Meselech mamo wolaita

Meselech mamo wolaita Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Meselech mamo wolaita, Art, Wolaita, Addis Ababa.

19/09/2025

Wolaytta Soddo Ambba Ballotaa Yamiyaa ayssya k/proof. Phawulossa zagayee aattido Gifaataa baalaa lo"o amuwaa"

"Wolaytta layttaa laamiya gifaataa baalawu hashshu saro gattees.

Yooyo gifaataa!

Gifaatay Wolaytta deriya laytta lamiya gallassa. Gifaatay wontto Woggaa galla /Shuha Woggaa galassi gita hombbocida hanotan Sooddo toho kuwaasiya denbban bonchchetees.

Wolytta laytta laame gifaataa baalay ubba asaassi saro, payatetta, siiqo ufayssanne baalota baala gidana mala amottaysi."

የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ የጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፣

"ለወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ዮዮ ጊፋታ!! ጊፋታ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ነው።

በዓሉ በቀጣይ እሁድ ዕለት /Shuha Wogaa/ በሶዶ ሁለገብ ስቴዲየም በአደባባይ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።

ለመላው ወላይታ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆን እመኛለሁ።"
ዮ ዮ ጊፋታ!!

Yoo Yoo Gifaataa
ዮዮ ጊፋታ!
ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ
የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
መስከረም 9፣ 2018 ዓ.ም
ዮዮ ጊፋታ

03/09/2025

የ1500ኛውን የነቢዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በማስመልከት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማሪያም ለእስልምና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ።እንደሚከተለው ይቀርባል ።

እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በአል ህዝበ ሙስሊሙን በሰላም አደረሳችሁ ያሉት ከንቲባዋ ነብዩ መሐመድ(ሰዓወ) በእስልምና ሀይማኖት በነበራቸው አስተምህሮት የሰው ልጆች ያለ ዘርና ሃይማኖት ልዩነት የምድር ፍጡራን ሁሉ እኩል መሆናቸውን ሲያስተምሩ መቆይታቸውን በማውሳት የመወሊድ በዓል የመቻቻልና የመከባበር ተምሳሌት የሆነ በዓል በመሆኑ አርአያነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል ።

በዓሉን ስናከብር የበዓሉ እሴቶች የሆኑትን የመርዳት፣ የወደቁትን የማንሳት፣ የታረዙትን የማልበስና የተራቡትን የመመገብ ተግባራት የበለጠ በማጠናከር ሊሆን ይገባል ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል ።

ኢድ ሙባረክ -መልካም በአል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ
ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማሪያም

03/09/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ ለነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓልን አስመክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1500ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የእስልምና፣ የክርስትና፣ እና የሌሎችም ነባር እምነቶች ሀገር በመሆኗ፣ ሕዝቦቿ፣ በእምነቶቻቸው አይደራደሩም፡፡

በዓሉን ሰናከብር የመረዳዳት በዓለችን በመውሊድ ቀን ብቻ ሳይሆን የእለት ተዕለት ተግባራችንና በትውልድ ቅብብሎሽ የሚቀጥል በመሆኑ የዘንድሮውን በዓል ስናከብር የመረዳዳት፣ የመተዛዘንና በጋራ መስራት የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ በዚሁ አጋጣሚ ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

እንዲሁም ሰው ተኮር እና በፈጣሪ ዘንድም ትልቅ ዋጋ ያለውን ትለቅ ተግባር የሆነውን አቅመ ደካሞችን፥ ረዳት የሌላቸውን አረጋውያን፥ አዛውንቶችን እንዲሁም ወላጅ አጥ የሆኑ ሕፃናትን እንድንደግፍ እና ካለን እንድናካፍል ቤተሰባዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ በዓሉ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላም፤ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ረ/ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ
የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

03/09/2025

የ2017 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች በመላው ሀገሪቱ ይከበራሉ

25/08/2025

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ረ/ፕ ዘገዬ ጳውሎስ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት የብዙዎች እምባን ያበሰ 106 ቤቶችን በአንድ ጀምበር ገንብተናል ብለዋል።

በከተማው በአንድ ጀንበር 102 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን ለመገንባት ታቅዶ ከዕቅድ በላይ መፈጸሙን አስታውቀዋል።

በዚህ ትልቅ የህሊና እረፍት የሚሰጥና በፈጣሪም ዘንድ ዋጋ ያለው ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት በሙሉ በከተማው መንግስትና በራሱ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በጎ ተግባር ጧሪ ያጡ ወገኖቻችን፣ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን እምባን የሚያብስ ከመሆኑ በላይ ትልቅ የህሊና እረፍት እና በሰማይ ፈጣሪም በምድር በሰው ልጆችም ዘንድ ትልቅ በርከት የሚሰጥ በመሆኑ ባህል አድርገን ማስቀጠል አለብን ብለዋል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ረ/ፕ ዘገዬ።

ፓርቲያችን ብልጽግና ሰው ተኮር ከመሆኑ የተነሳ ሰው ተኮር የሆነውን በጎ ተግባር አብሮነትን የሚያጠናክር፣ የወንድማማችነት እና እህተማማችነትን ለማጎልበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ የገለጹት የመንግስት ዋና ተጠሪው በጎነት ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ መገለጫ እንደሆነም ገልጸዋል።

መላው የከተማው ህዝብ በዚህ መልካም ተግባር ላይ ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመሳተፍ የታቀደው እንዲሳካ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋና በድጋሚ አቅርበዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር ዘገዬ ጳውሎስ
የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ

04/07/2025

ግብርን በታማኝነት መከፈል አዳጊ የህዝባችንን ፍላጎቶች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ያስችላል፦ አቶ ፀጋዬ ተ/ሀይማኖት

13/04/2025

I am True wolayitta

08/04/2025
08/04/2025
08/04/2025

My generation Tower in Wolaita S**o, October 9
Welcome # Rophnan
Somebody say s**o!

Address

Wolaita
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meselech mamo wolaita posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category