Endrias film prodaction

30/01/2023

Ethiopian new cover muzic bast song popelar 2023 ኢቢኤስ ቲቪ ቴዲ አፍሮ ቪንቸር ፋና ቲቪ ናሆም ሪከርድ ምነው ሸዋ ሆፕ ኢንተርተይመት

29/01/2023

አልበርት አንስታይን

ራስን መለወጥ

t.me/changeitwow
www.youtube.com/

29/01/2023

ምክረ-አዕምሮ ~ ሥራህን ስራ!

| አወጣህ አወረድክ፣ ታመምክ ተሰቃየህ፣ በላህ አልበላህ፣ አየህ አላየህ፣ አሳካህ አላሳካህ፣ ደረስክ አልደረስክ ማንም ሰው አይመለከተውም። ሃሳብህ፣ ህልምህ ራዕይህ ያንተ ነው።

የጠለቀ ግንኙነት ቢኖርህም አንድ ቀን ትረሳለህ፣ ለረጅም ጊዜ ብትለፋም ውጤት ታጣለህ፣ ከአቅምህ በላይ ብትታገልም ያሰብከውን አታገኝም። የሚለፉ፣ የሚደክሙ፣ የሚታትሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፣ ስኬታማና ደስተኞች ግን እጅግ ጥቂት ናቸው።

ስለመዳረሻህና ወደፊት ስለምታሳካው ግብህ እያሰብክ ደስታና ስኬትን ልታገኝ አትችልም። ምንም ትልቅ ነገር ልታደርግ ትችላለህ፣ ህልምህን ልታሳካ፣ ግብህንም ልትመታ ትችላለህ፡፡ የትኛውም መዳረሻ ግን የእራሱ መንገድ አለው፤ እርከን አለው፤ ሂደት አለው። ገና ለገና ከሰማይ የምታወርደው ስኬትና ደስታ ያለ ይመስል እርሱን በመጠበቅ ጊዜህን አትፍጅ። እርሱ መምጣት ካለበት የሚመጣው ስለጠበከው ሳይሆን ሆነኸው ስለተገኘህ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ሥራህን ሥራ፤ የፈለከው ነገር በጊዜው እራሱ ይሰራል፣ ይመጣል። ያሰብከውን ነገር አድርግ፤ የታሰርክበትን ሰንሰለት በጥስ፤ ጥቃቅኗን ነገር በጥልቀት አድርጋት፣ በእርምጃህ ውስጥ ስሜትን ፍጠር። ስኬትን መመኘት ሳይሆን ሆነኸው ተንቀሳቀስ፣ ደስታን መናፈቅ ሳይሆን ፈጥረኸው ኑርበት። በተዓምራት የሚከሰት ትልቅነት እንደሌለ ታውቃለህ፣ በአንዴ የሚፈጠር ስኬት እንደማይኖርም ይገባሃል። ውስጥህ ያልፈጠርከው ነገር ኬትም እንደማይመጣ አስተውል፤ ማረፊያ ያላዘጋጀህለት፣ አምነህ ያልጀመርከው፣ ጣሪያ ያላበጀህለት፣ ተንትነህ በግልፅ ያላስቀመጥከው ስኬትም ሆነ ከፍታ በፍፁም ሊመጣ አይችልም።

ምናልባት ያላሰብከው የመሰለህ ነገር በህይወትህ ተከስቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሳታስበውና በውስጥህ ምንም ነገር ሳይኖር በህይወትህ የሚከሰት አንዳች ነገር አይኖርም። ሃሳብ ያደክማልና አንድ ሰሞን አስበህ ትተኸው ይሆናል፣ በሌላ ሃሳብም ተክተኸው ይሆናል። አንተ ብትረሳውም ሰውነትህ ግን አይረሳውም፤ ያኔ በሃሳብህ ውስጥ ሰውነትህ የተሰማው ስሜት በሂደት ባልገመትከው መንገድ ወደ ቀድሞ ሃሳብህ እውንነት መርቶሃል።

አዎ! አስበህ፣ አምነህ፣ ተቀብለህ በህይወትህ ውስጥ እውን እንዲሆን የምታደርገው ነገር ይኖራል። አንድን እሳቤ አስተውል፣ " የምትፈልገውና የሚያስፈልግህ ነገር እንዲከብህ ማድረግ ሊከብድህ ይችላል፤ ነገር ግን የሚያስፈልግህንና የምትፈልገውን ነገር በውስጥህ መፍጠር ትችላለህ።" ቀላልና ከባድ፣ አዝናኝና አሳዛኝ፣ አሳራፊና አድካሚ የሚባሉ የህይውት አጋጣሚዎች ይኖራሉ። ምንም ይሁኑ ግን የህይወትህ አንድ አካል ናቸው። ተቀብለህ የማስተናገድ ግዴታ አለብህ። ስሜቱን ባትፈልገውም ከባድ፣ አሳዛኝና አድካሚ የሆኑትን ክስተቶችም ማጣጣም ይኖርብሃል። ከባዱን ካልተሻገርክ ቀላሉን አታገኝም፤ አሳዛኙን ካላሸነፍክ አስደሳቹ ጋ አትደርስም፤ አድካሚውን ካልተወጣህ ዕረፍትህን አታጣጥምም።

በእያንዳንዱ እርምጃህ ውስጥ ነፍስን ፍጠር፣ ስሜት አግኝ። ሰርተህ ስትጨርስ፣ ሃላፊነትህን ከተወጣህ በኋላ ሳይሆን እየሰራህ፣ ሃላፊነትህንም እየተወጣህ ደስተኛና ስኬታማ እንደሆንክ አምነህ ተንቀሳቀስ።

“Once you have commitment, you need the discipline and hard work to get you there.”
Haile Gebrselassie

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

16/01/2023

Watch, follow, and discover more trending content.

Address

70 Derja
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Endrias film prodaction posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Endrias film prodaction:

Share