ንስር Tube

ንስር Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ንስር Tube, Addis Ababa.

ንስር Tube (Nisir Tube) 🦅 - ዜናዎችን ከከፍታው ይመልከቱ።
​በኢትዮጵያ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ አስፈላጊ መረጃዎችን፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ጥልቅ ትንታኔዎችን እናቀርባለን።
​🎯 የንስር ዓይን ያለው እይታ፡ ከላይ በመሆን ያልተሰሙ እውነታዎችን እናሳያለን።
​ለፈጣን እና አስተማማኝ መረጃ ተከታተሉን!

04/02/2026

እየሞከርኩ ነው

02/02/2026

ጊዜው አሁን ነው! (አንድ ሼር ትርጉም አለው!)
የነፂን ቤተሰብ ለማገዝ ጊዜው አሁን ነው! ሀዘናችንን ለመግለፅ እንደተረባረብነው ሁሉ እንደ አቅማችን የነፂን ቤተሰቦች ከጎናችሁ ነን እንበላቸው! የጎፈንድሚ ሊንኩ ኮመንት ስር አለ! የቻልን በገንዘባን ያልቻልን ደግሞ ሼር በማድረግ ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን እንግለፅላቸው!

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህይወቱ ያለፈው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ነው።  ሰይፉ ፋንታሁን ይናገራል። ሰይፉ ፋንታሁን በቅርቡ በዝግጅቱ ላይ እንደገለጸው፣ የኪነጥበብ ሰው ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት...
26/01/2026

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህይወቱ ያለፈው በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ነው። ሰይፉ ፋንታሁን ይናገራል።

ሰይፉ ፋንታሁን በቅርቡ በዝግጅቱ ላይ እንደገለጸው፣ የኪነጥበብ ሰው ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት የተከሰተው በድንገት በቤቱ ውስጥ ነው።

በዚያን እለት ጠዋት ነፃነት ከቁርስ ጋር ጁስ መጠጣት ፈልጎ ከጠጣ በኋላ ወዲያውኑ እንዳስመለሰው እና ቤተሰቦቹም በድንገት በመደናገጥ ለጓደኞቹ ደውለው የጠቢታ አምቡላንስ በፍጥነት መድረሱን ገልጿል።

አምቡላንሱ በቦታው ደርሶ ኦክስጅን ለመስጠት ቢሞክርም፣ ወደ ያኔት ሆስፒታል እንደደረሰ ሐኪሞች ነፃነት አስቀድሞ ህይወቱ ማለፉን አረጋግጠዋል።

ሰይፉ ይህንን መረጃ የሰጠው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "ሆስፒታሉ አልተቀበለውም ወይም በቸልተኝነት ነው የሞተው" የሚሉ የተሳሳቱ ወሬዎችን ለማረም ሲሆን፣ የሕክምና ባለሙያዎቹ የሚችሉትን ሁሉ ጥረት ማድረጋቸውን እና ነፃነት ሆስፒታል ከመድረሱ በፊት ህይወቱ ማለፉን በዝርዝር አስረድቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ፡ በቆሼ አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል!በአዲስ አበባ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የማህበር ቤቶች ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተነስቷል። ከአካባቢው የሚወጡ...
25/01/2026

የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ፡
በቆሼ አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከስቷል!

በአዲስ አበባ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የማህበር ቤቶች ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተነስቷል።

ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አደጋው በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

* እባካችሁ በስፍራው የምትገኙ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችና ተሽከርካሪዎች በሙሉ ትኩረት ወደ ስፍራው በማቅናት የሰዎችን ህይወት እንድታተርፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

* እባካችሁ ለእሳት አደጋ መኪናዎች መንገድ በመልቀቅና የሚቻለውን ትብብር በማድረግ ተረባረቡ።

ፈጣሪ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ይሁን።
ህዝባችንን ከአደጋው ይሰውርልን።

የሀዘን  ዜና፦ ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየበኢትዮጵያ የጥበብ ዓለም ውስጥ ስመጥር እና በሁላችንም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረው ባለሙያ ነጻነት ወርቅ...
16/01/2026

የሀዘን ዜና፦ ተወዳጁ የኪነጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ የጥበብ ዓለም ውስጥ ስመጥር እና በሁላችንም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበረው ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ (ነፂ) ባደረበት ድንገተኛ ከዚህ ዓለም መለየቱን በከፍተኛ ሀዘን ሰምተናል።

ነፃነት ወርቅነህ በተለይም በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት የሚተላለፈው በብዙ ቤቶች ዘንድ በሚወደው የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢነቱ ይታወቃል።

ከፕሮግራም አቅራቢነቱ ባሻገር፣ በበርካታ ፊልሞች ላይ ባሳየው ድንቅ የትወና ብቃቱ እና ልዩ በሆነው የሰው አክባሪነቱ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ነበረው።

የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ናት፤ ትላንት ማታ "ቻው" ብሎ የተለየን ሰው፣ ዛሬ በቤቱ በዛው ላይመለስ ይሄዳል ብሎ ማን ይገምታል? ነፂ የኛ ምስኪን፣ ነፂ የኛ የዋህ... እንዲህ በድንገት መለየትህ መላውን የጥበብ ቤተሰብና አድናቂዎችህን በሀዘን ሰበር አድርጎናል።

ነፃነት ወርቅነህ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር። ባበረከታቸው ስራዎችና በደግነቱ ሁልጊዜም በልባችን ሲታወስ ይኖራል።

ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የጥበብ አፍቃሪዎች ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።

ነፍስህን በገነት ያኑራት!
ነፂ የኛ ምስኪን

😭😭😭

ንስር Tube

16/01/2026
የአደይ አበባ ስታድየም ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ::ግዙፉና ዘመናዊው የአደይ አበባ ስታድየም ዋናው የመጫወቻ ሜዳ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) የተደረገለትን ጥብቅ ግምገማ በ...
14/01/2026

የአደይ አበባ ስታድየም ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ::

ግዙፉና ዘመናዊው የአደይ አበባ ስታድየም ዋናው የመጫወቻ ሜዳ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) የተደረገለትን ጥብቅ ግምገማ በስኬት አጠናቋል።
እንደ መረጃው ከሆነ፣

የስታድየሙ መጫወቻ ሜዳ በፊፋ ባለሙያዎች የተደረጉለትን ልዩ ልዩ ቴክኒካዊ ቴስቶች በከፍተኛ ውጤት በማለፉ ነው ይህ ይፋዊ እውቅና የተሰጠው። ይህም ሜዳው ደረጃቸውን የጠበቁ ዓለም አቀፍ ግጥሚያዎችን ለማስተናገድ ሙሉ ብቃት እንዳለው ማረጋገጫ ሆኖታል።

ይህ ስኬት ለአገራችን እግር ኳስ እድገትና ለደጋፊዎቻችን ትልቅ ብሥራት ነው።

እንኳን ደስ አለን!

ንስር Tube

🦅 🦅 🦅

ከንቲባ  ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህመም ላይ ያለውን ማስተር አብነት ከበደን ጎበኙየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በበጎ አድራጎት ስራው የሚታወቀውንና በአሁኑ ወቅት...
14/01/2026

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህመም ላይ ያለውን ማስተር አብነት ከበደን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በበጎ አድራጎት ስራው የሚታወቀውንና በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ የሚገኘውን ማስተር አብነት ከበደን በአካል በመገኘት ጠይቀዋል።

ከንቲባዋ ማስተር አብነት ለወጣቶች ያለውን አርአያነት በማድነቅ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡-

"በማህበራዊ በጎ አድራጎት ስራህ ለብዙ ወጣቶች ምሳሌ የሆንከው ማስተር አብነት ከበደ ፈጣሪ አምላክ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈውስህ ፀሎታችን ነው።

ያንተ አርአያነት በርካታ በጎ አድራጊ ወጣቶችን ማፍራት የሚያስችል ነው።"

ማስተር አብነት ከበደ በተለይም አቅመ ደካሞችን በመርዳትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮት ያለው ወጣት ነው።

ለማስተር አብነት ከበደ ፈጣን ምህረትና ጤናን እንመኛለን!

ንስር Tube

_____ምስጋና ______Ishow speed ሃገራችን ከመጣ በሗላና ላለም መልካም ባሃላችንን፣ ከተማችንን ብቻ ባጠቃላይ ብዙዎቻችንን ከልብ ያስደሰተ ስራ ተሰርቷል። አሁን አንድ በአንድ ማመስ...
14/01/2026

_____ምስጋና ______

Ishow speed ሃገራችን ከመጣ በሗላና ላለም መልካም ባሃላችንን፣ ከተማችንን ብቻ ባጠቃላይ ብዙዎቻችንን ከልብ ያስደሰተ ስራ ተሰርቷል። አሁን አንድ በአንድ ማመስገን እፈልጋለው።

✦መጀመሪያ ለ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ታኮራላችው ስረ አታችው አንድ ሰው እንኳን ገንዝብ ስጠኝ ብሎ የቀፈለው የለም(መርካቶ ላይ ብቻ ሁለቱ ሴት ነጋዴዎች 6000 ብር ቲ ሸርት የሸጣች ሁለት ገቢዎች ይጎብኛችው)

✦ጠሚ ዐብይና ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ልፋታችው ከንቱ አልሆነም ፈጣሪ ጠብቆ ለ አለም ያሁሉ ትግላልችውን ህልማችውን እንዲያይ አድርጎታልና። ይህ የጽዳትና የኮሪደር ስራ ባይሰራ ከተማዋ ጃጅታ ነበር። እናመሰግናለን

✦ አዶናይ፣ እኔ ላንተ ቃላት የለኝም። አንተኮ ሶሻል ሚድያ ላይ ያለነውን ሰዎች ሁሉ አመለካከት የቀየርክ ቅን ሰው ነህ። ለኛው ልጅ ስትል ስትገፋ ታውቂ ሆነህ እኔ ታዋቂነኝ ብለህ ፎቶ እንኳን እንነሳ ያላልክ፣ እንደዛ የተፋለጥክ ኢትዮ ስፒድን ታዋቂ ያረከው፣ ህልሙን ያስካህለት ሰው ነህ። ብቻ እንወድሃለን ማርከኸናል።

✦ሚስ ኢትዮዽያ ሃሴት፣ አቤት ውበት አቤት ሴትነት ፣ አትቀለቀል እዩኝ እዩኝ አላለች፣ የመግባባት ችሎታዋ ብቻ ድንቅ ነበረች።

✦የቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ ታሪካችንን፣ ባሃላችንን፣ የቦታ አመራረጣችው ምን ለበል በጣም አኩርታች ሁናል እናመሰግናለን
ጥቁር ልብስ ለብሰህ ስታስተረጉም የነበርከው አንተ ባትኖር ብዙ ይጎድል ነበር፣ ታሪካችንን አጉልተህ ለአለም እንዲሰማ ስላደርክ እናመሰግናለን

✦ሼፍ ማርከስ፣ የፍንዳቃ ባሃል ማእከል፣ ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል፣ ስካይ ላይት ሆቴልስ ሳይንስ ሙዚየምና፣ መብራት ሃይል ሌሎችም

✦በመጨረሻም ተማር ልጄ ብለው ለሚመክሩን ቤተሰቦቻችን ትናንትና ምን ያህል መማር፣ ቋንቋ ማወቅ እንደሚጠቅም ያየነበት ቀን ነው። ቤተሰቦቻችን እናመሰግናለን መማር ውጤቷ ብዙ ነው

ብቻ የተዋጣ ቆይታ በልባችን ደስታን የፈጠረ ሃገራችን ከሰራን ትልቅ እንደምትሆን ያየንበት፣ ከተዋደድን፣ ከተክባበርን ምን ያህል ሃብት እንዳለን ያሳየች ቀን ነበርች የትናንቷ ቀን

Source: Lemman Tsegaye

Thank you My people... Love you on behalf of Addisout Media.

ዜና ከቅን ልቦች፦ የታህሳስ ወር የክብር አሸናፊዎች ታወቁ! የታህሳስ ወር የማህበራዊ ሚዲያ ተፅኖ ፈጣሪ ውድድር በታላቅ ፉክክር ተካሂዶ አሁን አስደሳች ውጤት ላይ ደርሰናል። በወሩ ማጠቃለያ ...
12/01/2026

ዜና ከቅን ልቦች፦
የታህሳስ ወር የክብር አሸናፊዎች ታወቁ!

የታህሳስ ወር የማህበራዊ ሚዲያ ተፅኖ ፈጣሪ ውድድር በታላቅ ፉክክር ተካሂዶ አሁን አስደሳች ውጤት ላይ ደርሰናል።

በወሩ ማጠቃለያ ላይ የነበረውን ውጤት በጥቃቅን መረጃዎች ከመረመርን በኋላ፣ በዚህ ወር ሁለት ተፅኖ ፈጣሪዎችን ለመሸለም ወስነናል!

ለምን ሁለት አሸናፊዎች ተመረጡ?

1. ሜላት ንጉሴ (Melat Negusse):

በኤስ ኤም ኤስ (SMS) ድምፅ አሰጣጥ እና በዳኞች ከፍተኛ ነጥብ በማግኘት የውድድሩ ቀዳሚ አሸናፊ ሆናለች።

2. አዶናይ (Adonay):

የቅን ልቦች የሁልጊዜ አጋር በሆኑት ጉርሻ ፔጅ እና ፋስት መረጃ ገጾች ስር የሚሰጡ አስተያየቶችን (Comments) እንቆጥራለን ባልነው መመሪያ መሰረት፣

አዶናይ በነዚህ ገጾች ላይ እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ድምፅ በማግኘቱ የክብር አሸናፊ እንዲሆን ተወስኗል።

የቅን ልቦች አዘጋጆች ሁልጊዜም ግልፅነትን እና ፍትሃዊነትን መመሪያችን በማድረግ፣ በዳኛም ሆነ በህዝብ ድምፅ ተመራጭ የሆኑትን ማበረታታት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።

ስለዚህ በበጎ ስራቸውና በማህበራዊ ሚዲያ ተፅኖአቸው ህዝብን እያገለገሉ ላሉት ለእነዚህ ብርቱ ወጣቶች ሽልማቱ ይገባቸዋል።

የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?
ሁለቱም አሸናፊዎች መሸለማቸውን እንዴት አያችሁት?

የእርስዎን ድጋፍና ደስታ በኮመንት ይግለጹላቸው!
ለሁለቱም እንኳን ደስ አላችሁ!

©️ቅን ልቦች

ንስር Tube

🦅 🦅 🦅

Address

Addis Ababa
1001

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ንስር Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to ንስር Tube:

Share