Yami Media

Yami Media Yami media is a media that available in Addis Ababa Ethiopia and registerd in Ethiopian Media Authority. You can get different kinds of information.

So like,share and invite.

07/07/2022
ደራሲና አዘጋጅ ሰለሞን አለሙ ባደረበት ህመም ምከንያት ሰኔ 21 ቀን 2014ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ሰለሞን አለሙ በይበልጥ የሚታወቅበት አብዬ ዘርጋው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ደራ...
29/06/2022

ደራሲና አዘጋጅ ሰለሞን አለሙ ባደረበት ህመም ምከንያት ሰኔ 21 ቀን 2014ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ሰለሞን አለሙ በይበልጥ የሚታወቅበት አብዬ ዘርጋው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ደራሲ ብቻ ሳይሆን ተዋናይም ነበር።
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ከ አምስት ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችንና መነባንቦችን ሰርቷል።
ሰለሞን ለጥበብ ጊዜ የሰጠ ጥበብን ያነገሰ ጎበዝ ታታሪ ተዋናይ ደራሲ ነበር። የክብር አሸኛኘት ፕሮግራሙ የሥራ ባልደረቦቹ፣ ቤተሰቦቹ ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም የሙያ አድናቂዎቹ በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ከቀኑ 6:00 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል። የደራሲ ና አዘጋጅ ሰለሞን አለሙ የቀብር ሥነሥርዓት ሰኔ 22 ቀን 2014ዓ.ም ከቀኑ 8:00 በመንበረ ፀባኦተ ሥላሤ ካቴድራል ይከናወናል።
ያሚ ሚዲያ በሰለሞን አለሙ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ ፣ ለሥራ ባልደረቦቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

[ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።አቶ ተወልደ ይህን የገለፁት ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ...
23/03/2022

[


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።

አቶ ተወልደ ይህን የገለፁት ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብለው ጡረታ መውጣታቸውን ገልፀው ፤ ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጠዋል።

አቶ ተወልድ አየር መንገዱን ለ37 አመት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ያገለገሉ ሲሆን ላለፉት 11 አመታት በዋና ስራ አስፈፃሚነት አገልግለዋል።

አቶ ተወልደ በአገልግሎት ዘመናቸው " የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ስራ አስፈፃሚ " ን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሽልማቶችን ለግላቸው እና ለአየር መንገዱ አስገኝተዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም/ ይፋ አልተደረገም።

መረጃው የኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ (https://t.me/ethiopiacheck/1152) ድረገፅ ነው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ለ ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ዘጋቢው ቶማስ ጋርድነር ማስጠንቀቂያ ሰጠ! የኢፌዲሪ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ለተሰኘው ጋዜጣ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ቶ...
23/03/2022

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ለ ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ዘጋቢው ቶማስ ጋርድነር ማስጠንቀቂያ ሰጠ!

የኢፌዲሪ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ለተሰኘው ጋዜጣ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ቶማስ ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጠ።

: “መጋቢት 10 ቀን በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕወሓት መሪ ጋር ተነጋገሩ” በማለት በግል የትዊተር ገፁ ያሰራጨውን መረጃ የተመለከተው ባለስልጣኑ፤ የቶማስ ጋርድነር መረጃ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሀገራዊ ጉዳይ ሲሆን ተገቢውን የመረጃ ምንጭ ያልጠቀሰ እና በሚመለከተው ባለስልጣን ያልተደገፈ ነው ብሏል።

ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው “ይህ ተግባር የጋዜጠኛነትን ሙያ እና ንቃት የማይመጥን” በመሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል። በቀጣይ ዘገባዎቹም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጋዜጣኛውን አስጠንቅቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ!ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማ...
23/03/2022

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ!

ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከጤናቸው ጋር በተገናኘ በይፋዊ መንገድ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል።
ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም አቶ ተወልድ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታት አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡

22/03/2022

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙ ረቂቅ ህጎችን እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አምባሳደሩ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷በቅርቡ በአሜሪካ ሁለቱ ምክር ቤቶች ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የሚባሉ ረቂቅ ህጎች ኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ጫናዎችን ለመፍጠር በውይይት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
ረቂቅ ህጎቹ በተለይም ኢትዮጵያ እራሷን የመከላከል ሉዓላዊ መብቷን ለማስጠበቅ እራሷን በጸጥታው ዘርፍ እንዳታደራጅ የሚከለክሉ እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዳትጠናከር ለማድረግ ያለሙ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በጦርነቱ የወደሙ መሰረት ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ብድር እና እርዳታ እንዳይገኝ የሚከለክሉ መሆናቸውን ነው የጠቆሙት፡፡
ዜጎች በሀገር ቤት ውድ ህይወታቸውን ከፍለው ያረጋገጡትን ሉዓላዊነት ለማስከበር÷ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፉ መድረክ የሚመጡ ጫናዎችን በጋራ ሆነን መመከት አለብንም ብለዋል፡፡
ስለሆነም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ተትውልደ ኢትዮጵያውያን በግንባር የተሸነፉ አካላት በሌላ በኩል ይዘውት የመጡት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙ ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ የተጠናከረ ተቃውሞ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

22/03/2022

አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 እንዲቃወም ጥሪ አቀረቡ
************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 እንዲቃወሙ ጥሪ አቀረቡ።

ኢትዮጵያውያኑ ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተባሉት በአሜሪካ ምክር ቤቶች በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የታቀዱት አደገኛ ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ ሰፊ ዘመቻ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

አቶ ደመቀ በመላው አሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የታስክ ፎርስ፣ የሲቪክ ማህበራት አመራሮችና ተወካዮች ጋር ትናንት በዙም ውይይት አድርገዋል።
አቶ ደመቀ በአሜሪካ ም/ቤቶች በኢትጵያ ላይ ለማሳለፍ የታቀዱት ረቂቅ ሕጎች "እጅግ አደገኛ" ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሕጎቹ እንዳይፀድቁ ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ረቂቅ ሕጎቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ጨምሮ ዲያስፖራውን ከእናት ሀገሩና ዘመዱ ጋር የሚያቆራርጡ እጅግ አሳሪና ታይቶ የማይታወቅ የሉዓላዊነት መቀሚያ ረቂቅ ህጎች ናቸው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ ከተጣሉት ማዕቀቦች ሁሉ እጅግ የከፋው ማዕቀብ   ነው። ይህ ረቂቅ ህግ በአንድ በኩል ባለፈው አመት እንዳደረጉት በሰብዓዊ እርዳታ ስም ለህወሓት የጦር መሣሪያ ለማቅረብ ያለመ ...
22/03/2022

በኢትዮጵያ ላይ ከተጣሉት ማዕቀቦች ሁሉ እጅግ የከፋው ማዕቀብ ነው። ይህ ረቂቅ ህግ በአንድ በኩል ባለፈው አመት እንዳደረጉት በሰብዓዊ እርዳታ ስም ለህወሓት የጦር መሣሪያ ለማቅረብ ያለመ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በእርዳታ አቅርቦቱ ዙሪያ አንዳች ጥያቄ ቢያነሳ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉሎአል በሚል ማዕቀብ ይጣልበታል።
በዚህ መልኩ ያለ በቂ ምክንያት የሚጣለው ማዕቀብ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ እንዳይገዛ ለማድረግ፣ እንደ ሩሲያ፥ ቻይና፥ ቱርክ፥ የተባበሩት አረብ ኢሜሬት፥ ኢራን እና ኤርትራ ከመሳሰሉት ወዳጅ ሀገራት ምንም ዓንነት ድጋፍ እንዳያገኝ ማድረግ፣ እንዲሁም ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፥ የዓለም ባንክ፣ ከአሜሪካ ልማት ባንክ፣ ከአውሮፓ ልማት ባንክ፣ ከኢሲያ ልማት ባንክ፣ ከአረብ ልማት ባንክ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ምንም ዓይነት ብድር እንዳያገኝ ማድረግ እና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ፈንድን ማቋረጥ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
ይህ ሁሉን አቀፍ የሆነ ማዕቀብ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪ የፀጥታው ምክርቤት አባል ሀገራት፣ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት፣ የNATO አባል ሀገራት እና ሌሎች የአሜሪካ ወዳጅ ሀገራት ተሳታፊ ይሆናሉ ይላል። በአጠቃላይ የHR6600 የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን እንደ ሰሜን ኮሪያ፥ ኩባ፥ ኢራን ወይም ዝምባዋብዌ በማዕቀብ ማቆራመድ አሊያም ሀገራችንን እንደ ዩጎዝላቪያ፥ ሊቢያ፥ ኢራቅ፥ ሲሪያ ወይም የመን ማፈራረስ ነው።
ይህ ረቂቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊንታገለው የሚገባ የባርነት ቀንበር ነው። በሴራ እና ጦርነት ያልቻሉትን ነገር በማዕቀብ ኢትዮጵያን እንዲያፈርሱ መፍቀድ የለብንም

22/03/2022

ቻይና ከትላንናው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ እስካሁን አንድም የተረፈ ሰው አልተገኘም ብላለች።

ትናንት 132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረ " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል።

ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ማግኘት አለመቻሉን የቻይና መንግስት አስታውቋል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአውሮፕላን መከስከስ አደጋው በህይወት ያለ ሰው የማግኘት ተስፋቸው መደብዘዙን ማሳወቃቸውን TRT ዘግቧል።

22/03/2022
አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑክ ጋር የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት ተፈራረሙ፡፡ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከልዑኩ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በዘላ...
22/03/2022

አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑክ ጋር የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት ተፈራረሙ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከልዑኩ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በዘላቂ ልማት ዙሪያ ላይ ከተወያዩ በኋላ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑካን ቡድን ከክልሉ መንግስት ጋር በዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በህብረተሰቡ ህይወት ላይ ካደረሰው ተፅዕኖ መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ የልማት መርሃ ግብሮችን ለመተግበር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በማቀድና በመተግበር ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።

  የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት...
22/03/2022



የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት (AU) እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነው።

ልዩ መልዕክተኛው ትላንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴኦዬ ጋር መክረዋል።

ምክክራቸው ትኩረቱን ያደረገው በሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ጉዳዮች ላይ እንደነበር ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚታየውን አለመረጋጋት ለመፍታት የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከዚህ ቀደምም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበሩ አይዘነጋም።

Address

4kilo
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yami Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share