Lisan tilahun

Lisan tilahun Jesus is the answer! በበዛው ድካማችን ብርታታችንን የገለጥክ አባ ዘላለም ክበርልኝ፤

21/04/2026
06/04/2026

ልዩ የትንሳኤ አዳር በሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስትያን ‼️

ሚያዝያ 3 ቅዳሜ ከምሽቱ 03፡00 ሰአት ጀምሮ የበአል የአዳር ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቹሀል፡፡ ሞትን ድል አድርጎ ለተነሳው ለትንሳኤው ንጉስ ልዩ አምልኮ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
ከፓስተር ታሪኩ ቴዎድሮስ ጋር የትንሳኤውን ሀይል እናውጃለን

!
" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
ትንቢተ ኢሳይያስ 53:3

አድራሻ፤

20/03/2026
12/03/2026

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በሦስት አህጉራት ላይ ነው፦‼️

➬አፍሪካ
➬አውሮፓ
➬እስያ

በሦስት ቋንቋዎች
➬ዕብራይስጥ
➬አረማይክ
➬ግሪክ

ከ40 በላይ በሚሆኑ ልዩ ልዩ ሰዎች
➬ነገሥታት
➬ነቢያት
➬ዓሣ አጥማጆች
➬ሐኪም

ሆኖም ግን አንድ ወጥ ታሪክ ይተርካል
➬ፍጥረት
➬ውድቀት
➬ቤዛነት (መድኃኒት)
➬ክርስቶስ

እግዚአብሔር ድንቅ ነው 🥰🙌🏾
ከወደዳችሁት ለሌሎችም እንዲደርስ #ሼር አድርጉት !!

07/03/2026

በፕሮቴስታንት የዝማሬ ታሪክ ዉስጥ ሪከርድ መስበር የቻለዉ ‘ዌይ ሜከር" መዝሙር‼

የናይጄሪያዊቷ ዘማሪ ሲናቼ ‘ዌይ ሜከር የተባለው ታዋቂ መዝሙር በዮቲዩብ ከ 200 ሚሊየን በላይ እይታ አገኝቷል፡፡

መዝሙሩ በታህሳስ 2015 በዩቲዩብ ለህዝብ የቀረበ ሲሆን በ2020 በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የክርስቲያን መዝሙር መሆን ችሎ ነበር፡፡

ዘማሪዋ መዝሙሩን ዘፍጥረት ምዕራፍ 12 ስታጠና መንፈስ ቅዱስ በሰጣት መረዳት እንደጻፈችውና ክርስቲያን ወገኖችን ለማበረታታት እንደዘመረችው ተናግራለች፡፡

መዝሙሩ አማርኛ ቋንቋን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት ቋንቋዎች ተተርጉሞ የተዘመረ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ እንደ ሊላንድ፤ ቤተል ሚዩዚክ መዘምራን እንዲሁም ሚካኤል ደብሊው ስሚዝ፣ ማንዲሳ፣ ክሪስታፋሪ እና ዳርሊንን በመሳሰሉ ታዋቂ ክርስቲያን ዘማሪዎች ተዘምሯል፡፡

‘ዌይ ሜከር’ በአሜሪካ 51ኛው ጂኤምኤ ዶቭ አዋርድ የአመቱ ምርጥ የወንጌል መዝሙር በሚል የተሸለመ ሲሆን በ ቢኤሜአይ የአመቱ ምርጥ መዝሙር በሚል ከአፊሪካ ቀዳሚ ሆንዋል፡፡

በተለይም በኮቪድ 19 ወረርሽን ወቅት ተስፋንና ጥንካሬን ለማደስ በየሆስፒታሉና በተለያዩ የህዝብ ስፍራዎች መዝሙሩ ይዘመር የነበረ ሲሆን ዘማሪ ሲናቼ ወደተለያዩ የአለም ክፍሎች በመጓዝ በዚህ ዝማሬ አገልግላለች፡፡

በቅኔ spritual tube ተንታኝ በልሳነወርቅ የቀረበ
ምንጭ:- (ሲላሃፍሪክ)

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lisan tilahun posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Lisan tilahun:

Share

Category