10/12/2023
መልኬ በቃኝ
የነበረ ሀሳብ ቴዲ አፍሮ ሲነካው አዲስና ድንቅ ይሆናል። ሌሎች የነካኩት በብዙም ተጠበብንበት ያሉት ርዕሰ ጉዳይ በቴዲ አፍሮ ብዕር ሲወለድ የደነቀ ነገር ሆኖ ይገኛል። ምነው መልኬ ብቻ በቃኝ አልሽ ሲባል ሰምታቹ አታውቁም...? እናቶች ልጃቸው ሙያ አለምድ ብትላቸው ይኼን ቃል ይጠቀሙታል። ሴት ልጅ በጣም ውብና ተወዳጅ፣ ተፈቃሪ እንደሁም እንክብካቤ የሚገባት ፍጡር ብትሆንም መልኳ ብቻ ግን ለነዚህ ሁሉ ክብር አያበቋትም። አንዲት መልከመልካም (ቆኔጆ ሴት) መልኳ ላይ ጠባይና ሙያ ካልታከለበት በማህበረሰቡ ዘንድ እንደ እናቷ በትዳሯ ተከብራና ታፍራ አትኖርም።
መጠሪያ ወንድ ያላት ሴት (የእግሌ ሚስት ነች የምትባል ሴት) ከምድራችን አደገኛ ሴቶች በላይ ትፈራለች። ዘውድ እንደጫነች ንግሥትም የታፈረች ነች። አልያ ግን መንገደኛው ወንድ ሁሉ ጭኗን ለመግለጥ (ለማርከስ) ይመኛታል። ከዚህ በዘለለ ክብር የሚፈልጋት ወንድ ባሏ ብቻ ነው። "መልኬ በቃኝ" ያለች-እንደው ግን፥ ሁሉም ወንድ የሚመኛት የጤዛን እድሜ ያህል ብቻ ይሆናል። በቃ ሴት ከሆንሽ መልክሽ ብቻ አይበቃሽም።
በዘመናችን የነበሩ ቆነጃጅት እንስቶች በውበታቸው ተመክተው ከአንዱ መሆን ከብዷቸው ሲመርጡና ሲያማርጡ ቆይተው በስተመጨረሻ ነገራቸው እንዳይሆን ሆኖ የቀሩ ብዙ ናቸው። ጠባይዋ ምናባቱ መልኳ ድንቅ ነው ብሎ ሊችል ያገባት ወንድ ሁለት ልጅ ከወለደችለት በኋላ አይኗን ማየት እስኪያስጠላው የደረሰ ብዙ ወንድ አለ። መልክሽ ብቻውን እንደ አንድ ቀን የጠሐይ ውሎ ነው።
የኔ ቅንጆ አዎ በጣም ቆንጆ ነሽ ግን መልኬ በቃኝ አትበይ ጸባይ አክዪበት። ይኼን ምክር የቀደሙ ጠቢባን አባቶችም ለልጆቻቸው ይመክሩ ነበር። ምክኒያቱም የሴት ልጅ ውበቷ እንደ ጤዛ ረጋፊ መሆኑ ይታወቃልና። ጸባይ ግን ያድራል። ያሳድራልም። ቴዲ አፍሮ ይኼንን የተለመደ ሀሳብ ነው ይዞ የመጣው። ግን እንዴት ደረደረው...? ብለው ቢመረመሩ ነገሩ ይደንቃል። አበባ መአዛ ከሌለው ንብ እንደማያርፍበት ሁሉ ቆንጆ ሴትም ጠባይ ከሌላት ባል አይኖራትም ሲል በቅኔ ከቁንጅና ጠባይ እንዲልቅ ያስተምራል።
የውበትን ከንቱነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ያነበበው የክቡሮ ዶክተር ቁንጅና ለጊዜው ዘለዓለማዊ መስሎ ይሞሸር እንጂ የቅርብ ሚዜው ሞት ነው ሲል ውበት ከሰናይ ጠባ ከራቀ ለሙሽራ ሚዜ ቅርቡ እንደሆነ ያህል ቁንጅናም ለሞት ቅርብ የሆነ መሆኑን ያስተምራል።
"አምሮ ጽጌሬዳ ቢታደል ውበትም
ከሌለው መአዛ ንብ አያርፍበትም"
በዚህ አጋጣሚ "ልዑል" የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ ስብስብ ለማድመጥ በሚቀላችሁ ዲጂታል መተግበሪያ ላይ Leul Sisay በማለት እድታደምጡ እጋብዛለሁ።
✍ (ነፃ ብዕር)