Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ ፔጁን ላይክ ፎሎው በማድረግ የተለያዩ አነቃቂ እና ቁም ነገር አዘል የጥበብ ስራዎችን ይከታተሉ .

22/02/2026
07/01/2026
28/11/2025

የመጀመሪያ የፕሮዳክሽን ስራችን ነው ኑና መርቁልን .....

አዲስ የጎንደር ሙዚቃ እየመጣ ነው

እሁድ 8 : ዐዐ ሰአት ላይ በደብረብርሃን እምዬ ምኒልክ አዳራሽ የመጀመሪያ ምርቃቱን ያደርጋል ......



#ጎንደር

ልደትነሃሴ 14ጀግና ተወለደየጅሩ ሰው ነውብቻውን በቀል እንደ ክትክታየሚገነጠል የለውም መንታራስ አበበ አረጋይ
20/08/2025

ልደት

ነሃሴ 14
ጀግና ተወለደ

የጅሩ ሰው ነው
ብቻውን በቀል እንደ ክትክታ
የሚገነጠል የለውም መንታ

ራስ አበበ አረጋይ

የደብረ ብርሃን ሊቼ የባህል ቡድን አባላት የከተማውን የኮሪደር ልማት  ጎበኙደብረ ብርሃን፤ሀምሌ 25/2017 (ደብመኮ)፡-የባህል ቡድኑ የአካባቢውን ጥበብ ከማሳደግ ጎን ለጎን ለከተማ ልማትና...
01/08/2025

የደብረ ብርሃን ሊቼ የባህል ቡድን አባላት የከተማውን የኮሪደር ልማት ጎበኙ

ደብረ ብርሃን፤ሀምሌ 25/2017 (ደብመኮ)፡-የባህል ቡድኑ የአካባቢውን ጥበብ ከማሳደግ ጎን ለጎን ለከተማ ልማትና ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ እየተሰራ መኾኑን ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክለዮሃንስ ኃይለጊዮርጊስ እንደገለጹት በተቋማቸው ስር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባህል ቡድን አቋቁመውና ዕውቅና አሰጥተው ወደ ሥራ ለማስገባት ሥልጠና እየሰጡ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

የባህል ቡድኑ ዋና ሥራ የከተማውንና የሸዋን የጥበብ ሥራዎች ማውጣት ቢኾንም በከተማው የሚሰሩ ትልልቅ የልማትና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በጥበብ አዋዝቶ ማጉላት ሌላው ተግባሩ መኾኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የባህል ቡድኑ የአካባቢውን ጥበብ ከማሳደግ ጎን ለጎን ለከተማ ልማትና ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ እየተሰራ መኾኑን አመልክተዋል።

የዳበረ ልምድ ያላቸው ሙያተኞችን ያቀፈ የባህል ቡድን ነው ያሉት ኃላፊው፤ዛሬ የመንገድ ዳር ልማቶችን ጎብኝተው ልምድና ተሞክሮ እንዲቀስሙና ወደ ጥበብ እንዲቀይሩት የከተማውን የኮሪደር ልማት እንዲጎበኙ መደረጉን ጠቁመዋል።

የደብረ ብርሃን ሌቼ ባህል ቡድን ሥራ አስኪያጅ ነፃነት ዘውዴ በበኩላቸው ቡድኑ ሥራውን በስኬት መፈጸም የሚያስችል የክህሎት፣በጋራ የመስራት፣የስነ ምግባርና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ስልጠና እየወሰደ መኾኑን አስረድተዋል፡፡

ዛሬ የከተማውን የኮሪደር ልማት በመጎብኘታቸው ደስተኛ መኾናቸውን ገልጸው በቀጣይ በጥበብ አዋዝተው ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩ ፍንጭ ሰጥተዋል።

በሊቼ የባህል ቡድኑ የተሰየመበ ምክንያትም ዳግማዊ ምኒሊክ እና ዐፄ ዮሐንስ በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት ሊቼ ላይ በውይይት በመፍታት ለዘመናዊ የግጭት አፈታት መነሻ የኾነውን ድንቅ መላ ለዓለም ያስተዋወቁበትን ቦታ ስለኾነ ነው በማለት አብራርተዋል፡፡

በመኾኑም የባህል ቡድኑ አባላት የሌቼን ታሪክ በውል ተገንዝበው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አካባቢውን እንዲጎበኙ መደረጉንም አመልክተዋል፡፡

via = ደብረብርሃን ኮምንኬሽን

የሽዋ 38ቱ  ነገሥታት! በሽዋ ነገሥታት ጊዜ የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ቀይ ባሕር፣ የአደን ባሕረ ሰላጤ፣ ሕንድ ውቅያኖስ እና ላይ ኛው የአባይ ሸለቆ /ነጭ አባይ/ እንደሚያዋስኑት የታወቀ ሲ...
30/05/2025

የሽዋ 38ቱ ነገሥታት!

በሽዋ ነገሥታት ጊዜ የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ቀይ ባሕር፣ የአደን ባሕረ ሰላጤ፣ ሕንድ ውቅያኖስ እና ላይ ኛው የአባይ ሸለቆ /ነጭ አባይ/ እንደሚያዋስኑት የታወቀ ሲሆን፤ በውስጧ ያሉት የእስልምናና የክርስትና እንዲሁም የሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ሕዝቦች በማዕከላዊው መንግሥት ስር ተጠቃለው የሚተዳደሩ፣ ነገር ግን ላለመገብርና ራስ ገዝ ለመሆን የንጉሥ ነገሥት መንግሥቱን ሲወጉ የነበሩ አሉ።

በሽዋ ነገሥታት የነገሡት ስምና ዓ. ም👇

1/ አፄ ይኩኑ አምላክ (ከ1253_1268 ዓ. ም)

2/ አፄ አግብዓ ጽዮን (ከ1268_1277)

3/ አፄ ፅንፈ አርዕድ (ከ1277_1278)

4/ አፄ ሕዝበ አሠግድ (ከ1278_1279)

5/ አፄ ቅድመ አሠግድ (ከ1279_1280)

6/ አፄ ጃን አሠግድ (ከ1280_1281)

7/ አፄ ስበዓ አሠግድ (ከ1281_1282)

8/ አፄ ውድም አርዕድ (ከ1282_1297)

9/ አፄ ዓምደ ጽዮን 1ኛ (ከ1297_1327)

10/ አፄ ሰይፈ አርዕድ (ከ1327_1355)

11/ አፄ ውድም አስፈሬ (ከ1355_1365)

12/ አፄ ዳዊት (ከ1365_1395)

13/ አፄ ቴዎድሮስ 1ኛ (ከ1395_1399)

14/ አፄ ይስሐቅ (ከ1399_1414)

15/ አፄ እስክንድያስ (እስክንድር) (ከ1414_1414 በወራት ነው የነገሠው)

16/ አፄ ሕዝብናኝ (ከ1414_1418)

17/ አፄ በድልናኝ (ከ1418_1419)

18/ አፄ ዓምደ እያሱ "ዳዊት" (ከ1419_1426)

19/ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ (ከ1426_1460)

20/ አፄ በእደ ማርያም (ከ1460_1470)

21/ አፄ እስክንድር (ከ1470_1486)

22/ አፄ ዓምደ ጽዮን 1ኛ (ከ1486_1487)

23/ አፄ ናኦድ (ከ1487_1500)

24/ አፄ ልብነ ድንግል (ከ1500_1532)

25/ አፄ ገላውዲዎስ (ከ1532_1551)

26/ አፄ ሚናስ (ከ1551_1555 ዓ. ም)

በሸዋ ብቻ ንጉሥ የሆኑ ናቸው እኒህ:- አቤቶ ያዕቆቦች ይባላሉ!🥰

27/ አቤቶ ያዕቆብ

28/ አቤቶ ሥግው ቃል

29/ አቤቶ ነጋሲ(ነጋሲ ክርስቶስ)

30/ አቤቶ ስብስቴ(ሰብስቲያኖስ)

31/ መርድ አዝማች አብየ

32/ መርድ አዝማች አምሀየስ (አመኃ ኢየሱስ)

33/ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን

34/ መርድ አዝማች ወሰን ሰገድ

35/ ንጉሥ ሣህለ ስላሴ

36/ ንጉሥ ኀይለ መለኮት

እንደገና ሙሉ ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ!

37/ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ አፄ ምኒልክ (እምዬ)

38/ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ (ጃንሆይ)

ጥይት በጀበርና _ ዝናር ተንተርሶ፣
ሽዋ ሰው ይሰራል _ እንደ እግዜር አፍርሶ።

ብዕር 🙋
24/05/2025

ብዕር 🙋

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ        ...
20/04/2025

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

ወይእቲ አሚረ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምናዝሬት ዘገሊላ ወአጥመቆ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ወወጺኦ እማይርእየ ተሰጥቀ ሰማይ ወወረደ መንፈስ ቅዱስ ከመ ርግብ ወነበረ ዲቤሁ   ያን ጊዜም ጌታች...
19/01/2025

ወይእቲ አሚረ መጽአ እግዚእ ኢየሱስ እምናዝሬት ዘገሊላ ወአጥመቆ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ወወጺኦ እማይርእየ ተሰጥቀ ሰማይ ወወረደ መንፈስ ቅዱስ ከመ ርግብ ወነበረ ዲቤሁ ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ ዮሐንስም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀው ወዲያውኑ ከውኃው በወጣ ጌዜ ሰማይ ሲከፈት መንፈስ ቅዱስ እደ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ
ማር:1:9

እንኳን ለጌታችን ለመደሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ ።

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን .... በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የድህነት እንዲሆን የኀልዮ ሚዲያ ልባዊ ምኞት ነው ...
06/01/2025

እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን .... በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የድህነት እንዲሆን የኀልዮ ሚዲያ ልባዊ ምኞት ነው .....።

Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Halyo Media ኀልዮ ሚዲያ:

Share