎቹ 10 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡

የስታዲየሙ ምእራፍ 2 ግንባታ የጣራ ስራ፣ የወንበር ገጠማ፣ የፊኒሺንግ፣ የሴኩሪቲ፣ የተለያዩ መሰረተ ልማት የማሟላት ስራዎች እንዲሁም ፓርኪንግ፣ የዋና ገንዳ እና ጂምናዚየም ስራዎች ተካተውበታል።

ስታዲየሙ ለተለያዩ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን እንዲያስተናግድ 60,000 መቀመጫዎች እንዲኖረው ተደርጐ እየተገነባ ሲሆን ለከፍተኛ አመራሮች ፣ ለሚዲያ፣ ለስፖርተኞች፣ ለዳኞች እና ለክብር እንግዶች 2,000 ተጨማሪ መቀመጫዎች ስለሚሰሩ ብሔራዊ ስታዲየም 62,000 ተመልካቾች በድምሩ ማስተናገድ ይችላል ተብሏል።

ከስታዲየሙ ውጭ 3,231 ተመልካች ማስተናገድ የሚችሉ ትናንሽ የእግር ኳስ ሜዳዎች እና የመሮጫ መም የሚኖረው ሲሆን 3,500 መኪናችን የማስተናገድ አቅም አለው።

የሂሊኮፕተር ማረፊያ፣ የቮሊቮል፣ የቅርጫት ኳስ፣ የባድሜንተን፣ የሜዳ ቴኒስ፣ አምፊቲያትር አዳራሾች፣ ሰው ሰራሽ ሀይቆች እና ፖርኮች እንዲሁም የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች የስታዲየሙ ውጫዊ ገፀ በረከቶች ናቸው ተብሏል።

ብሔራዊ ስታዲየሙ የአለም ዋንጫን እና የኦሎምፒክን መስፈርት ያሟላ ሲሆን ስታዲየሙ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ኢትዮጵያ አህጉር አቀፍ እና አለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላት ይጠበቃል።

12/01/2019

Journalism is also an investigation and reporting events, issues and trends to a large audience. Though there are many variations of journalism, the ideal is to inform the intended audience about topics ranging from government and business organizations to cultural aspects of society such as arts and entertainment. The field of journalism include; editing, photojournalism and documentary.

11/12/2018

?
~~~~~~~~
?
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሠሞኑን ኢትዮ FM አንድ ዜና አይሉት አሉባልታ አሰምቶናል። አሉባልታው በብሔራችን ምክንያት ከከንቲባ ፅ/ቤት ተቀንሰናል የሚሉ የቀድሞ ሠራተኞች ቅሬታ ያሠማሉ የሚል ነው።
ራዲዮ ጣቢያው ይህን አሉባልታ የሠራበት ሰዓትና ተቀነሥን ያሉትን ሰዎች ያቀረበበት ሁኔታ እንዲሁም የመረጃውን እውነትነት ለማጣራት ያደረገው ጥረት አለመኖሩን ስናይ #ከኢትዮ FM ጀርባ አንዳች እረጅም እና ፈርጣማ እጅ እንመለከታለን ...... #ሚድሮክ......
የFM ጣቢያው ባለ አክሲዯኖች ሰራዊት ፍቅሬ ሰይፉ ፋንታሁን እንዲሁም ማህደር አሠፋ (መዲ) እና ሌሎችም እንደሆኑ ይታወቃል።

=>> #የሰይፉን ሰርግ በሸራተን ስፖንሰር ያደረገው ሚድሮክ ነው።

=>> ማህደርን በቅምጥነት ከማስቀመጥ አልፎ መኖርያ ቤት የገዛላት እንዲሁም የራዲዮ ጣቢያው ከፍተኛ ባለ አክሲዮን ያደረገጋትም ሚድሮክ ነው።

=>> የሠራዊት ፍቅሬ የጡት አባት የሆነው ሚድሮክ ሠራዊት ፍቅሬ ገናና ከነበረበት ግዜ አንስቶ አሁን ተቀባይነቱ ወድቆ እንኳ ታማኝ አገልጋዩ ነው። አሁን ላይ ሠራዊትን ማስታወቂያ የሚያሠራው ብቸኛው ተቋም የሚድሮኩ "ኩል ውሃ" ነወ።

ይህን ስታውቅና ኡማ በህገወጥ መንገድ ታጥረው ለዘመናት የቆዩ ቦታዎችን ሲያሥመልሱ ከሚድሮክ ብቻ ፒያሣ ያለውን ጨምሮ 11ቦታዎችን መቀማታቸውነን እና ለህዝብ ጥቅምም ለማዋል መዘጋጀታቸውን ስትደምርበት ሚድሮክ ረጅም እጁን ከመጠቀም ይቆጠባል ብለህ ካሰብክ ተሳስተሃል።

ከተማዋ ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ያላዩትና ያልሰሙት ነገር ግን የተከሰተ ነገር በምን ሁኔታ ኢትዮ FM ጋር ብቻ ሊደደርስ ቻለ? ብለህ ስትጠይቅ የእነ ገንዘብና ፍንትው ይልልሃል።

ገንዘብ የመሪን እጅ የሚጠመዝዝበት ግዜ አክትሟል።

ጥሩው ነገር ከንቲባው ላያቋርጡ የጀመሩትን ህግን የማሥከበር ስራቸውን የሚገፉበት መሆኑና በገንዘብ ከፈረጠመው የሚድሮክ ክንድና ከኢትዮ FM ተላላኪነትም በላይ በቁርጠኝነት እየሠሩ መሆናቸው ነው።

12/02/2018

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት በተከታታይ በሁከትና ብጥብጥ፣ በሽብር እንዲሁም በሀይማኖት አክራሪነት ክስ የተመሰረተባቸው እና ቅጣት የተወሰነባቸው ግለሰቦች ላይ ክስ የማቋረጥ እና ይቅርታ የማድረግ ተግባር ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ይህንን ተከታታይነት በመቀጠል በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መንግስት ወስኗል።

በዚህም መሰረት አቶ በቀለ ገርባ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል።

ነገር ግን ተጠርጣሪዎቹ ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸውን በሚከታተሉበት ጊዜ ባሳይዋቸው ችሎት የመድፈር እና ህግ የመጣስ ተግባራት ምክንያት ጉዳዩን የሚመለከተው ፍርድ ቤት በእያንዳንዳቸው የአንድ ዓመት እና የስድስት ወር ቅጣት መበየኑ ይታወቃል።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዚህ ምክንያት ጉዳያቸው በፌደራል የይቅርታ ቦርድ እንዲታይ የተወሰነ መሆኑን እና ጉዳዩም ለሀገሪቱ ርእሰ ብሄር ቀርቦ ሲፀድቅ ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉ ነው ያስታወቀው።

30/01/2018

ውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ ጀምሮ እንዲነሳ በመንግስት ተወሰነ።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ትናንት ለሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እግዳው መነሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል።

የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ታግዶ የነበረው ዲፕሎማሲያዊ እና የሰራተኛ ልውውጥን የተመለከቱ ስምምነቶች እስኪዘጋጁ ድረስ እንደነበር ይታወሳል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያው አቶ ባሳዝን በርሄ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ እገዳው ከዛሬ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል።

ሚኒስቴሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤትም የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እገዳ እንዲነሳ መወሰኑን የሚያመላክት ደብዳቤ እንደደረሰው አቶ ባሳዝን አረጋግጠዋል።

በአጠቃላይ የእገዳውን መነሳት አስመልክቶ ከነገ በስቲያ ሀሙስ መግለጫ ይሰጣል ነው ያሉት ባለሙያው።

ዜጎች በህጋዊ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት ለስራ የሚጓዙበት ሁኔታ ሳይመቻች የውጭ ሀገራት ስምሪቱ መታገዱ አግባብ አለመሆኑን የሚያነሱ አሉ።

በውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ህገወጥ ጉዞን ከመቀነስ ይልቅ ማበረታቱም ይነገራል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ግን እገዳውን ለማንሳት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ነው የገለፀው።

በ2008 ዓመተ ምህረት የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አዋጅ እንዲፀድቅ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ አዋጁን ለማስፈፀም የሚረዱ ደንብ እና መመሪያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ።

አዋጁ በዋናነት ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የስራ ስምሪት ስምምነት ወዳልተፈራረመችባቸው ሀገራት ለስራ መጓዝን የሚከለክል ነው።

ስለሆነም ከተቀባይ ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የሀገራቱን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ አዋጁን ተፈፃሚ ለማድረግ ረጅም ጊዜ ወስዷል።

አቶ ባሳዝን በርሄ፥ በውጭ ሀገራት ለስራ የሚሰማሩ ዜጎች ምን ምን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለባቸው የሚለው በሚወጡ መመሪያዎች መካተት የነበረበት መሆኑም ሌላኛው የአዋጁን ተፈፃሚነት ያጓተተ ጉዳይ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን ከዮርዳኖስ እና ኩዌት ጋር የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን፥ ከሊባኖስ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችና ከባህሬን ጋርም የሁለትዮሽ የስራ ስምምነት ለመፈረም እየተዘጋጀች ነው።

በተለይም ከሊባኖስ ጋር በስራ ስምሪት ሰነዱ ላይ ስምምነት ተደርሶ ለመፈረም ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የተደረሰው ስምምነትም በመንግስት እንዲፀድቅ ከነማብራሪያው ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተገልጿል።

17/01/2018

ሰበር ዜና- እውቁ ፓለቲከኛ ዶር መረራ ጉዲና ዛሬ ተፈቱ DR Merara Gudina Freed

03/01/2018

በአቃቤ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ እና የተፈረደባቸው የተለያዩ ፖለቲከኞች እና ሌሎች ግለሰቦችም የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአራቱ የኢህአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች ሊቀመንበሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው ላይ የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ “የህዝባችንና የወዳጆቻችንን ስጋት እየቀረፍን የጠላቶቻችን ከንቱ ምኞት፣ ድባቅ እየመታን ለዚሁ በቅተናል። ለውድቀት የታጨን አይደለንምና ለጊዜው ባጋጠመን ተግዳሮች ውስጥ እንኳ ብናልፍ በአሸናፊነት እንወጣለን።” ብለዋል።
"በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ በአቃቤ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦችም የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስነኗል::" ነው ያሉት።
በደርግ ዘመን በምርመራ ስም ልዩ የጭካኔ ተግባር ሲፈጸምበት የነበረውና በተለምዶ ማዕከላዊ በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማእከል እንዲዘጋ ተደርጎ ሙዝየም እንዲሆን እንደተወሰነ አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።
በምትኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር መሰረት አዲስ የምርመራ ተቋም ተቋቁሞ በሌላ ህንፃ ስራ መጀመሩም በመግለጫው ላይ አስታውቀዋል።
መግለጫውን የኢህአዴግ እና ደኢህዴን ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ እና የህወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ናቸው በጋራ የሰጡት።

Address

Addis Ababa
6839

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FEAR MY BLUE PEN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to FEAR MY BLUE PEN:

Share