የፍቅር ነገር

የፍቅር ነገር ለሁሉም ስው ፍቅር አስፈላጊ ነውና ኢትዮጵያን በፍቅር እንኖር ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!

"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው ራሱን ሳይሆን ሌሎችን...
28/01/2025

"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው ራሱን ሳይሆን ሌሎችን ነው። ከዚያ ባደገ ቁጥር ሰዎችን ጠልቶ ራሱን መውደድ ይጀምራል። ......እና እንዳልኩሽ አንድ ሰው ሀገር ከመግዛት እራሱን መግዛት ይከብደዋል፣ እራሱን የገዛ ሰው ግን አለምን መግዛት ይችላል። ስለዚህ እራስን መውደድ፣ መግዛት እና ማሸነፍ ከሁሉም ይቀድማል።....."
".......ሁሌም ከማንም እንደማታንሺ አስቢ፣ ለእራስሽ ክብር ስጪ፣ ራስሽን ውደጂ፣ ሁሉንም እችላለው ብለሽ ተነሺ፣ ፈተናዎችን በጥበብ እንደምትወጪ እመኚ፣ አንብቢ፣ ሁሌም ለነገሮች ዝግጂ ሁኚ፣ ያኔ ሁሉም ሰው ያከብርሻል። ሁሉንም ታሸንፊያለሽ፣ ሁሉም ይወድሻል። ሰነፍ አትሁኚ፣ የሰው ልጅ ውድቀት የሚጀምረው በስንፍናው ነው። ሰነፍ ሰው መጥፎ ነገሮሽን ሁሉ በጫንቃው ይሸከማል። ምክንያቱም በስንፍናው ስጋው የሚበላው ያጣልና። ሰው ሰነፍ ከሆነ የሰውን ይመኛል። ሌባ ይሆናል፣ ውሸትን ይናገራል፣ ነውርንም ይፈጽማል። ስለዚህ ብርቱ ሰው መሆን አለብሽ። አንቺ ማንንም መፍራት እና እንደዚህ ይሉኛል ማለት የለብሽም!! አንቺ በትክክል መልእክትሽን ካስተላለፍሽ ምን ችግር አለው ሰው የፈለገውን ቢል?? ሰውን አክብሪ!!!....."
ከ "ውብ" መጽሐፍ የተወሰደ
4ተኛ ዕትም በቅርብ ቀን!
ከጃዕፈር መጽሐፍ መደብር ያገኛሉ!

መልካም ሀሳብ መልካም ቀን!
22/01/2025

መልካም ሀሳብ መልካም ቀን!

23/12/2024
ተመስገን! ላመስግንህ እንጂ ደጅህ ተሳልምጤንነት ሰጥተኸኝ ስለሄድኩኝ ቆሜ።ከፍዬ አልጨርሰው እኔ ያንተን ውለታፀጋህ አይጓደል ክበርልኝ ጌታ።
23/12/2024

ተመስገን!

ላመስግንህ እንጂ ደጅህ ተሳልም
ጤንነት ሰጥተኸኝ ስለሄድኩኝ ቆሜ።
ከፍዬ አልጨርሰው እኔ ያንተን ውለታ
ፀጋህ አይጓደል ክበርልኝ ጌታ።

ህንዳዊው ቢሊየነር ራታንጂ ታታ በሬዲዮ በስልክ ቃለመጠይቅ ላይ ተጠይቆ ሲቀርብ:ጋዜጠኛው በህይወትህ ደስታ ያገኘህበትን ጊዜ ትዝ ይልሃል?ራታንጂ ታታ እንዲህ አለ:በህይወት ውስጥ አራት የደስታ...
23/12/2024

ህንዳዊው ቢሊየነር ራታንጂ ታታ በሬዲዮ በስልክ ቃለመጠይቅ ላይ ተጠይቆ ሲቀርብ:
ጋዜጠኛው በህይወትህ ደስታ ያገኘህበትን ጊዜ ትዝ ይልሃል?
ራታንጂ ታታ እንዲህ አለ:
በህይወት ውስጥ አራት የደስታ ደረጃዎችን አልፌያለሁ፣ እናም በመጨረሻ የእውነተኛ ደስታ ትርጉም ገባኝ፦
የመጀመሪያው ሀብት ማካበት የጀመርኩበት ሲሆን
ነገር ግን በዚህ ደረጃ የምፈልገውን ደስታ አላገኘሁም።
ከዚያም ውድ የሆኑ እቃዎችን መሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ መጣ።
ነገር ግን የዚህ ነገር ጣጣው ጊዜያዊና ውድ ነገሮችም ብዙ እንደማይቆይ ተረዳሁ።
ከዚያም ትልቅ ፕሮጀክት የማግኘት ሶስተኛው ምዕራፍ መጣ። ያኔ ነበር 95% የሚሆነው የህንድ እና አፍሪካ ውስጥ የነዳጂ አቅርቦት የነበረኝ።
በህንድ እና በኤዥያ ትልቁ የብረት ፋብሪካ ባለቤትም ነበርኩ።
ነገር ግን እዚህም ቢሆን ያሰብኩትን ደስታ አላገኘሁም።
አራተኛው እርምጃ አንድ ጓደኛዬ ለተወሰኑ አካል ጉዳተኛ ልጆች ዊልቸር እንድገዛላቸው ሲጠይቀኝ ነበር።
200 የሚሆኑ ህፃናት
ከጓደኛየ ጋር ወዲያው ዊልቸሮቹን ገዛሁ፡፡
ጓደኛየ ግን አብሬው ሄጄ ዊልቸሩን ለልጆቹ እንዳስረክብ አሳመነኝና ተዘጋጅቼ አብሬው ሄድኩ።
ይኸው ለእነዚህ ልጆች ዊልቸሩን በገዛ እጄ ሰጥቻቸዋለሁ። በእነዚህ ህፃናት ፊት ላይ እንግዳ የሆነ የደስታ ፍንጭ አየሁ ሁሉም በዊልቸር ተቀምጠው ሲንቀሳቀሱ እና ሲዝናኑ አየኋቸው።
ሽርሽር ቦታ የደረሱ ይመስል ነበር የአሸናፊነት ስሜት የሚስተዋልባቸው።
እውነተኛ ደስታ ውስጤ ተሰማኝ።
ለመሄድ ስወስን አንዱ ልጅ እግሬን ያዘኝቀስ ብዬ እግሬን ለማስለቀቅ ሞከርኩ ልጁ ፊቴን አይቶ እግሬን አጥብቆ ያዘኝ። ተደግፌ ልጁን ጠየኩት? ሌላ ነገር ትፈልጋለህ?
ይህ ልጅ የሰጠኝ መልስ በጣም ያስደነገጠኝ ብቻ ሳይሆን ለህይወት ያለኝን አመለካከት ሙሉ ለሙሉ ቀይሮልኛል
ይህ ልጅ እንዲህ አለ፦
"ፊትህን ላስታውሰው በሰማይ ሳገኝህ እንዳውቅህ እንደገና እንዳመሰግንህ.....!! . . ምንም ነገር ትንሺናት ብለህ ከማድረግ አትቆጠብ። የመልካም ነገር ዋጋው ከሰጩ ይልቅ ለተቀባዩ ታላቅ ነውና።

" ሴት ልጅ ከዚህ ውጭ ምንም ጥቅም የላት" እያሉ እየተሳሳቁ ክፉ ነገርን ፈጸሙባት።አራተኛው ቀን ፍላጎታቸውን አርክተው እሷም ላይ ጉዳት አድርሰው ሲጨርሱ በወሰዱበት መንገድ መልሰው መንደሯ ...
02/12/2024

" ሴት ልጅ ከዚህ ውጭ ምንም ጥቅም የላት" እያሉ እየተሳሳቁ ክፉ ነገርን ፈጸሙባት።
አራተኛው ቀን ፍላጎታቸውን አርክተው እሷም ላይ ጉዳት አድርሰው ሲጨርሱ በወሰዱበት መንገድ መልሰው መንደሯ ላይ አምጥተው ጥለዋት ሄዱ። ከእሷ በቀር ማንም ሰው ስለሆነባት ነገር አያውቅም፤ ታለቅሳለች። አይደለም ሰው እንስሳ እንደዚህ አያደርግም ቢባልም ሆነባት። እንደ እንስሳ ከዚያም በላይ ዝቅ ብላ በደል ደረሰባት። ይሄ ደግሞ ከዚያ ቦታ ብትወጣ እንኳን አዕምሮዋ ላይ ይመላለሳል። ገላዋን ብትታጠብም፣ ሰዎች አጠገቧ ሆነው ቢያበረታቷትም፤ አይዞሽ እያሉ ቢያግዟትም የነውረኛ ሰዎች ነውር ላይዋ ላይ ነበር። ከሰውነቷ ለዘለዓለም ላይፋቅ እንደማይለቅ ንቅሳት ታትሟል።
***
" ድረሱልኝ እባካችሁ ድረሱልኝ!" ጮኸች ሰው ከረፈደ ደረሰ። ወደ ሆስፒታል ሳትወሰድ ያለም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች፤ አመለጠች። ሁሉንም የሆነባትን ነገር በልቧ እንደያዘች፤ ለማንም ሳታወያይ ነበር የሞተችው። ድንኳን ተዘረጋ እና ለሶስት ቀን ተለቀሰ።
***
" እማ እማ!" የያዝኩትን መኮረኒ መሬት ላይ ጣልሁት። ሮጬ ሄድኩ እናቴን አቅፌ ተጣራሁ። አልመለሰችልኝም፤ ወደ እህቴ ሄድሁ። እህቴም እንደዛው አትመልስም፤ ሁለቱም ሰውነታቸው በጥይት ተበሳስቷል። አባቴስ የት ሄዶ ነው?
***
" እንባዬ መጣ! ከዓይኔ እንዲወጣ አልፈለግኩም፤ ኮስተር አልኩ። ብርክክ ብዬ ወደ አፈሩ ቀረብኩ አፈሩን በእጄ እያሸሁ ቃል ገባሁ። ደግሜ ወደዚህ የምመለሰው ቤተሰቦቼን ያሳጣኝን ሰው ስበቀል ብቻ ነው። ካልተበቀልኩ ወደ እዚህ መጥቼ ከቤተሰቤ ቀብር ላይ የእነሱን አጽም አፈር ላላለብስ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ስም ለራሴ ቃል ገባሁ። ተቆጨሁ፣ አንገበገበኝ... የቱን ያህል ጊዜ ቢፈጅም አደርገዋለሁ።
***
" የሁሉን ሰው መከራ፣ ስደትና ስቃይ ፈጣሪ ይመለከታል። የሰራውን የሚያፈርስ ራሱ የፈጠረው ነው። "
***
" በክፉዎች አትቅና ዓመጻንም በሚያደርጉት ላይ አትቅና እንደ ሳር ፈጥነው ይደርቃሉና እንደለመለመ ቅጠል ይረግፋሉና"
" የክፋት ውርስ" ኔጌር
መልካም ሰኞ!

@ትዝታሽን
29/11/2024

@ትዝታሽን

አስተውል " ስማኝ ማነህ ተብለህ ስትጠየቅ እኔ ነኝ በማትልበት ቦታ አትገኝ። አስተውል መንገድ ሁሉ አይወስድም ቦታ ሁሉ አያኖርም… ከገዳዮች ጋር አትተባበር ነፍሰ ገዳይ የሚሄድበትን አያውቅም...
29/11/2024

አስተውል
" ስማኝ ማነህ ተብለህ ስትጠየቅ እኔ ነኝ በማትልበት ቦታ አትገኝ። አስተውል መንገድ ሁሉ አይወስድም ቦታ ሁሉ አያኖርም… ከገዳዮች ጋር አትተባበር ነፍሰ ገዳይ የሚሄድበትን አያውቅም የረከሰም ነው፡፡ ሰውን ገሎ ደማቸውን ጠጥቶ አይረካም ስጋቸውን በልቶ ሰላም የለውም፡፡ በቀልና ቂምን ለነገ ይተዋል … የተበደሉ ሰዎች መጮህ ባትችልም ከገዳይ ጋር አትተባበር፡፡ ዛሬ የራቀ የመሰለህ ነገ ደጃፍህ ይደርሳል፡፡ ዛሬ የምትሞቀው እሳት ካላጠፋኸው ነገ ያቃጥልሀል፡፡ዛሬ የዘራኸው መጽፎ ተግባር ነገ ለአንተና ልጆችህ ነውና አስተውል።"
"የክፋት ውርስ" (ኔጌር)
ሁለተኛ ዕትም
ጃዕፈር መጽሐፍ መደበር !

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የፍቅር ነገር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share