Degsew

Degsew ቅጥልጥል ሀሳቦች፣የተዘበራረቀ እይታ፣ጉራማይሌ ግጥሞች https://www.facebook.com/Adespromotion/?ref=pages_you_manage

01/09/2025
“ጉማ ላይ ማሸነፌ በሕይወቴ የማልዘነጋው ትልቅ ነገር ነው”ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተወልዳ ያደገችው በባሕር ዳር ከተማ  ነው:: በባህርዳር ከተማ የካቲት 23 የአንደኛ ደረጃ፣ የመለስተኛ...
02/07/2023

“ጉማ ላይ ማሸነፌ በሕይወቴ የማልዘነጋው ትልቅ ነገር ነው”
ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ተወልዳ ያደገችው በባሕር ዳር ከተማ ነው:: በባህርዳር ከተማ የካቲት 23 የአንደኛ ደረጃ፣ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በፋሲሎ ተከታትላለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በጣና ሐይቅ መሰናዶ ትምህርት ቤት አጠናቃለች::
የዚህ እትም እንግዳችን ከልጅነቷ ጀምሮ ነበር የኪነ ጥበብ ፍቅር ያደረባት። ተዋናይነት ደግሞ የጥበብ ጥሪዋ መዳረሻ ሆነ። የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በክረምት የቲያትር ፣ የሙዚቃ እና የድርሰት ሥልጠናዎችን ሲሰጥ ከተሳታፊዎች ውስጥ አንዷ ነበረች::

የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ለክረምት ሰልጣኞቹ የሰጣቸውን የክረምት ስልጠና በተግባር ልምምድ ሲያሳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሙዚቃዊ ቲያትር ላይ የተሳተፈችው እንግዳችን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት /ያሁኑ አሚኮ/ ያስተላልፋቸው በነበሩት አጫጭር የቴሊቪዥን ጭውውቶች ላይ በተዋናይነት በመሥራት የምኞቷን ምዕራፍ ‘ሀ’ ብላ ጀምራለች::

በአማራ ቴሌቪዥን የአየር ሰዓት ገዝተው ይሠሩ ከነበሩት ከነ ጥላሁን ዘውገ፣ አለልኝ መኳንንት እና በምናቡ ከበደ ጋር አጫጭር ጭውውቶችን በመሥራት የጥበቡን ዓለም ተቀላቀለች። በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ማኅደረ ጣና በሚለው ፕሮግራም የሬዲዮ ድራማዎች ላይ በመተወንም ከሙያው ጋር ይበልጥ ትውውቅ አድርጋለች::

ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል በተዋናይነት ተቀጥራ እስካሁንም ድረስ እያገለገለች ነው። እንግዳችን ገዳይ ሲያረፋፍድ፡ አዲናስ፣ ላምብ፣ ሁለት ዓለም እና የማር ውኃ ፊልሞች ላይ ተውናለች:: ሰው ለሰው፣ ፍለጋ እና ፍትህ አዳኝ በሚሉ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይም ተውናለች::

የሙሉዓለም ባህል ማዕከል በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ቲያትሮች ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው እንግዳችን በ2015 በተካሄደው የጉማ ሽልማት ላይም በማር ውኃ ፊልም ምርጥ ረዳት የሴት ተዋናይ ተብላ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላታል::

አሁን ላይ በሙሉዓለም የባህል ማዕከል በተዋናይነት ሙያ ላይ የምትገኘው እንግዳችን ባለተስፋዋ ተዋናይ መስከረም ነጋ ናት:: ከመስከረም ጋር የጥበብ ጉዞዋን እና የክልሉን ባህል ከጥበብ ጋር ለማስተሳሰር የተሠሩ ሥራዎችን እያነሳን ቆይታ አድርገናል::
መልካም ንባብ!

ወደ ጥበቡ ዓለም እንዴት ገባሽ?
ልጅ እያለሁ ጀምሮ ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር ነበረኝ:: በውስጤ ያለውን መከፋት፣ መደሰት እና ሌላም ስሜት የምገልፀው ሙዚቃን በመጫወት ወይም በማዳመጥ ነበር:: የ10ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ደግሞ በክልሉ ባህል፣ ቱሪዝም እና ማስታወቂያ ቢሮ የቲያትር ስልጠና ሲሰጥ በቀጥታ ሙዚቀኛ ባልሆንም ሙዚቃዊ ቲያትር ላይ በመሳተፌ ወደ ጥበብ ዓለም የገባሁበት የመጀመሪያው ሥራ እሱ ይመስለኛል::

ምንም እንኳን ከልጅነቴ ጀምሮ ለሙዚቃ ሥራ ልዩ ፍቅር ቢኖረኝም በመሀል ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ያደላሁበት ወቅት ስለነበረ ሙዚቃን እና መንፈሳዊ ሕይወትን በአንድ ላይ ማስኬድ ተቸግሬ ነበር:: የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝም እና ማስታወቂያ ቢሮ /ባቱማ/ ያንን የቲያትር ስልጠና ከሰጠኝ ጊዜ አንስቶ ደግሞ በተዋናይነት ሙያ ላይም ጥሩ ፍላጐት አድሮብኛል::

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሥር በነበረው የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ፣ በአማራ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ላይ በድምጽ እና በአካል በመተወን የጀመረው የጥበብ ሕይወቴ በ2002 ዓ.ም በሙሉዓለም የባህል ማዕከል ተዋናይ ሆኜ በመቀጠር አሁንም ድረስ በዚሁ ሙያ ውስጥ ሆኜ እንድቀጥል አስችሎኛል::

ቤተሰቦችሽ ለኪነ ጥበቡ ያላቸው ምልከታ ምን ይመስላል?
አባቴ በሕይወት ቢቆይልኝ ኖሮ በኪነ ጥበቡ ዘርፍ የምፈልገው ቦታ እና ደረጃ ላይ ለመድረስ እንደማልቸገር እርግጠኛ ነበርኩ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን አባቴ በፈጣሪ ፈጥኖ በመጠራቱ ያሳደገችኝ እናቴ ብቻዋን ነው:: እናቴ ደግሞ እኔ በኪነ ጥበቡ ውስጥ እንድቀጥል ፈጽሞ ፍላጐት አልነበራትም:: የእናቴ ምክንያት በቲያትር ሥልጠና ሰበብ ልጇ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳልሄድባት ነው:: የብዙ ጐረቤቶቻችን አመለካከትም ከእናቴ ጋር ተመሳሳይ ነው::

አሁን ላይ በጥበብ ሥራዬ ለደረስኩበት አነስተኛ ስኬት ቆመው ያጨበጨቡልኝ እና አኮራሽን ያሉኝ ጐረቤቶቻችን ያኔ እኔ ወደቲያትር ሥልጠና ስሄድ ወዳልተፈለገ ቦታ እንደምሄድ እና የምሄድበትን መንገድ ልጆቻቸው እንዳይከተሉት እናቴን በማስፈራራት እና በመውቀስ ላይ የተሠማሩ ነበሩ::
የኪነ ጥበብ ሙያ ብዙ በማንበብ በብዙ የሚያሳውቅ እንጂ ሴት ልጅ ወዳልተፈለገ አቅጠጫ ያምትጓዝበት እንዳልሆነ አሁንም ድረስ ከተሳሳተው እሳቤ ላልወጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና ወላጆች ምክሬን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ:: በአጭሩ እኔ ወደ ኪነ ጥበቡ ዓለም ስቀላቀል የቤተሰብም ሆነ የማኅበረሰብ ድጋፍ አልነበረኝም:: አባቴን በማጣቴ ምክንያት ዝምተኝነት የባህሪዬ መገለጫ ሆኖም ስለነበረ የጥበብ ሰው መሆን እንደማልችል በብዙ ጓደኞቼ ጭምር እየተነገረኝ አድጌ ነው የጥበብ ሰው መሆን የቻልኩት::

የአማራ ከልል ቱባ እሴቶቹን በጥበብ ለማስተዋወቅ ምን ያህል ሠርቷል?
እንደ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል በርካታ ነገሮች እንደተሠሩ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ:: ለአብነት ያህልም ጉማ የሚባለው የራያዎችን ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት የሚያሳየው ትውፊታዊ ቲያትራችን፣ አራት ዐይና የሚለው በአለቃ ገብረሃና እውቀቶች ላይ የሚያጠነጥነው ትውፊታዊ ቲያትራችን በክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በጀት የለኝም የሚል ምክንያት ከሙሉዓለም የባህል ማዕከል መድረክ ውጪ የትም ያልታዩ ቲያትሮቻችን ናቸው::

እነዚህ ለአብነት ያነሳኋቸው ሁለት ትውፊታዊ ቲያትሮች በኛ በሙያተኞቹ ብዙ ተለፍቶባቸው ለመድረክ ከበቁ በኋላ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች አየተንቀሳቅስን የክልሉን መልካም እሴቶች ማስተዋወቅ ነበር። በጀት የለንም በሚል ሰበብ ቲያትሮቹ እንዳይታዩ መደረጋቸው ለክልሉ ባህል እና እሴት በሚመለከተው አካል የተሰጠውን አነስተኛ ግምት ለማወቅ አንቸገርም::

እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ትውፊታዊ ቲያትሮች በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች መታየት የነበረባቸው ምርጥ የጥበብ ሥራዎች ነበሩ:: የአማራ ክልልን ባህል እና እሴቶች በተገቢው መልኩ ማስተዋወቅ ሲቻል ኢትዮጵያ በውስጧ ምን ያህል ጥሩ እሴቶች እንዳሏት ማሳያም ጭምር በሆነ ነበር:: ብዙ ባለሀብቶችም የተለያዩ ነገሮችን በገንዘባቸው ሲደግፉ የጥበብ ሥራዎችን ግን ሲደግፉ አይታዩም:: በዚህ ረገድ ያለው ያልተስተካከለ አረዳድ እንዲሻሻል ዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት ጥረት ማድረግ አለባቸው የሚል እምነትም አለኝ::

ጉማ የሚባለው የራያዎች ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ሀገራችን አሁን ላለችበት የእርስ በርስ ብጥብጥ መድኅኒት መሆን ስለመቻሉ የሞከረው አካል የለም:: የአንዱ አካባቢ መልካም እሴት ለሌሎች አካባቢዎች የሚያስተምረውን ነገር በኪነ ጥበብ አዋዝተን ካላቀረብነው በቀር በፖለቲከኞች ትዕዛዝ ወይም በምሁራን ጥናት ብቻ ለውጤት የምናበቃውም አይደለም::

በቅርቡም የሙሉዓለም የባህል ማዕከል እንዛታ የተሰኘ በአዝማሪዎች ሕይወት ላይ የሚያጠነጥን ትውፊታዊ ቲያትር አየሠራ ነው:: እነዚህ ሁሉ የክልሉን መልካም እሴቶች የሚያንፀባርቁ የጥበብ ሥራዎች በክልሉ መንግሥት በኩል በቂ ትኩረት እና ድጋፍ ካልተሰጣቸው ግን ክልሉ የጥበብን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አልተረዳውም ከማለት ውጪ ምንም ማለት አልችልም::

ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ሁሌ በየሳምንቱ እሁድ በዘጠኝ ሰዓት የእግዜር ጣት የሚለውን የጌትነት እንየውን ድርሰት በቲያትር እያሳየ ነው:: ስለዚህ ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ከክልሉ ቱባ እሴቶች ውስጥ እየቆነጠረ በማሳየት ላይ ቢገኝም በበጀት እና በተመልካች እጦት ግን የባህል ማዕከሉ በታሰበው ልክ እየተንቀሳቀሰ አይደለም::

የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ትኩረት ለክልሉ መንግሥት ወይስ ለክልሉ ባህል?
የሙሉዓለም ባህል ማዕከል በክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ስር የሚተዳደር የመንግሥት ተቋም ነው:: የማዕከሉን ራዕይ እና እሴቶች ስናይ የክልሉን ባህል ማስተዋወቅ እና ማሳደግ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው:: ያም ቢሆን ግን ሙሉዓለም የባህል ማዕከል የክልሉ መንግሥት ለደራሽ እና ወቅታዊ ሥራዎች ሲፈልገው አልመጣም የማለት ሥልጣን የለውም:: ስለዚህ በእኔ አረዳድ ባህል ማዕከሉ ሕዝብንም መንግሥትንም የማገልገል ተልዕኮ የተሰጠው ነው ብዬ አስባለሁ::

ብዙ ፊልሞች እና ቲያትሮች ወደሚበዙባት አዲስ አበባ ያለመሄድሽ ምክንያቱ ምን ይሆን?
ጥበብን ከልጅነቴ ጀምሮ እንደምወዳት ለመግለጽ ሞክሬያለሁ:: ለጥበብ ስል ወዴትም የመሄድ ፍላጐት ግን የለኝም:: ባሕርዳርም ሆነች ሁሉም የአማራ ክልል የጥበብ ሰዎችን በማፍራት የሚታሙ አይደሉም:: ስለዚህ ብዙ ፊልሞች እና ቲያትሮች ላይ ለመሥራት በሚል ሰበብ ከትውልድ ሀገሬ ከባሕር ዳር የመሄድ ፍላጐት የለኝም:: እኔ ጥበብን የማከብራት እና የምወዳትን ያህል ጥበብም በኔ መገለጽ ከፈለገች አሁን እየሆነ እንዳለው ሥራዎች ወደኔ ይመጣሉ የሚል ተስፋው አለኝ::

አዲናስ የተባለው ፊልም መቼቱ በአዊ ብሔረሰብ ቢሆንም ፊ

 #ዓድዋ ቅኔ ነው፡ዓድዋ ቅኔ ነው!ሰንደቅ ባሰረው ቃልበአረንጓዴ ቢጫ በቀይ ብዕር ተፅፎ፣ባንድነት ሕብረ-ቃል ከመሐል እስከ ጥግ በዘራፍ ተዘርፎ፡፡ዘመንን ተሻግሮበኛው በራስ ቋንቋ ዛሬን ምንቀ...
28/02/2023

#ዓድዋ ቅኔ ነው

ዓድዋ ቅኔ ነው!
ሰንደቅ ባሰረው ቃል
በአረንጓዴ ቢጫ በቀይ ብዕር ተፅፎ፣
ባንድነት ሕብረ-ቃል ከመሐል እስከ ጥግ በዘራፍ ተዘርፎ፡፡
ዘመንን ተሻግሮ
በኛው በራስ ቋንቋ ዛሬን ምንቀኘው፣
ሺዎች.. ለሚሊዮን፣ በከፈሉት ዋጋ… ነፃነት ወርሰን ነው፡፡
ነ ፃ ነ ት

ዓድዋ ፈውስ ነው!
ያዋቂ እጅ ስራ፣ ድንቅ ረቂቅ ጥበብ ነጭን ያስደመመ፣
ሸውራራ ዕይታን፣ ጥመትን የገራ… ብሌንን ያከመ፡፡

ዓድዋ ብርታት ነው!
አድማስ ያልከለለው
ድንበር ያለልገደበው ለጥቁር ሕዝብ ሁሉ ብርታትን ያደለ፣
ካገር የገዘፈ
ከሐይቅ የጠለቀ፣ ኢትዮጵያዊ ዓርማ፣ አፍሪቃን ያከለ፡፡
ማሸነፍን ማልዶ
ጎሳስሞ ነጋሪት ነፃ እኔነት ነፃነት ያወጀ፣
እንደጥላ ሁሉም አትከተል ቢሉት ከቶ ማይለው በጀ፡፡
ሐበሻም ደረጀ….

ዓድዋ ፋኖስ ነው!
እንዳልተፈጠረ በአምሳሉ በገፁ ቀለም ጥቁረት
ፈጣሪውን ላኮረፈ፣
ሽንፈት የተቃኘን የእሳቤን ፅልመት ለእልፎች፣ የአዕላፍ የገፈፈ፡፡

ዓድዋ ደወል ነው!
ነ ፃ ነ ት ስትማቅቅ ጭንቅ ጥብብ ሲላት
በገዡ እጅ ወድቃ፣
ባልችልም ውስጥ ቅዠት በቀን የተኙትን
ለቁም የተኙትን እልፎችን ያነቃ፡፡

ዓድዋ ፀሐይ ነው!
ከሐበሻ ምድር ማልዶ የደመቀ
ወኔን ከጀግንነት ባጭር ያስታጠቀ፣
በነጭ ሸማ ደምቆ #ከዓድዋ ተራራ በጠዋት የፈለቀ፡፡
ማልዶ የደመቀ…

ዓድዋ ዕሴት ነው!
የረቀቀ ዜማ የሕብረት ዝማሬ ውበት ነው መድመቂያ፣
የአገር ልብስ ሸማ ካባና ጃኖ ነው ክብር ነው መታያ፡፡
አንድ የመሆን ምስጢር መተባበር ዓርማ፣
ኢትዮጵያዊ ኩራት
#ኢትዮጵያዊ ግርማ፡፡


ዋ!!

(ልክ እንደ ዓድዋ ለቦረና…)
Degsew Zegedam

 #ውግዘትን ከባድ የሚያደርገው ተወጋዡን ከሚገባው በላይ ማንቀዥቀዡ ነው።
18/02/2023

#ውግዘትን ከባድ የሚያደርገው
ተወጋዡን ከሚገባው በላይ
ማንቀዥቀዡ ነው።

 #ለሕጋዊ የሚድያ ተቋማት በሙሉ፤የካቲት ፱ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም """"""""""""""""""""""""""አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ *************** የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ...
16/02/2023

#ለሕጋዊ የሚድያ ተቋማት በሙሉ፤
የካቲት ፱ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
***************
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ያካበተቻቸውን መንፈሳዊ፣ ቁሳዊ፣ ታሪካዊ እና ኪናዊ ሀብቶቿን በተለያዩ የብዙኅን መገናኛ ተቋማት የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ጉልህ አስተዋጽኦ ስታበረክቱ መቆየታችሁ ይታወቃል።

ስለሆነም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከብዙኅን መገናኛ ድርጅቶች ጋር ተቀራርባ የምትሠራባቸው የተሻለ አሠራር መዘርጋት ትችል ዘንድ የብዙኋን መገናኛ ድርጅቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅና ተሰጥቷቸውና ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ ከቤተ ክርስቲያናችን የሚወጡ መረጃዎችን በኃላፊነት እና መርሕን ባከበረ መንገድ፤ ለተዛባ ትርጉም ሳይጋለጡ እንዲዘገቡ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሚዲያዎች መረጃዎችን በትክክል እንዲያደርሱ የግንኙነት መዋቅር መዘርጋት ይቻል ዘንድ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

ስለሆነም ይህ ማሳሰቢያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የግል እና የመንግስት ብዙኅን መገናኛ ተቋማት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዐውደ ምሕረት እና የአደባባይ በዓላትን ለመዘገብ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየጊዜው የምትሰጣቸውን መግለጫዋች የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት፤ በየአብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ቅርሶችን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና በርካታ ሀብቶችን መሰረት ያደረገ የሚዲያ ሽፋን በመስጠትና ልዩ ልዩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመሥራት ወዘተ... የሚፈልግ ማንኛውም የመንግስትም ይኹን የግል ሚዲያዎች ከዛሬ የካቲት 9ቀን 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በመገኘትና የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰብን አዲስ የሚመሠረት የሚዲያ ተቋምና ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ካልሆኑት በስተቀር ማንኛውም የሚዲያ ተቋም በእነዚህ ቀናት ተገኝቶ ምዝገባ በማከናወን ቤተ ክርስቲያናችን በምታዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ካልተካፈለ በምንም አይነት መንገድ ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት ጥያቄ ቢያቀርብ የማይስተናገድ መኾኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የህዝብ
ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 9 ቀን 2015
የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC

እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ...
08/02/2023

እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል።

በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 7 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።
ቤተመንግስትም ያለህ መከላከያም ያለ የኦርቶዶክስ ልጅ ሥራህን ለማንም ትተህ እንዳትወጣ።

ሃገር በጽንፈኛ እየፈረሰ ከኦርቶዶክሳዊነት ጎን እስከቆመ ድረስ ኢትዮ 360፣የቀድሞ የህወሃት አባል፣ኢህአፓ፣ የመቀሌ ልጅ፣የሱማሌ ፕሬዝዳንት ብሎ መለያየት የለም።ሁሉን በአንድ መስመር ተይዞ ይሄዳል።

==========
ጉዳያችን
=========

እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ምስጢራዊ የኦሮምያ ብልጽግና ቡድን ከአቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስ ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። ግንቦት 24፣2014 ዓም ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካሕናት ጉባዔ
ሲደረግ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅ ምርጫ ሲደረግ የቤተክህነት ምስጢራዊ የብልጽግና ቡድን አቶ አካለወልድን ለማስመረጥ ከፍተኛ ፍትግያ አድርጓል።

በምርጫው ሂደት ላይ ጉባዔውን ለማወክ ግልጽ የሆነ ማስፈራራት ሲፈጸም የኢጣልያ፣ፈረንሳይ እና አካባቢው ሊቀጳጳስ እና የኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ አቡነ ሕርያቆስ ያደረጉት ተጋድሎ በአግባቡ ለሕዝብ አልተገለጸም።አቡነ ሕርያቆስ ጉባዔውን በግልጽ በመገሰጽም ሆነ የምርጫው ሂደት በህገ ወጦች እጅ ሊገባ ሲል ጉባዔውን እረግጠው በመውጣት ምርጫው ትክክለኛ መስመር እንዲይዝ ከፍተኛ ተጽኖ ለመፍጠር የሞከሩበት ሂደት በቤተርክስቲያኒቱ ታሪክ ሲዘከር የሚኖር ነው።

ይህ ብቻ አይደለም አቡነ ሕርያቆስ ምርጫው በመንግስት ማስፈራርያ መሆን የለበትም ብለው ጉባዔውን እረግጠው ከወጡ በኋላ ተለምነው ሲገቡ ምርጫው በሕጉ እንዲፈጸም ቃል አስገብተው ነበር። በመጨረሻም በምርጫው አርባ አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ከተወዳደሩት
1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም 26 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦንስ 12
3. የቀድሞው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ 7 ድምጽ አግኝተዋል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በእጩነት ከቀረቡት መካከል
1. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ 20 ድምጽ በማግኘት ሲመረጡ
2. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 17
3. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ 8 ድምጾች አገኙ።

በቀጣይ ቀናት የብልጽግና የደህንነት ሰዎች በአቶ አካለወልድ አለመመረጥ በመብሸቅ ወደ አቡነ ሕርያቆስ ያረፉበት ቤት ድረስ ተልከው ለማስፈራራት የሞከሩ ሲሆን አቡነ ሕርያቆስም ካለአንዳች ፍራቻ ተገቢውን ምላሽ እንደመለሱ መረጃ አለ።

ይህ ማለት አቶ አካለወልድ በቤተክህነት ሥራ አስኪያጅነት እንዲመረጡ ቢደረግ ኖሮ ምን ዓይነት ከባድ ጥፋት በቤተክርስቲያን ላይ የብልጽግና ቡድን ሊያደርስ በምስጢር ተዘጋጅቶ እንደነበር በሚገባ መረዳት ይቻላል። በመሆኑም አሁን እየተፈጸመ ያለው ቤተክርስቲያንን በግልጽ የመውረር እና የማፍረስ ተግባር መንፈስ ቅዱስ ባወቀ በእነ አቡነሕርያቆስ ላይ አድሮ ጉባዔውን ባያጸና ኖሮ በምስጢራዊ መስመር ከባድ ጥፋት ሊፈጸም እንደነበር በጣም ግልጽ ነው።

በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 20 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ጥረት እየተደረገ ባለበት በእዚህ ጊዜ ብዙ ጥያቄዎች በአዕምሯችን ውስጥ ይመጣሉ።ከእነኝህ ውስጥ 20ዎች ብዬ ለመምረጥ ሞክርያለሁ።በእነርሱ ላይ የራሴን ምላሽ ለመስጠት እሞክራለሁ።እነኝህ ጥያቄዎች ነገ በማኅበራዊ ሚድያም ሆነ ሌላ ቦታ ስናገኝ አንድ ዓይነት ምላሾች እና ምንም ዓይነት መደናገሮች መኖር የለባቸውም።

ጥያቄ = የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደ ፖለቲከኞች በድርድር ይፈታል?

መልስ= ፈጽሞ በድርድር አይፈታም።ያለው መንገድ ቤተክርስቲያንን የከዱት ይቅርታ ቅዱስ ሲኖዶስን ጠይቀው፣የወሰዱትን መልሰው፣የሰበሩትን ጠግነው ሲቀርቡ ብቻ ነው። ፖለቲከኞችም ሆኑ አሁን የህዝቡን መነሳት አይቶ የጽንፍ ኃይሉ እንደፖለቲካ ድርድር የሚለው አሁን የህዝቡን መነሳት እና ነገሩ እንደማያዋጣ ሲያውቁ የሚያቀርቡት ነው።

ጥያቄ = ኦርቶዶክሳውያን የመንግስትን ሥራ ከቤተመንግስትም ከመንግስት ስራም ለቀው መውጣት አለባቸው?

መልስ = ፈጽሞ። መጀመርያ ሥራህ ቤተመንግስት ሆነ ጦር ሰራዊቱ ውስጥ ክልል ሆነ ቀበሌ ለቀህ መሄድ የለብህም። የሚፈለገው ይሄው ነው። በመጀመርያ ሃገሬ የእኔ ነች ማንም በችሮታ የሚሰጠኝ እና የሚነጥቀኝ አይደለችም ብሎ ማመን ያስፈልጋል።ይህንን እምነትህን ነው ቀድሞ ሊነጥቁህ የሚፈልጉት።

ወለጋ ሃገርህ እንዳልሆነ ሊነርግሩ ሲሞክሩ ውስጥህ ሃገርህ ሌላ እንደሆነ የሚስብ ስሜት ሊፈጥሩብህ እንደሞከሩ ተረዳ።ስለሆነም ኢትዮጵያ ሁሉ ሃገርህ፣ስራህ ሁሉ ማንም በችሮታ የማይሰጥህ መሆኑም ማመን እና ባለህበት ሃገርህን እንደምትጠቅም ማመን አለብሕ

ጥያቄ = ቤተክርስቲያንም ሃገሬም ለገጠማት ችግር የእኔ ድርሻ ምንድን ነው?

መልስ = መጀመርያ ባለህበት የሥራ መስክ ይህ ያንተ ግዛት መሆኑን እመን። ቦታህን አትልቀቅ። ቀጥሎ ውጭ ሃገር ሁን ሃገር ቤት፣ቀበሌ ውስጥ ሁን መምህር በእጅህ ባለው እና ባንተ ልክ ልትሰራ የምትችለውን በደንብ ለይተህ በሌሎች የማይደጋገም ሥራ ከአንተ ችሎታ አንጻር መስራት ያለብህን ለይተህ ሥራ። ዝም ብለህ ተመልካች ከሆንክ ከሞተው በላይ ከቆመው በታች መሆንህን እመን።

ጥያቄ = ዐቢይ ነገ በቴሌቭዥን ቀርቦ እያለቀሰ ተሳስቼ ነበር ብሎ ሊቀርብ ይችላል? ይህ ለውጥ ያመጣል?

መልስ = የለቅሶ ድራማ ጠብቅ።ለዓላማ የማይከፈል ነገር የለምና ያደርገዋል። ነገር ግን ባይሳካለትም በህሊናው ግን ቤተክርስቲያኒቱን ሰውቷታል። ቢያንስ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ህገወጦቹን እጅግ በሚያሳፍር ደረጃ ደግፏል።ማንም እንዳያግዳቸው የራሱን ካቢኔ ጨምሮ አስፈራርቷል።የሙስሊሞች ችግር ጊዜ የሰላም ሚኒስቴር መስርያቤት ችግሩን እንዲፈታ ተመድቦ የነበረበት ጊዜ እንዳልነበር አሁን ግን የሰላም ሚኒስቴርን ያስፈራራው እራሱ ጠቅላዩ መሆኑ የሄደበትን እርቀት ያሳያል።

ጥያቄ = ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ሥራ የአካባቢውን ጂኦ ፖለቲክስ ይቀይራል?

መልስ = በትክክል ይቀይራል። ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ሥራ በአንዳንድ መንግስታት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነበር።አሁን ዐቢይ ይህንን መነገጃ ለማድረግ ግልጽ ድፍረት አሳይቷል።ቤተክርስቲያን መፍረሷ ደግሞ ጂኦ ፖለቲካውን ያበላሻል ያሉ እንደሩስያ ያሉ መንግስታት በጥብቅ ጉዳዩን እየተከታተሉ ለመሆኑ አምባሳደሩ የሰጡት የሰሞኑ መግለጫ ማሳያ ነው።

አምባሳደሮች በአንድ ሃገር የውስጥ ጉዳይ ብዙ አስተያየት አይሰጡም።የሩስያው አምባሳደር ይህንን ያህል እርቀት የሄዱት የቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ የጂኦፖለቲካ ጉዳይ ላይ የሚያዛንፈው ብዙ ጉዳይ ስላለ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ጥያቄ = ስሜታችን በንዴት እንዲጎዳ የሚያደርጉ ሥራዎች ሲገጥሙ ምን ላድርግ?
መልስ = በወቅቱ ሁኔታ መበሳጨት ተፈጥሯዊ እና ጤነኛነት ነው።ነገር ግን የቤተክርስቲያን ጠላቶች ዋና ግብ ማበሳጨት ብቻ ሳይሆን ተስፋ የቆረጥክ እንድትሆን ምስጢራዊ የስነ ልቦና ዘመቻ ማድረግ ነው። በመሆኑም አንዳንዴ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሱ መሪዎች እየገለፈጡ በተነሱት ፎቶ በኢቲቪ እንዲታዩ የሚያደርጉት የተረጋጉ ለመምሰል እና የስነ ልቦና ጦርነት ለማድረግ እንደሆነ በሚገባ ተረዳ።

እራስህን አረጋግተህ ለሃገርህም ሆነ ለቤተክርስቲያንህ የሚገባውን ከራስህ ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት እና ኃይል ጋር እራስህን በራስህ አስታጥቅ እንጂ እየተበሳጨህ እራስህን አትጉዳ።ሥራ የሚጀምረው ምን ሰራሁ? ከሚል የራስ ጥያቄ ነው።

ጥያቄ = የሃይማኖት ጉዳይ ሲሆን ብቻ ልናገር ፖለቲካ ይቅርብኝ?

መልስ = ይህ ዛሬ ለደረስንበት ደረጃ ያበቃ የስህተት አስተሳሰብ ነው።አሁን ቤተክርስቲያንን እያመሰ ያለው የዶግማ ጉዳይ አይደለም። የጎጠኛ ፖለቲከኞች ከህወሃት ኢሃዴግ እና ብልጽግና እየተወራረሱ ያመጡት የዘር ፍጅት ፖለቲካ ነው።ስለሆነም መሞገት ያለብህ ፖለቲካውንም ጭምር ነው። ቤተመንግስቱ ሲስተካከል ቤተክህነቱ ይረጋጋል። ቤተመንግስቱን ትቼ ቤተክህነቱ ላይ ብቻ ልመልከት ካልክ ያለፈውን ስህተት ትደግመዋለህ። ቤተክርስቲያን ጎጥ አትቀበልም።ይህ ሃይማኖታዊ መልዕክት ነው።

ጳጳሳት ሳይቀሩ የመንግስት ጎጠኛ መንግስት አንቀበልም ማለት ይችላሉ።ማውገዝም ይችላሉ። ቤተክርስቲያኒቱ የጎጥ ፖለቲካ መንቀል በትክክል ትችላለች።ይህ ደግሞ ፖለቲካ አይደለም። ሃይማኖታዊ መልዕክት ነው።ጎጠኝነት ክርስቲያናዊ አለመሆኑን በመንገር እና በመቃወም ብቻ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ማቆም ይችላሉ።ይህንን የጎጠኘነት ፖለቲካ መቃወም ከካህን እስከ ዲያቆን፣ከጳጳስ እስከ ምዕመን ሊቃወመው የሚችለው አጀንዳ ነው።

አበቃሁ!
============////=========
Getachew Bekele

( #ፍቅርን ከክርስቶስ ትህትናን ከማርያም ያልተማረ አገልጋይአይሆንም ምሳሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ) #ለታመሙት ላኩላቸው!“ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን  #ሽምግሌዎች ወደ...
05/02/2023

( #ፍቅርን ከክርስቶስ ትህትናን ከማርያም
ያልተማረ አገልጋይ
አይሆንም ምሳሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ)

#ለታመሙት ላኩላቸው!

“ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን #ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው #ይጸልዩለት።”
— ያዕቆብ 5፥14

ለታመሙት ሽማግሌዎችን ላኩላቸው ከህመማቸው ከያዛቸው የዘር፣ የአጋንት ደዌ ለፍልፈውም ሆነ ጩኸው እንዲለቃቸው,,,,

“እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም #ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።”
— ማቴዎስ 18፥17

#የሽማግሌዎችን ፀሎት ባይሰማ ለቤተክርስቲያን ንገራት የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስ እንደስፍራቸው ይሰጣቸዋል። እንደቁራጭም ይጣላሉ።

"ሰላም ለኪ ቅድስት ቤተክርስቲያን አምሳለ ገነት ሰላማዊት"

#ለመበተን ሲጥሩ አንድነታችንን አጠነከሩ!!

28/05/2015

 #በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዳግመኛ ጥር ሃያ አምስት በዚህች ቀን ሰማዕቱ  #ቅዱስ መርቆሬዎስም በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከ...
02/02/2023

#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ዳግመኛ ጥር ሃያ አምስት በዚህች ቀን ሰማዕቱ #ቅዱስ መርቆሬዎስም በሥዕሉ ላይ አድሮ ቅዱሳን የሆኑ ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በመርዳት ከሃዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡

⛪️ #መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡

ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡

⛪️ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡

አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡

እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡

⛪️ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡

ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡

⛪️መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡

ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡

⛪️ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡

ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡

⛪️ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡

እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡

⛪️ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡

የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡

ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡

⛪️ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡

⛪️መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡

ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዓይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡

ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

👉 "ዲያቆን ሙሉቀን ግርማ"

 #የወደ ፊት ስጋቴ...:እኔ ድንቅ ልጅ ሲባል የማዉቀዉ...ያለእድሜያቸዉ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተካኑ እና ብዙ ሚያውቁ፥የፈጠራ ስራ ላይ ቀድመዉ የሚገኙ፥በጠቅላላ እዉቀትና IQ ከእኩያቸዉ ል...
01/02/2023

#የወደ ፊት ስጋቴ...
:
እኔ ድንቅ ልጅ ሲባል የማዉቀዉ...
ያለእድሜያቸዉ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተካኑ እና ብዙ ሚያውቁ፥
የፈጠራ ስራ ላይ ቀድመዉ የሚገኙ፥በጠቅላላ እዉቀትና IQ ከእኩያቸዉ ልቀዉ የሚገኙ ህጻናትን እንጂ ምላሳቸዉ የምትቅለበለብ ልጆችን አይደለም::

ከምላሳቸዉ የሚፈጥኑ እንዲህ አይነቶቹ ህጻናት የዘመኑ ልጆች የሁሉም ካራክተር ነው፥ብትፈልጉ በየቤቱ ነፍ ናቸዉ።

በትምህርት በቴክኖሎጂ ምጡቅ የሆኑ ጎበዝና አሰተዋይ ህፃናት ማፍራት ትተን አፈቀላጤ ህጻናትን የምንሸልም ከሆነ የምናፈራቸዉ ህጻናትም ከምላሳቸዉ የፈጠኑ ፥ከሳይንስ ከጥበብና ቴክኖሎጂ ግን የራቁ እንደሚሆኑ አትጠራጠሩ።

ሶፊ ከመቂ

 #ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች:ትዳር~ማለት 1 ወንድ አንድ ሴትትዳር~ማለት 1 እምነት አንድ እዉነትትዳር~ማለት 1 እሳት አንድ ዉሃትዳር~ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎትዳር~ማለት 1 መጥፎ አ...
31/01/2023

#ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች
:ትዳር~ማለት 1 ወንድ አንድ ሴትትዳር~ማለት 1 እምነት አንድ እዉነት
ትዳር~ማለት 1 እሳት አንድ ዉሃትዳር~ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
ትዳር~ማለት 1 መጥፎ አንድ ጥሩትዳር~ማለት 1 ጉልቻ አንድ ድስትትዳር~ማለት 1 ወንዝ አንድ ዉሃ የሚቀዳ ቢሆንም ካልተሳሰቡ እና ካልተቻቻሉበት ሊደርቅ የሚችል ወራጅ ወንዝ ነዉ;;

አስተዉሉ
ሴት ልጅን ባሏ ያመሰግናታል
የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል

ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች
ዘመኑም በሰላም ይጨርሳል
ደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነዉ::

#እግዝአብሔርን የሚፈራ ሰዉንም ወደ ዕድሉ ታደርሰዋለች
# መፅሐፈ ሲራክ 26፥1_3
ፈጣሪ በፍቅር ያማረ ትዳር እና ሠላም ያለዉ ፍቅር ይስጣችሁ!

Address

Addis Ababa
2121

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Degsew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Degsew:

Share