Tesfa

Tesfa የሰው ልጆችን በእውነተኛ ተስፋቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለመርዳት የተከፈተ ገፅ ነው

እግዚአብሔር ፊት ያቀረብከውን ልመና መልሱን ለረጅም ጊዜ እየጠበቅህ ሊሆን ይችላል። ጸሎትህ የዘገየ ሊመስልህ፣ ሁኔታህም እንደማይለወጥ ሊሰማህ ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር ጩኸትህን ይሰማ...
06/10/2026

እግዚአብሔር ፊት ያቀረብከውን ልመና መልሱን ለረጅም ጊዜ እየጠበቅህ ሊሆን ይችላል። ጸሎትህ የዘገየ ሊመስልህ፣ ሁኔታህም እንደማይለወጥ ሊሰማህ ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር ጩኸትህን ይሰማል። እርሱ ወደ አንተ ያዘነብላል፤ ከጥፋት ጉድጓድና ከረግረግ ጭቃ ያወጣሃል፣ እግሮችህንም በጽኑ ዓለት ላይ ያቆማል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ጠብቅ። በጊዜው ያወጣሃል፣ አረማመድህንም ያጸናል።

መዝሙር 40:1-2 ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።

በህይወት ጉዞ የሚጠብቅህን ሁሉ አስቀድመህ ማወቅ አትችልም። የሰው ማስተዋል ውስን ነው፤ አንተ የዛሬን ብቻ ታያለህ፣ እግዚአብሔር ግን ረጅሙን የሕይወትህን ጉዞ በሙሉ ያያል።ስለዚህ ይህን ሳም...
05/10/2026

በህይወት ጉዞ የሚጠብቅህን ሁሉ አስቀድመህ ማወቅ አትችልም። የሰው ማስተዋል ውስን ነው፤ አንተ የዛሬን ብቻ ታያለህ፣ እግዚአብሔር ግን ረጅሙን የሕይወትህን ጉዞ በሙሉ ያያል።
ስለዚህ ይህን ሳምንት ስትጀምር በራስህ ጥበብ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ተደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን ፈልግ፤ እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል።

ምሳሌ 3:5-6በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።

ዓለም ሰው የሚፈልገውን ለማግኘት ማታለልን፣ ተንኮልንና ራስ ወዳድነትን እንደ ጥበብ በምትቆጥርበት ጊዜ፣ በእውነትና በቅንነት መኖር እንደ አለመሳካት ሊታይ  ይችላል: አንዳንዶች በማይታወቅ መ...
01/10/2026

ዓለም ሰው የሚፈልገውን ለማግኘት ማታለልን፣ ተንኮልንና ራስ ወዳድነትን እንደ ጥበብ በምትቆጥርበት ጊዜ፣ በእውነትና በቅንነት መኖር እንደ አለመሳካት ሊታይ ይችላል: አንዳንዶች በማይታወቅ መንገድ ብዙ ነገር ሲያገኙ ታያለህ።ነገር ግን የሰው ስኬት የእግዚአብሔር ልኬት አይደለም። እርሱ የልብን እውነት ያያል። በቅንነት መኖርህ በሰዎች ዘንድ ምንም ዋጋ ባይሰጠውም፣ በእግዚአብሔር ፊት ግን ውድ ነው።አንተ በቅንነት ስትመላለስ ሁሉን ነገር በፍጥነት ላይሆንልህ ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ከመልካም ነገር አያሳጣህም!። ሰው ባያይህም እግዚአብሔር ያይሃል፤ ዋጋህንም ያውቃል። ስለዚህ ቅንነትህን አትተው። በእግዚአብሔር ፊት በእውነት መመላለስን ምረጥ፤ እርሱም ከመልካም ነገር ሁሉ አያጎልህም።

መዝሙር 84:11 እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን፡ ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።

በሕይወትህ የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሲበዙ የገንዘብ፣ የጤና፣ የቤተሰብ ወይም ሌላ ጉዳይ ብቻህን አትሸከም። እያንዳንዱን ጭንቀት ወደ ጸሎት አምጣ፤ ፍርሃትህን፣ ልመናህንና የልብህን ሁሉ ለእግዚአ...
30/09/2026

በሕይወትህ የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሲበዙ የገንዘብ፣ የጤና፣ የቤተሰብ ወይም ሌላ ጉዳይ ብቻህን አትሸከም። እያንዳንዱን ጭንቀት ወደ ጸሎት አምጣ፤ ፍርሃትህን፣ ልመናህንና የልብህን ሁሉ ለእግዚአብሔር ንገረው።
የትናንት ታማኝነቱ ዛሬም አልተለወጠም። ጌታ ቅርብ ነው፤ ስለዚህ ጭንቀትህን ለእርሱ ስጥና በሰላሙ እረፍ።

ፊልጵስዩስ 4:6 ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።

አምላክ መድኃኒትህ ነው። የኃጢአትን ቁስል በራስህ ጥረት ልትፈውሰው አትችልም፤ ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶሃል። መዳንህ በራስህ ጥረት የተገኘ...
29/09/2026

አምላክ መድኃኒትህ ነው። የኃጢአትን ቁስል በራስህ ጥረት ልትፈውሰው አትችልም፤ ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶሃል። መዳንህ በራስህ ጥረት የተገኘ ሳይሆን፣ በክርስቶስ ጸጋ የተሰጠህ ስጦታ ነው።
እርሱ ኃይልህም ነው። በራስህ ኃይል ሁሉን መሸከም አትችልም። ድካም ሲመጣ፣ ፈተና ሲበዛ፣ ተስፋ ማድረግ እንኳን ከባድ ሲሆን፣ እርሱ የሚያበረታህ ኃይል ይሆናል።
እርሱ ዝማሬህም ነው። በሐዘን መካከል፣ በለቅሶ ውስጥ፣ መልሱን ሳታውቅ እንኳን እርሱ ታማኝ እንደሆነ በማመን ማመስገን ነው።

ስለዚህ ችግር ቢኖርም፣ ከችግርህ የሚበልጥ አምላክ እንዳለህ እወቅ። ሕይወት ስትከብድ እርሱ መድኃኒትህ ነው፤ ስትደክም ኃይልህ ነው፤ ስታዝን ዝማሬህ ነው።

ዛሬ የሚያስፈራህ ነገር ቢኖር፣ በችግሩ ላይ ብቻ አትመልከት፤ ወደ ኢየሱስ ተመልከት። እርሱ ከኃጢአት ሊያድንህ፣ ከባርነት ነፃ ሊያወጣህ፣ በድካምህ ኃይል ሊሆንህ እና በሐዘንህ መካከል ዝማሬህ ሊሆንህ ይችላል።

አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። - ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1

ዓለም ብዙ መንገዶችን ብታሳይህም፣ እውነተኛ የሕይወት መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው። እርሱ  በእውነት በመንገድ ላይ ይመራሃል። ከእርሱ ጋር ያለ የሕይወት መንገድ እውነተኛ ደስታን ይ...
28/09/2026

ዓለም ብዙ መንገዶችን ብታሳይህም፣ እውነተኛ የሕይወት መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው። እርሱ በእውነት በመንገድ ላይ ይመራሃል። ከእርሱ ጋር ያለ የሕይወት መንገድ እውነተኛ ደስታን ይሰጥሀል፤ ከፊቱ ደስታ፣ በቀኙም የዘላለም ፍሥሐ አለ። የዚህ ዓለም ደስታ የሚጠፋ ነው፤ በእግዚአብሔር ያለው ደስታ ግን ዘላለማዊ ነው።

ዛሬ በሳምንቱ መጀመሪያ መንገድህን ለእርሱ አስረክብ፤ እርሱ ወደ እውነተኛ ሕይወት ይመራሀል፤ ደስታም ያጠግብሀል።

የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። - መዝሙር 16:11

በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️ የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካ...
11/09/2026

በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️

የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካርዱን ለማዘጋጅት እና ለመላክ ይህን ቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://t.me/tesfa_postcard_bot

በሁለት የቋንቋ አማራጭ ያገኛሉ (አማርኛ እና afaan oromo)

Postcard
Follow tesfa on Telegram (https://t.me/tesfa_gcme)

እንኳን ለ2019 በሰላም አደረሳችሁ! ኢየሱስ፣ የማይጠፋ ተስፋ! በሕይወትህ ምንም ቢለወጥ፣ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑ፣ተስፋህ አለ።ምክንያቱም ተስፋህ በምታየው ነገር ላይ አይደለም፤ ተስፋህ ኢየሱስ...
11/09/2026

እንኳን ለ2019 በሰላም አደረሳችሁ!

ኢየሱስ፣ የማይጠፋ ተስፋ!
በሕይወትህ ምንም ቢለወጥ፣
ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑ፣
ተስፋህ አለ።
ምክንያቱም ተስፋህ በምታየው ነገር ላይ አይደለም፤
ተስፋህ ኢየሱስ ነው።
እርሱ ሞትን አሸንፎ ተነስቷል።
እርሱ ሕያው ነው፤
እርሱ ከአንተ ጋር ነው፤
እርሱም የማይጠፋ ተስፋህ ነው።
አንድ ቀን የምንጠብቀው ተስፋ ይፈጸማል።
ኢየሱስ ይመጣል!

1 ጴጥሮስ 1:3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

11/09/2026

መልካም አዲአ አመት!

በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም አይጠፋምና።
ምሳሌ 23:18

በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️ የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካ...
10/09/2026

በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️

የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካርዱን ለማዘጋጅት እና ለመላክ ይህን ቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://t.me/tesfa_postcard_bot

በሁለት የቋንቋ አማራጭ ያገኛሉ (አማርኛ እና afaan oromo)

Postcard
Follow tesfa on Telegram

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912251111

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tesfa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Tesfa:

Shortcuts

Share

Category