70 Derja

Call Website

70 Derja Welcome to 70derja❤
If you want to promote, talk to us inbox.

28/07/2026

አይ በስንቱ😂😂😂

  💎 ❤🇪🇹
09/07/2026

💎
❤🇪🇹

ቴዲ 100 ሺህ ብር ከፍሎ ከእስር አስፈታኝ!❤️🙏የታላቁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) "ኢቶሪካ" አልበም ግራፊክስ ዲዛይነር የሆነው ወጣት ዳዊት ሰለሞን፣ ለኪነጥበብ አባቱ ለቴዲ አ...
09/07/2026

ቴዲ 100 ሺህ ብር ከፍሎ ከእስር አስፈታኝ!❤️🙏

የታላቁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) "ኢቶሪካ" አልበም ግራፊክስ ዲዛይነር የሆነው ወጣት ዳዊት ሰለሞን፣ ለኪነጥበብ አባቱ ለቴዲ አፍሮ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

የ23 ዓመቱ ወጣት ዳዊት፣ ከወራት በፊት ጓደኞቹ ጋር በሄደበት አጋጣሚ በፖሊስ ተይዞ በእስር መቆየቱ ይታወሳል ።

ዳዊት በአቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶበት ፍርዱን ሲከታተል ቆይቶ በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ፍርድቤት ወስኗል።

የቴዲ አፍሮ ግራፊክስ ዲዛይነር ዳዊት የተጠየቀውን ገንዘብ በመክፈል በዋስ መለቀቁን ገልጾ፤ ቴዲ አፍሮ ዳዊት ጨምሮ አብረውት የታሰሩትን ተጠርጣሪዎችን የዋስትና ገንዘብ ከፍሎ ከእስር እንዲወጡ ማድረጉን ተናግሯል።

ወጣቱ ዳዊት የተጠየቀውን የዋስትና ገንዘብ ክፍያ ቴዲ አፍሮ በመክፈሉ ልባዊ ምስጋናውን ገልጾ፤"ማኔ ቴቄል ፋሬስ"በማለት የእግዚአብሔር ፍርድን የሚያመለከት መልዕክት አጋርቷል።

የግራፊክስ ባለሙያው ዳዊት ከምስጋና ባሻገር ለንጉሱ ቴዲ አፍሮ ለ50ኛ የልደት በዓሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

©️ዳዊት ሰለሞን
❤

▣ በ90ቹ መጨረሻ LOVE & PEACE የሚሉ በቴዲ አፍሮ ፎቶዎች የደመቁ ደብተሮች በብዛት ለገበያ ቀርበው ነበር። ብዙ ጊዜ የቴዲን ፎቶ ለማየት ወይም ለማሳየት ሲባል በዘመኑ ደብተሮቹ በሌላ...
26/04/2026

▣ በ90ቹ መጨረሻ LOVE & PEACE የሚሉ በቴዲ አፍሮ ፎቶዎች የደመቁ ደብተሮች በብዛት ለገበያ ቀርበው ነበር። ብዙ ጊዜ የቴዲን ፎቶ ለማየት ወይም ለማሳየት ሲባል በዘመኑ ደብተሮቹ በሌላ ነገር አይታሸጉም ነበር። በእነዚህ ደብተሮች የተማረ አለሁ ይበል?

▣ ፍቅር እና ሰላም! Love & Peace! ንጉሣችን ከብላቴናነቱ የጀመረው ይሄን ስብከት በጉልምስና ዘመኑም አስቀጥሎታል። መልዕክቱ ሁሉ ፍቅር ነው፣ ጩኸቱም ለሀገር እና ሕዝብ ሰላም ነው።

▣ ፍቅር ሲል እውነተኛ ፍቅርን ነው። አሸናፊ የሆነ ፍቅር - ፍቅር ያሸንፋል እንዲል። ሰላም ሲልም የአፍ ሰላም ሳይሆን በይቅርታ የሚፀና ነብስን የሚያሳርፍ ምልዑ ሰላም ነው።

▣ ፍቅርና ሰላም ለሁላችን ይሁን!



Teddy Afro

Amleset Muchie

❤

▣ 100 ሚሊዮን እይታ በ9 ቀን ብቻ🎶 ገባኮ ጎበዝ! ▣ ነገ ዳግማዊ 888 ነው። 8 ቁጥር ያው ኢቶሪካ ተብላለች።▣ ገና ይቀጥላል! YouTube ግቡ፣ ስሙ!https://youtu.be/sPYg...
25/04/2026

▣ 100 ሚሊዮን እይታ በ9 ቀን ብቻ🎶 ገባኮ ጎበዝ!

▣ ነገ ዳግማዊ 888 ነው። 8 ቁጥር ያው ኢቶሪካ ተብላለች።

▣ ገና ይቀጥላል! YouTube ግቡ፣ ስሙ!
https://youtu.be/sPYgRlfA-kc?si=0olIk81h-2C9uaI8


Teddy Afro
Amleset Muchie
Teddy Afro Fans

❤

25/04/2026

#በርታልን ጀግናው😍💪 ゚viralシfypシ゚

የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ መዘረፉየአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። ትናንት ማምሻውን የወጡ መረጃዎች መሣሪያ የታጠቁ እና በተ...
24/04/2026

የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ መዘረፉ

የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። ትናንት ማምሻውን የወጡ መረጃዎች መሣሪያ የታጠቁ እና በተሽከርካሪ የመጡ አካላት ጠባቂዎችን በመደብደብ አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ሲኤምሲ በሚባለው አካባቢ ከሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ንብረቶች መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው እኝህ የመረጃ ምንጭ፦ በበኩላቸው ትናንት ምሽት ወደ ሦስት ሰዓት ገደማ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። አክለውም ጠባቂዎችን በመደብደብ ስቱዲዮው ተሰብሮ አርቲስቱ ለሙዚቃ ሥራው የሚጠቀምባቸው ንብረቶች መዘረፋቸውንም አመልክተዋል።
አርቲስት ቴዎድሮስ በርካታ የሙዚቃ ሥራዎች እንዳሉት የገለጹልን የመረጃ ምንጩ፦ አብዛኞቹ እስካሁን አልወጡም ነው ያሉት። ቴዲ አፍሮ በየዕለቱ በሙዚቃ ሥራና ልምምድ፤ እንዲሁም የሙዚቃ ቅንብር ጊዜውን የማሳለፍ ልምድ አለው ያሉት የቅርብ መረጃ ምንጩ፤ በርካታ ግጥሞችና የሙዚቃ ሥራዎቹን ለሌሎች አርቲስቶች እንደሚሰጥም ገልጸውልናል።

ምንም እንኳን አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን «ኢቶሪካ» የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ከመውጣቱ በፊት ጀምሮ የሥነልቡና ጫና ሊያደርሱ የሚችሉ ወከባዎች በአካባቢው እየተፈጸሙ ቢሆንም እንቅስቃሴው ተገትቶም ቢሆን እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል። በመንግስት በኩል ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የተባለ ነገር የለም።

ዶይቸ ቬለ
DW
❤

በኢቶሪካ አልበም የተሳተፉ ባለሙያዎች‼️🔷 ቴዲ አፍሮ የ18ቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑ በተጨማሪ 'የአዞ እምባ አይደለም' በሚለው ዘፈን ላይ በአቀናባሪነት አግዟል🔷 'ፅዮን ሙሽራዬ...
24/04/2026

በኢቶሪካ አልበም የተሳተፉ ባለሙያዎች‼️

🔷 ቴዲ አፍሮ የ18ቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑ በተጨማሪ 'የአዞ እምባ አይደለም' በሚለው ዘፈን ላይ በአቀናባሪነት አግዟል

🔷 'ፅዮን ሙሽራዬ' በተሰኘው ሙዚቃ 23 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፤ ይህም በአልበሙ ውስጥ ከሚገኙ ሙዚቃዎች መካከል ብዙ ሰው ያሳተፈ ሙዚቃ አድርጎታል

🔷 በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያላቸው ባለሙያዎች በዚህ አልበም አሻራቸውን አሳርፈዋል፤ አንጋፋው የሊድ ጊታር ተጫዋች ሰላም ስዩም 'ዝ ፀዳል' እና 'ተወዳጅ' በተሰኙ ስራዎች ላይ ተጫውቷል፤ እውቁ የሳክስፎን ተጫዋች ያሬድ ተፈራ ደግሞ በስምንት ሙዚቃዎች ላይ ድንቅ ጥበቡን አሳይቷል፤ አበጋዝ ክብረወርቅ በሁለት ሙዚቃዎች ላይ በድምፅ ቅጂና በማስተሪንግ አስተዋፅኦ አድርጓል፤ ክብረት ዘኪዎስ በድምፅ ቀረፃ ተሳትፏል

🔷 'ፅዮን ሙሽራዬ' በአቦጊዳ ባንድ የተቀናበረ ሲሆን ቀሪዎቹ 17 ስራዎች በ6 ባለሙያዎች ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድና ማስተሪንግ ተሰርቶላቸዋል

🔷 ወጣቱ በረከት ተስፋዝጊ ስምንት ሙዚቃዎችን ሰርቷል፤ ታየኝ፣ መሬማ፣ ስምምነ፣ ዝ ፀዳል፣ በመስኮቱ፣ ብልጭታ፣ ሳምነው፣ የማዕረግ ጥግ የእሱ ውጤቶች ናቸው፤ በተጨማሪ ሊድ ጊታርም ተጫውቷል

🔷 የዳስ ጣል፣ ቲንታጎና ኢቶሪካ አቀናባሪ እንዲሁም የመሬማ፣ ታየኝ፣ ስምምነ፣ በመስኮቱ፣ ተወዳጅና የማዕረግ ጥግ ማስተሪንግ ቀማሚ ደግሞ ማሩ አለማየሁ ነው

🔷 አቤል ጳውሎስ የአዞ እምባ አይደለምና ተወዳጅ፥ ሀይፐር ዜማ መርከብና ስማ እራሴ፥ በፍቃዱ ግርማ ጀምበር እንዲሁም ሮቤል ዳኜ ሺ ቢባል ዜማዎችን አቀናብረውና ሚክስ አድርገው ለአልበሙ ስኬታማነት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል

🔷 ታመነ መኮንን ክራር፥ ቻላቸው አረጋና ወንድሜነህ ክፍሌ ማሲንቆ እንዲሁም ጣሰው ወንድምና ኤርሚያስ ናደው ዋሽንት በመጫወት የሀገራችንን ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪዎች ከዘመናዊው ጋር አቀናጅተው ለአልበሙ ተጨማሪ ጣዕም አበርክተዋል

🔷 ስድስት የውጭ ሀገር ዜጎችም ተሳትፈዋል፤ ጀምስ ክሮምዌል እና ኮይሲ ክሮምዌል ትራምፔት፥ ስቲቭ ብራድሊና ፎስተር ሞቲ ትራምቦን፥ ግሬግ ጃንግ ሳክስፎን፥ ዴስትኒ ፒቮንካ አልቶ ሳክስፎን ተጫውተዋል

🔷 ድምፃዊ አስገኘው አሽኮ(አስጌ ዴንዳሾ) በቲንታጎ ዘፈን በግጥምና በፊውቸሪንግ ተሳትፏል፤ ተዋናይ መኮንን ላዕከ ደግሞ በስማ እራሴ በድምፅ ግብአት ያልተጠበቀ ክስተት ሆኖ ተደምጧል፤ የወሎ እናቶች ምርቃት(ፀሎት)፣ የፀሀዬ ደመቀችና የኢትዮጵያ ትቅደም ዜማዎች እንዲሁም የአፄ ሀይለስላሴ ንግግር በጀምበር ሙዚቃ በድምፅ ግብአት ገብተዋል

🔷 ድምፃዊያኑ ሚኪያስ ቸርነት፣ ልዑል ሲሳይ፣ አዲስ ጉርሜሳ፣ ምኞት ሀይሉ(ዲጄ ዊሽ)፣ አለማየሁ ደሊልና በሀይሉ ዳንኤል አጃቢ ተቀባዮች ሆነው አልበሙን አድምቀዋል

በአጠቃላይ 50 የሚጠጉ ባለሙያዎች በኢቶሪካ አልበም ተሳትፈው ለስኬታማነቱ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል፤ ለሁሉም ምስጋና ይገባቸዋል!

(ታምሩ ዓለሙ)
❤

ቃሉ ፑቱክስ (Kalu Putiks) ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን በስፋት እያገኘ ነው! 🚀🌟በፈጠራው እና በይዘቱ ሁላችንም የምናደንቀው ተወዳጁ ቲክቶከር ቃሉ ፑቱክ በይፋዊ የኢንስታግራም (Instag...
24/04/2026

ቃሉ ፑቱክስ (Kalu Putiks) ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን በስፋት እያገኘ ነው! 🚀🌟
በፈጠራው እና በይዘቱ ሁላችንም የምናደንቀው ተወዳጁ ቲክቶከር ቃሉ ፑቱክ በይፋዊ የኢንስታግራም (Instagram) ገጽ ላይ እንዲተዋወቅ ትልቅ ግብዣ ቀርቦለታል። የግዙፋ ኢንስታግራም ድርጅች ኦፊሻል ገፅ፤ ከ700 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት አለም አቀፋዊ ገጽ ሲሆን፣ ቃሉን "በልዩ ሁኔታ ልናስተዋውቅህ እንፈልጋለን" በማለት በይፋ ጋብዞታል።
ይህ ግብዣ ትላንት በኢንስታግራም አካውንቱ በለቀቀው ቪዲዮ ላይ በተጻፈለት አስተያየት (ኮሜንት) የተደረገ ሲሆን፣ "Hi! We'd love to feature you on our account next week..." በሚል መልእክት የተረጋገጠ ነው። ይህ ለቃሉ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፈጣሪ ወጣቶች ትልቅ ሞራል እና ማሳያ ነው።
በእውነት የሚያስደስት ዜና ነው። እንኳን ደስ አለህ ቃሉ! 🎉
በውጤትህ ሁላችንንም አኩርተኸናል። ኢትዮጵያ ትኮራብሃለች!

Address

Great
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00

Telephone

+251983687914

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 70 Derja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share