CALM media and communication

CALM  media and communication provides quality services in the field of media and communication through the production of audio-visual and designing and printing communication materials

10/04/2020
The right time to be....
20/06/2019

The right time to be....

27/02/2019

provides quality services in the field of media and communication through the production of audio-visual and designing and printing communication materials

02/07/2018
Arbaminch & Gonder
09/04/2018

Arbaminch & Gonder

የኪነጥበብ ( ፊልም ፣ትያትር፣ስነፅሁፍ፣ሙዚቃ ፣ስነስዕል እና ሌሎች  ስራዎች በአንድ ሀገር ኢኮኖማዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ (ዕድገት)ለይ ከፍ ያለ ሚና አላቸው፡፡እንዚህ የኪነጥ...
09/12/2017

የኪነጥበብ ( ፊልም ፣ትያትር፣ስነፅሁፍ፣ሙዚቃ ፣ስነስዕል እና ሌሎች ስራዎች በአንድ ሀገር ኢኮኖማዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ (ዕድገት)ለይ ከፍ ያለ ሚና አላቸው፡፡እንዚህ የኪነጥበብ ስራዎች በኢኮኖሚ ለይ ከሚያመጡት ለውጦች በተሸለ በአንድ ሀገር ማህበራዊ እና ፖለቲካ ለውጥ ለይ ሊሰጡጥ የሚችሉት ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡ይህንን ሚናቸውን በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ደግሞ በዘርፉ እና ሌሎች የትምህር ዘርፎች እና የካበተ የንባብ እና የስራ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች መኖር ፣ከፍ ያለ ስነውበታዊ ደራጃን እና የኪነጥናብን ስራ ሚና የሚረዳ ማህበረሰብ( ህግ /ፖሊሲ/ አርቃቂ፣ተርጓሚዎች እና አስፈፃሚዎች ከዚህ ማህበረሰብ መውጣታቸውን ልብ ይሏል) እና ዘርፉን ሊያንቀሳቅስ የሚችል የጎለበተ ኢኮኒሚ መኖር አስፈላጊዎች ናቸው፡፡
በሀገራችን ባህላዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካ እንቅቃሴ ለይ የሀገራችን የኪነጥበብ ስራዎች ሚና ምን ይመስላል፣ምን ደረጃ ለይ ነው፣ የትኞቹ ስራዎች አስተዋፅኦ አድረገዋል የሚለውን ጥያቄ መልሱን በድፍረት ለመናገር ሁሉም የኪነጥብ ስራዎችን መሰረት አድርጎ የተሰራ ጥልቅ ምርምር ያስፍጋል፣
ይሁንና ለኪነጥበብ ስራዎች መዳበር እና እድገት ምቹ ሜዳ በሌለበት የተሰሩ ፋይዳ ያላቸው ስራዎች በውፍ በረር እይታ እና ተመርተው ለእይታ፣ ንባብ እና መደመጥ በቅተው በተደራሲያን ስምምነት የተደረሰባቸው የኪነጥብብ ስራዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከነዚህ ዘመን ተሸጋሪ ፣የላቀ ኪነ-ጥበባበዊ ስነ ውበት፣ ከፍ ያለ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሀሳብ፣ እና ፍልስፍና ካላቸው ስራዎች፣ የአዲስ አለማየሁ ፍቅር እስቀመቃብ፣የበዐሉ ግርማ ኦሮማይ፣ የሎሬት ፀጋዩ ገ/መድህን ውብ ታሪካዊ ባህላዊ እና ፖለቲካ አዘል ግጥሞች፣እና ትያትሮች፣ የዳኛቸው፣አደፍረሰ፣የገብረክርሰሰቶስ፣ ደበበ ሰይፉ፣አብዩ መንግስቱ ለማ እና የሌሎች የግጥም እና ትይትር ስራዎች፣የእስክንድር ቦጎሲያሰ፣ገብረክርስቶስ እና የሎሬት አፍወርቅ ተክሌ ድንበር ዘለል እና አለምአቀፋዊ ስዕሎች እና የዘመናዊ ሙዚቃ መነሻ ተብሎ ከሚታመኑበት ዘመን ጀምሮ(በፎክ አርት ውስጥ ከሚገኘው በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የሚዜሙ ባህላዊ ዘፈኖች እንዳሉ ሆነው) በተለያዩ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሰናዱ ሙዚቃዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በሀገራችን ከነዚህ የረጅም ዘመን እድሜ ካላቸው የኪነጥበብ አይቶች እና ስራዎች በተጨማሪ የፊልም ፣ቴሌቭዥን፣እና ሌሎች (የስክሪን ፕለይ) ስራዎችም በሌሎች አለም የደረሱበት ደረጃ ልክ ባይሆኑም በመሰናዳት ለይ ይገኛሉ፡፡በእነዚህ የጥበብ ስራዎች ክፍ ባለ ጥራት ለማሰናዳት የሚያስችሉት ግብዐቶች በሌሉበት ፣ለሙያው ከፍተኛ ፍቅር ባላቸው፣ራሳቸውን በሚያስተምሩ እና ችግሮችን በራሳቸው መንገድ በምፍታት ከላይ በተጠቀሰው ባለድርሻዎች ልክ በመሰራት ዘርፉ በሀገር ኢኮሚ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለይ ሊሰጥ የሚገባውን አስተዋፅኦ በማበርከት ለይ ይገኛሉ፡፡
አሁን አሁን በነዙህ በሀገራች ውስጥ ተሰናድተው በሚወጡ የኪነጥበብ ስራ ውጤቶች ጥራት እና ደረጃ ለይ ከሊቁ እስከ ደቂቁ በሚባልበት ደረጃ መስፈሪያ በሌለው ሙገሳ እና እርግማን የሚወርድበት ዘርፍ ሆኗል፡፡ባለሙያዎቹም የበዐላት እና ፕሮፓጋንዳ መናጆ በመሆን የሚሰጣቸውን ሙገሳ በሙሉ የሚደርስባቸውን ወቀሳ በዝምታ በማለፍ ፣ባለድርሻዎቹን ሲያገኙ ከፈረሱ ጋሪውን አስቀድመው (ከትምህርት ቤት ካሜራ እና መኪና ነፃ ቀረጥ፣ አግባበው ያልሆነውን ቀረጥ ከማስረቀረት የማህበራቸው የሚሆን ነፃ ቢሮ፣እና ነፃ ህክምና ) በመጠየቅ ራሳቸውንም ሆነ ሙያውን ሰድቦ ለሰዳቢ በመስጠጥ ለይ ይገኛሉ፡፡
በትኘውም የሙያ ዘርፍ ጥራት እና ፋይዳ ያላቸው ስራዎች ለማምረት ሶስት ነገሮች ማሳ ለማሳ ማደግ አለባቸው ተብሎ ይታመናል፡፡
ትምህርት፣ ግንዛቤ(የሙያው ምንነት እና ጥቅም) እና ኢኮኖሚ፣
በሀገራችን የኪነጥበብ ሙያዎች ለይ እነዚህ ሶስት የጥራት መሰረቶች ምን ደረጃ ለይ ናቸው ?
?
?
ስክሪፕቶ፣አፍ እና መጠንቆያ ጣቶች ስላለን ብቻ ከምንም ነገር የሆነ ነገር እየፈጠሩ ያሉ ባለሙያዎች ያለመስፈሪያ በደስ አለኝ እና መሰለኝ በደፈናው የምትኮንኑ ፀሀፊዎች፣ከትችቱ በፊት ባለሙያዎቹ የሚሰሩበትን ሜዳ፣ዘርፉ የተሸለ ምርት እንዲያመርት የሚያስፈልጉ ግብዐቶች መኖራቸውን እና መስፈሪያ መሰረት በማድረግ መተቸት ብትችሉ፣ የበአል ማድመቂያ እና የሌሎች ዝግጅቶች ማድመቂያ በመሆን ሙያውን ለሰዳቢ የምትሰጡ ״አንዳንድ״ ባለሙያዎች፣ስራዩ ״በአፍሪካ״ አንደኛ ״በአለም״ ሶስተኛ ነው የሚለውን በመተው፣ከምንም ነገር የሖነ ነገር እየሰራችሁ እንደሆነ እና ፣ትምህርት፣ግንዛቤ እና የገንዘብ አቅም ቢኖረን የተሸለና ፋይዳ ያላቸው ስራዎች መስራት መቻሉን በመናገር ሙያውን አቅም፣ችሎታ እና ፋይዳ እንዳለው ለማሳየት ብትሞክሩ፣ያኔ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ስራዎች መስራት ይቻላል፡፡ ያኔ ረብ ያላቸው ስራዎች ይመረታሉ፣ያኔ ……………………………………------------------------ ……………

…………………………………………..
ልክ እንደነዚህ
ሀራ አብዲ

While most movies are mass-produced entertainment and escapism, there are some that have had a profound impact on culture. Whether intentionally or not, so

Address

Bole Road
Addis Ababa
185338

Telephone

+251911109405

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CALM media and communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share