04/04/2020
🔵 Artist-ንዋይ ደበበ
Song-አልዋሽም
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለው
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ ተክዛለው
ጨዋታና ሳቅሽን አስታዉሼ እህ እላለው
ተክዛለዉ
አስባለው
አስባለዉ
እንግዲያው አንቺም ከተለየሽኝ ከራቅሽኝ አስታውሺኝ
በፍቅር ከልብ ከአንጀት ከሆድሽ ውስጥ አታውጪኝ
እንዳረሳሁሽ አደራ አንቺም አትርሺኝ አስታዉሺኝ
ፍቅሬ አስቢኝ አስቢኝ አስታዉሺኝ
እንደም ነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደምነሽ እንደምነሽ
ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለው መች ትመለሻለሽ
ለብቸኝነቴ ለብቸኝነቴ ለአዲሱ እንግዳዬ
ትካዜ ብቻ ነዉ መስተናገጃዬ
እንደምነሽ ብዬ ሁሌ አስብሻለዉ
በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለው
እንደምነሽ ብዬ ሁሌ አስብሻለዉ
በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለውየኔ ፍቅር(2×)
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን
ክጄ አላበላሽም
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለው
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ ተክዛለው
ጨዋታና ሳቅሽን አስታዉሼ እህ እላለው
ተክዛለዉ
አስባለው
አስባለዉ
እንደ ምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደ ምነሽ እንደምነሽ
ኧረ እንዴት ነሽ
ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለው መች ትመለሻለሽ
ናፍቆትሽ በአይኔ ላይ
ናፍቆትሽ በአይኔ ላይ
ከተመላለሰ
የፍቅር እመቤቴን አንቺን ካስታወሰ
እንደምነሽ ብዬ አስታውስሻለው
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለው
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለው የኔ ፍቅር
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለው(2×)
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን
ክጄ አላበላሽም(3×)
▶️🎙የተለያዩ ሙዚቃዎች(ግጥሞች)ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑት
🔴ቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኙታል
🔵 Https://t.me/pro5mobile