02/05/2026
🇪🇹
አዲስ የኢንስታግራም ታሪክ ለኢትዮጵያ
የቃሉ ፑቲክ (Kalu Putic) የአንድ ሌሊት አስደማሚ ስኬት!
ጠ ይ ም |
አንድ የፈጠራ ስራ በዲጂታሉ ዓለም ምን ያህል ርቀት ሊጓዝ ይችላል? ኢትዮጵያዊው የጥበብ ሰው እና ኮንቴንት ክሪኤተር ቃሉ ፑቲክ የዚህን ጥያቄ መልስ በተግባር አሳይቶናል።
ቃሉ የ1 ሚሊዮን ተከታዮችን (1M Followers) ስኬት ከደጋፊዎቹ ጋር ለማክበር በዝግጅት ላይ ሳለ፣ ባሳለፍነው ለሊት ያጋራው አንዲት አጭር ቪዲዮ (Viral Video) ያልታሰበ እና የሁሉንም ግምት የቀየረ ክስተት ፈጥራለች።
በአንድ ጀምበር ብቻ የገጹ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት ተተኩሶ 2.5 ሚሊዮን የገባ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓትም 2.8 ሚሊዮን በማለፍ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ቃሉ ለ1 ሚሊዮን ዝግጅት ሲያደርግ፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን በድንቅ የፈጠራ ስራው ተማርኮ እጥፍ ድርብ ስጦታ አበርክቶለታል።
ይህ አስገራሚ እምርታ ቃሉን በኢንስታግራም መድረክ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማፍራት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል። ይህ ስኬት የቁጥር እድገት ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያዊያን የፈጠራ አቅም በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚችል የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው።
ለቃሉ ፑቲክ፣ እንዲሁም ለጠይም የዲጂታል ሚዲያ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
👏
#ጠይም