Desta kussa ye Itiye lij

Desta kussa ye Itiye lij I love wolayta and Ethiopia

05/11/2025
‎አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል -የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ‎ወላይታ ሶዶ፤‎ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም በክልሉ አዲሱ የኑሮ ማሻ...
05/11/2025

‎አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል -የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ

ወላይታ ሶዶ፤‎ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም በክልሉ አዲሱ የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቅር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተጠቁሟል።

‎በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የወላይታ ሶዶ ክላስተር ማዕከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ ፣መንግስት የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ ለመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቁመዋል።

‎ይህንኑ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ፣ ክፍያውን ለመፈፀም የሚያግዙ መረጃዎች በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በመግባት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎የኑሮ ማሻሻያ ቋሚ፣ መደበኛና ጊዜያዊ የመንግስት ሰራተኞችን እንደሚያካትት ገልፀው ፣ክፍያው በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቀር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎አሁን ላይ በታችኛው መዋቀሮች አልፎ አልፎ የመረጃዎች ክፍተቶች ስለመኖራቸው የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፣ይህም በአጭር ጊዜ ተሟልተው ለክልል ፋይናንስ ገቢ ሆኖ ክፍያ ይፈፀማል ብለዋል።

‎በተወሰኑ በታችኛው መዋቀሮች ደመወዝንና ደረጃን በትክክል የሚገልጹ የመረጃ ክፍተቶች እንደ ችግር መታየቱን ጠቁመው ፣ይህንኑ የማጥራት ስራ እየተፋጠነ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

‎የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አዲሱን የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፤ ማህበረሰቡ በሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

#ምንጭ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ

02/11/2025

ኸረ ጆሮ ያለው መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ሶዶ ላይ ያላቹ ወይ ደረሰኝ አይቆረጥ። መነሐሪያ በጠራራ ፀሐይ ዝርፊያ እየተካሄደ ነው ካልሰማቹ ስሙ

02/11/2025

እኔም ዝም አልልም በሚል፣ 👇
እኔ ምለው #የኦቶና ሆስፒታል ግንባታ ጉዳይ የት ደረሰ? ምን ያህል ገንዘብስ ተሰበሰበ? ግንባታው እስካሁን የዘገየው በምን ምክንያት ነው? ከዚህ የሚበልጥ ጉዳይ ለሕዝብም ለመንግስትም ምን አለና ነው ዝምታ የተመረጠው? እስከመቼስ ነው እንዲህ እየጠየቅን የምንቆየው?
ጥያቄያችን እኮ ችላ የሚባል የቅንጦት ጥያቄ አይደለም ፤ የሚሊዮኖች የጤና ጉዳይ (የመኖር ያለመኖር) የሕልውና ጉዳይ እንጂ...የጤና ጉዳይ ከፋይዳ መታወቂያም ፣ ከኮሪደር ልማቱም ፣ ከመዋቅር ማሻሻያም በላይ ወሳኝና አንገብጋቢ ነው ።

01/11/2025
01/11/2025
23/10/2025
23/10/2025

Address

Addis Ababa
SODDO

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Desta kussa ye Itiye lij posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share