Mekonen negash

Mekonen negash Actor and production manager,castingand advertising

07/02/2025
 #ኢትዮጵያ2017እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦- የሰላም- የፍቅር - የአንድነት- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት- ደመ የማይፈስበት- ሰው ታገተ፣...
11/09/2024

#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ደመ የማይፈስበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የማንሰማበት
- በመላ ሀገሪቱ ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የማንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
- ሁሉም በአንድ መንፈስ ለእናት ሀገሩ " አለሁልሽ " ብሎ የሚቆምበት ያደርግል

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን ! #መኮንን ነጋሽ

“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናትልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እን...
28/04/2024

“ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ ” - የ9 ዓመቷ ታዳጊ እናት

ልጃቸው ለየልብ ህመም የታመመችባቸው እናት ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዟቸው ተማጽኑ።

ወ/ሮ መባ አላምረው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሊያ የ3ኛ ክፍል ተማሪ 2ኛ ልጄ ናት። #ልቧ 15 ሚሊ ሜትር #ክፍተት አለው ” ብለዋል።

የልብ ስፔሻሊቲ ዶክተርም፣ “ ‘ችግሩ ክፍተት መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን የቀኝ ልቧ አቅጣጫውን በመሳት ወደ ሳምባዋ ክፍል ደም እየረጨ ነው። ሳምባዋም ወደ ማበስበስ ደረጃ እየደረሰ ነው። በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት’ ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።

“ በፊት ላይ ‘ #የሳንባ #ምች ነው’ እየተባለ ነበር። አሁን ‘የልብ ክፍተት ነው’ ተባለች። #እጇንም #እግሯንም #መሸምቀቅ ጀመራት። ትምህርቷን አቋርጣ ቤት ከተቀመጠች 1 ወር ሆናት ” ብለዋል።

“ ‘ሳንባዋ ለንቅለ ተከላ የሚደርስ ነው’ አሉኝ ” ያሉት እኝሁ እናት፣ ለሰርጀሪው ብቻ 595 ሺሕ ብር፣ የሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ 700 ሺሕ ብር ለቀዶ ጥገና እንደተጠየቁ አስረድተዋል።

የታዳጊዋ እናት፣ “ ልጅ ያለው የልጅን ነገር ያውቀዋል። ቶሎ ካልታከመች ክፍተቱ እየጨመረ ነገሮች ሁሉ ይከብዳሉ። ሁሉም ያቅሙን በገንዘብም በጸሎትም እንዲተባበረኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳኝ እለምናለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

እናት መባ አላምረውን በስልክ ለማግኘት በ +251939665539 መደወል ይቻላል። የባንክ የሒሳብ ቁጥራቸው 1000470071536 ነው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912296692

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekonen negash posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share