Isehacbaba

Isehacbaba የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን! የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን! ፈታ ዘና እያልን፣ እየተዋወስን ላይፋችንን እንቅጭ አቦ!

የስራ ፖስት ስለሆነ በላይክ ጀምሩ👐😍ቡልጋሪያ፦ መኖሪያ እና ሱቅ?​የ30% ታላቅ የዋጋ ቅናሽ!​ቴምር ፕሮፐርቲስ (Temer Properties) በከተማዋ እምብርት በሆነው ቡልጋሪያ፣ ዘመናዊ መ...
19/05/2026

የስራ ፖስት ስለሆነ በላይክ ጀምሩ👐😍

ቡልጋሪያ፦ መኖሪያ እና ሱቅ?
​የ30% ታላቅ የዋጋ ቅናሽ!

​ቴምር ፕሮፐርቲስ (Temer Properties) በከተማዋ እምብርት በሆነው ቡልጋሪያ፣ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና ለንግድዎ ስኬት የሚሆኑ ሱቆችን በልዩ ቅናሽ ይዞላችሁ ቀርቧል።

​ ለላቀ ምቾት - የመኖሪያ አማራጮች (ከ7ኛ ፎቅ ጀምሮ)
​በአዲስ አበባ ውብ እይታ እየተደሰቱ የሚኖሩባቸው ሰፊ ቤቶች፦
​ባለ 1 መኝታ፦ ከ 60 ካሬ ሜትር ጀምሮ
​ባለ 2 መኝታ፦ ከ 95 ካሬ ሜትር ጀምሮ
​ባለ 3 መኝታ፦ ከ 125 ካሬ ሜትር ጀምሮ
​🛍️ ለንግድዎ ስኬት - ዘመናዊ ሱቆች
​ከ 1ኛ - 5ኛ ፎቅ የሚገኙ፣ ለትራንስፖርት ምቹ እና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ባለበት ስፍራ ላይ ያረፉ ሰፊ ሱቆች ለሽያጭ ቀርበዋል።

​ የዋጋ ዝርዝር እና የክፍያ አማራጮች
​ከ7ኛ - 10ኛ ፎቅ፦ በካሬ ሜትር 120,000 ETB
​ከ11ኛ - 13ኛ ፎቅ፦ በካሬ ሜትር 115,000 ETB
​የቅድመ ክፍያ፦ 20% ብቻ!
​ልዩ ስጦታ፦ 100% ሙሉ ክፍያ ለሚከፍሉ ደንበኞች የ30% ታላቅ ቅናሽ እናደርጋለን!

​የህንፃው ልዩ ገፅታዎች
​6ኛ ፎቅ፦ ለነዋሪዎች የጋራ መዝናኛ እና መገልገያ (Communal Space) ተብሎ የተለየ።
​አካባቢው፦ በቡልጋሪያ ዋና መንገድ ላይ የሚገኝና ለትራንስፖርት እጅግ ምቹ።
​እይታ፦ አዲስ አበባን ቁልቁል የሚመለከቱበት ማራኪ ቪው።

​📍 አድራሻ፦ ቡልጋሪያ (Bulgaria)
📞 አሁኑኑ ይደውሉና የቤት ባለቤት ይሁኑ፦ 0905931111

​ #የቤትሽያጭ #ቡልጋሪያ #ተመርሪልስቴት #አዲስአበባ

የዙልሂጃ ወርቃማ ቀናት" ​የአመቱ ምርጥ እና እጅግ የተባረኩት 10 ቀናት ዛሬ ጀምረዋል። እነዚህ ቀናት ዝም ብለው የሚያልፉ ተራ ቀናት አይደሉም፤ አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን ላይ የማለባቸው፣ ...
18/05/2026

የዙልሂጃ ወርቃማ ቀናት"

​የአመቱ ምርጥ እና እጅግ የተባረኩት 10 ቀናት ዛሬ ጀምረዋል። እነዚህ ቀናት ዝም ብለው የሚያልፉ ተራ ቀናት አይደሉም፤ አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን ላይ የማለባቸው፣ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ደግሞ "መልካም ስራ አላህ ዘንድ ይበልጥ የሚወደድባቸው ቀናት የሉም" ያሏቸው የወርቅ ዕድሎቻችን ናቸው።

​በእነዚህ ቀናት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን መልካም ስራዎች ፈጠን ብለን እንቀላቀል፡

​ምላሳችንን በዚክር እናድምቅ፡ ተክቢራ (አላሁ አክበር)፣ ተህሊል (ላ ኢላሃ ኢልለላህ) እና ተህሚድ (አልሃምዱሊላህ) ማብዛት።

​ጾም፡ በተለይ የመጀመሪያዎቹን 9 ቀናት (በተለይም የአረፋን ቀን) መጾም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል።

​ሰደቃና ዱዓ፡ የምንችለውን ያህል መለገስና ወደ ፈጣሪያችን እጃችንን መዘርጋት።

​ዱንያ በስራና በጭንቀት ልባችንን አድርቃው ከሆነ፣ ልባችንን የምናለመልምበትና ወደ አላህ የምንመለስበት ትክክለኛው ወቅት አሁን ነው።

​አላህ ስራዎቻችንን ይቀበለን፣ በእነዚህ ቀናት ከሚጠቀሙትም ያድርገን። 🤲 ያወቁትን ማሳወቅ መልካም ነውና ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩት።

​ #ዙልሂጃ #አስሩቀናት

ኮሜንት ላይ አሳዉቁን 🥰   #ጁምዓ
15/05/2026

ኮሜንት ላይ አሳዉቁን 🥰

#ጁምዓ

ኸሚስ 💚ጨለማን ለማባረር መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ የልብን ጨለማ ለማስወገድም በነቢዩ ላይ የሚወርድ ሰለዋት ያስፈልጋልሰሉ ዐለል ሀቢብ 🥰​         #ትዝብት  #ፈገግታ
14/05/2026

ኸሚስ 💚

ጨለማን ለማባረር መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ የልብን ጨለማ ለማስወገድም በነቢዩ ላይ የሚወርድ ሰለዋት ያስፈልጋል

ሰሉ ዐለል ሀቢብ 🥰

​ #ትዝብት #ፈገግታ

"ነገሮች እንዲቀየሩ ከፈለግህ፣መጀመሪያ የአንተን አመለካከት ቀይር።አንተ ስትቀየር ዓለም አብራህ ትቀየራለች።"ዓሊ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ)​         #ትዝብት  #ፈገግታ
14/05/2026

"ነገሮች እንዲቀየሩ ከፈለግህ፣
መጀመሪያ የአንተን አመለካከት ቀይር።
አንተ ስትቀየር ዓለም አብራህ ትቀየራለች።"
ዓሊ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ)

​ #ትዝብት #ፈገግታ

የኢማም አሕመድ ቢን ሐንበልና የዳቦ ጋጋሪው ታሪክ​ታዋቂው የሐዲስ ሊቅ ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበል እድሜያቸው በገፋ ጊዜ አንድ ወቅት ወደ አንዲት ከተማ ለጉዞ ይሄዳሉ። በከተማዋ ማንም የሚያው...
12/05/2026

የኢማም አሕመድ ቢን ሐንበልና የዳቦ ጋጋሪው ታሪክ

​ታዋቂው የሐዲስ ሊቅ ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበል እድሜያቸው በገፋ ጊዜ አንድ ወቅት ወደ አንዲት ከተማ ለጉዞ ይሄዳሉ። በከተማዋ ማንም የሚያውቃቸው ሰው አልነበረም። ሶላተል ኢሻን መስጂድ ውስጥ ሰግደው ሲጨርሱ፣ በዚያው ለመኝታ ማረፍ ፈለጉ። ሆኖም የመስጂዱ ዘበኛ ኢማሙን ስለማያውቃቸው "መስጂድ ውስጥ መተኛት አይፈቀድም፣ ውጣ!" በማለት አዘዛቸው። ኢማሙም "የምሄድበት ቦታ የለኝም" ቢሉም ዘበኛው ግን በግዴታ እየጎተተ ከመስጂዱ አወጣቸው።

​በዚህ መሀል በመስጂዱ አቅራቢያ ዳቦ የሚጋግር አንድ ሰው ሁኔታውን ይመለከት ነበር። የኢማሙን መንገደኛነትና አዛውንትነት አይቶ አዘነላቸውና "ወደ ቤቴ መጥተህ ማረፍ ትችላለህ" በማለት ጋበዛቸው።

​ኢማም አሕመድ ወደ ዳቦ ጋጋሪው ቤት ገቡ። ሰውየው እንግዳውን ካስተናገደ በኋላ ወደ ስራው ተመለሰ። ኢማሙ በትኩረት ይመለከቱት ጀመር። ዳቦ ጋጋሪው ዱቄቱን ሲያቦካ፣ ሊጡን ሲያዘጋጅና ዳቦውን ወደ ምድጃው ሲያስገባ ያለማቋረጥ "አስተግፊሩላህ" (አላህ ሆይ ማረኝ) እያለ ይዘክራል። ከምላሱ ዚክር አይለይም ነበር።

​ኢማም አሕመድ በዚህ ሰው ተግባር እጅግ ተገረሙና እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ "ይህንን ዚክር በማዘውተርህ ያገኘኸው ፍሬ አለን?"

​ዳቦ ጋጋሪውም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "አዎ! በአላህ እምላለሁ፤ የጠየቅኩት ዱዓ ሁሉ ተቀባይነትን አግኝቷል። አንድ ዱዓ ብቻ ሲቀር።"

​ኢማሙም በጉጉት "ያ ያልተመለሰልህ ዱዓ ምንድን ነው?" አሉት።

​ሰውየውም "ታላቁን የሐዲስ ሊቅ ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበልን በአካል አይቼው እንድሞት አላህን ለምኜው ነበር፤ እስካሁን ግን አላገኘሁትም" አላቸው።

​በዚህ ጊዜ ኢማም አሕመድ እንባቸው መፍሰስ ጀመረ። "አላሁ አክበር! አላህ ዱዓህን ሰምቶሃል! መስጂድ ውስጥ መተኛት ከልክሎኝ በዘበኛ እየተጎተትኩ ወደ አንተ ቤት የመጣሁት እኔው አሕመድ ቢን ሐንበል ነኝ። አላህ ያንተን ዱዓ ለመቀበል እኔን እስከ ቤትህ ድረስ አምጥቶኛል" አሉት።

​ሁለቱም በደስታ ተቃቀፉ።

​ምንጭ፦ "መናቂቡል ኢማም አሕመድ" (ኢብኑል ጀውዚ)

​ #ትዝብት #ፈገግታ

ሁላችንም በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ፣ ጭንቅ ሲበዛብንና መውጫ ቀዳዳ ያጣን ሲመስለን የምንጠጋበት፣ የልባችንን የምናፈስበት ኃይል እንፈልጋለን። ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ደግሞ እንዲህ ይ...
08/05/2026

ሁላችንም በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ስናልፍ፣ ጭንቅ ሲበዛብንና መውጫ ቀዳዳ ያጣን ሲመስለን የምንጠጋበት፣ የልባችንን የምናፈስበት ኃይል እንፈልጋለን። ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ። ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
(ሱረቱ በቀራ 186)

የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን 🥰

ኸሚስ 💚የታላቁ ነቢይ ናፋቂዎች ሆይ! ዛሬ ደግሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን፣ ልባችንን አውርደን በሳቸው ላይ ሰለዋት እናውርድ። አንድ ጊዜ በእሳቸው ላይ ሰለዋት ላወረደ አላህ በእሱ ላይ አስር...
07/05/2026

ኸሚስ 💚

የታላቁ ነቢይ ናፋቂዎች ሆይ! ዛሬ ደግሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን፣ ልባችንን አውርደን በሳቸው ላይ ሰለዋት እናውርድ። አንድ ጊዜ በእሳቸው ላይ ሰለዋት ላወረደ አላህ በእሱ ላይ አስር ጊዜ እዝነቱን ያወርዳል።"
ሰሉ ዐለል ሀቢብ 💚

​ #ትዝብት #ፈገግታ

ጥያቄያችንን ቀድሞ በመመለስ አሸናፊ የሆነው ቶፊቅ ሀይረዲን  ነው።​በመላው ቁርአን ውስጥ "ሁለት ሱጁዶች የሚገኙባት ብቸኛዋ ሱራ የትኛዋ ናት?" ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛው መልስ፦​ሱረቱ አል-...
06/05/2026

ጥያቄያችንን ቀድሞ በመመለስ አሸናፊ የሆነው ቶፊቅ ሀይረዲን ነው።
​በመላው ቁርአን ውስጥ "ሁለት ሱጁዶች የሚገኙባት ብቸኛዋ ሱራ የትኛዋ ናት?" ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛው መልስ፦
​ሱረቱ አል-ሐጅ (Surah Al-Hajj) ናት።

​ለታታሪ ተሳታፊዎቻችን ምስጋና ይግባችሁ። ቀጣይ በሌላ የሽልማት ጥያቄ እንመለሳለን ❤
​ #ትዝብት #ፈገግታ

Address

Addis Ketema Sub City, House No 048/B
Addis Ababa
1000

Website

http://www.somitube.com/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Isehacbaba posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Isehacbaba:

Share