03/06/2025
ድንቅ የቁርዓን ሳይንሳዊ ❲Scientific❳ ተዓምር።
በሥነ-አየር 'meteorology' ጥናት ውስጥ ሳይንቲስቶች በቅርቡ የደረሱበት አንድ እውነታ አለ። እርሱም በሰማይ ያሉ ደመናዎች እንደሚታዩት ክብደት ያሌላቸው ቀላል፣ ተንሳፋፊ ኃይል አልባ፣ ወይም እንደ ጥጥ ልፍስፍስ ሳይሆኑ እጅግ ከባድ መጠን ❲Weight❳ የሚመዝኑ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በዚህም መሰረት በ1km³ ውስጥ የሚገኝ ደመና '500 ቶን' ወይም 500,000 Kg ያኽል እንደሚከብድ ገልጸዋል። ግን ሲታዩ ንፋስ እንጂ 1kg እንኳ የሚመዝኑ አይመስሉም አይደል ? 'አዎ' ማንም እንደዛ ነው የሚገምተው። እስኪ ሳይንቲስቶቹ ያሉትን እንመልከት:-
[፨] የአሜሪካው የሥነ-አየር ምርምር ማዕከል።
«A 1 km³ cloud with 0.5 g/m³ of water contains 500,000 kg of water. ይህ ክብደት 1.1 ሚልዮን ፓውንድ ነው።»
(🌐ምንጭ:- U.S. Geological Survey How Much Does a Cloud Weigh July 7, 2019. «እዚህ ጋር» በመጫን ያንብቡ።
[፨] 'Clouds look light and fluffy, but they're surprisingly heavy. When you're flying in an airplane above a blanket of clouds, the pillars of white and gray look soft, fluffy and lighter than air. But don't be fooled, those bouncy-looking clouds are much, much heavier than they appear.
(🌐ምንጭ:- https://www.livescience.com/how-much-does-a-cloud-weigh)
[፨] Now that we determined that clear air has weight,....we discover that our cumulus cloud contains 500,000 kilograms, or 1.1 million pounds, of water droplets. That's the equivalent weight of five adult blue whales, the largest animal on the planet.
(🌐ምንጭ:- https://weatherworksinc.com/news/how-much-does-a-cloud-weigh
እንግዲህ ይህ በ21ኛው ክፍለዘመን የሥነ-አየር ሊቃውንት 'Meteorologist' ሚልዮን ዶለር የወጣባቸውን ሳታላይቶች፣ ራዳር፣ ክራፍት ድሮኖች፣ ሲሎሜትር እና ራዲዮ-ሜትር የመሳሰሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ያገኙት አዲስ ግኝት ነው። ከዚህ ቀደም መሰል የሥነ-አየር ጥናት ምርምር ባለመኖሩ ይህን እውነታ ማወቅ ለሰው ልጆች በፍጹም የማይታሰብ ነበር። በተለይ ደግሞ ይህ ነጭ ደመና በሚልዮን ኪ.ግ. የሚቆጠር ክብደት አለው ብሎ መገመት ዘበት ነው።
ታድያስ ቁርኣን ከዚህ ጋር ምን ያገናኘዋል ? እያላችሁኝ እንደሆነ አስባለሁ። አዎ ! ይህንን ድንቅ ሳይንሳዊ እውነታ ጌታ አምላክ አስቀድሞ በዚያ ያልተማረ ማህበረሰብ ውስጥ፣ በሐሩር በረሃ ለሚኖር አንድ ማንበብም ሆነ መጻፍ የማይችል ነቢይ በማስነሳት ዛሬ ሊቃውንቶች በተራቀቁ ማሺኖች ያገኙትን አዲስ ግኝት ቀድሞ ነግሮናል።
هُوَ الَّذِي يُرِيكُمُ الْبَرْقَ خَوْفًا وَطَمَعًا وَيُنشِئُ السَّحَابَ الثِّقَالَ
እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ «ከባዶች ደመናዎችንም» (Heavy clouds) የሚያስገኝ ነው፡፡ ❲ቁርኣን 13፥12❳
وَهُوَ الَّذِي يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَقَلَّتْ سَحَابًا ثِقَالًا سُقْنَاهُ لِبَلَدٍ مَّيِّتٍ فَأَنزَلْنَا بِهِ الْمَاءَ فَأَخْرَجْنَا بِهِ مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۚ
እርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው፡፡ «ከባዳዎችንም ደመናዎች» በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ኾነ አገር እንነዳዋለን፡፡ ❲ቁርኣን 7፥57❳
ሱብኃን-አላህ ! ይህ ዘመናዊው ሳይንስ ከመምጣቱ 1400 ዓመታት በፊት የተነገረ ድንቅ ተዓምር ነው። ደመና ከባድ ❲Heavy❳ መሆኑን በዚህ ደረጃ ከቁርኣን አስቀድሞ የተናገረ አንድም ስንኳ የለም። እንዲህ ያለ የአጽናፈ ዓለሙን ምስጢር ከአምላክ በስተቀርስ ማን ሊያውቀው ይችላል ? በተለይ ደግሞ በዚያ ጥንት ዘመን።
**
By:- ☑️Sαlαh Responds