አደይ

አደይ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አደይ, Arts and entertainment, Any Where, Addis Ababa.
(2)

“መንግስት የምፈልገውን ቦታ ከሰጠኝ፣ 10-Star ሆቴል ለመገንባት ዝግጁ ነኝ!” ሼይኽ ሙሀመድ አሊ አላሙዲሼይኽ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ በኢትዮጵያ ከሚገኘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞ...
17/09/2026

“መንግስት የምፈልገውን ቦታ ከሰጠኝ፣ 10-Star ሆቴል ለመገንባት ዝግጁ ነኝ!” ሼይኽ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ

ሼይኽ ሙሀመድ አሊ አላሙዲ በኢትዮጵያ ከሚገኘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞች ጋር በቅርቡ ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ባለ 10-ኮከብ ሆቴል ለመገንባት ያላቸውን ሀሳብ ገልጸዋል።

ሼይኹ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የዓለም ትልልቅ ሀብታሞችና የG20 ሀገራት ተሳታፊ የሚሆኑባቸውን ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማስተናገድ የሚመጥን ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሆቴል ሊኖራት ይገባል።

“ሆቴሎች አሉ፤ ነገር ግን እነዚህን እንግዶች የሚመጥን ሆቴል ያስፈልጋል” በማለት ሀሳባቸውን ያብራሩት ሼይኹ፣ የሚመሯቸው ኢንጂነሮች እንዳሉና የ10-Star ሆቴል ግንባታውን ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም፣ መንግስት የሚፈልጉትን ቦታ ከሰጣቸው ፕሮጀክቱን ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፣ መንግስትም ሀሳቡን እንዲያጤነው ጥሪ አቅርበዋል።

“ህልምና ምኞት አይከለከልም” ሲሉም ኢትዮጵያዊዉ ባለፀጋ አላሙዲ ራዕያቸውን ገልጸዋል።

ረዳት ኮሚሽነሩ አረፉ! የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ረዳት ኮሚሽነር ኦሊ አባመጫ ህይወታቸው አልፏል። የረዳት ኮሚሽነር ኦሊ አባመጫ ቀብር ስነስርዓት ነገ ጁመአ ሶላት ከተ...
17/09/2026

ረዳት ኮሚሽነሩ አረፉ!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ረዳት ኮሚሽነር ኦሊ አባመጫ ህይወታቸው አልፏል።
የረዳት ኮሚሽነር ኦሊ አባመጫ ቀብር ስነስርዓት ነገ ጁመአ ሶላት ከተሰገደ በኃላ ከሰዓት በከፋ ዞን ቦንጋ ሙስሊሞች ቀብር ቦታ ቡስጣ ወዳጅ ዘመዶች የስራ ባልደረቦች በተገኙበት በወታደራዊ ስነስርዓት ይፈጸማል።

ጫት ሲያስገቡ በተገኙ ላየ እርምጃ ተወሰደ በሸርቆሌ ወረዳ የተላለፉ ክልከላዎችን በመጣስ ወደ ሸርቆሌ ከተማ ጫት ይዘው ሲገቡ የተገኙ ጫት ነጋዴዎች ላይ ፖሊስ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የወረዳ...
17/09/2026

ጫት ሲያስገቡ በተገኙ ላየ እርምጃ ተወሰደ

በሸርቆሌ ወረዳ የተላለፉ ክልከላዎችን በመጣስ ወደ ሸርቆሌ ከተማ ጫት ይዘው ሲገቡ የተገኙ ጫት ነጋዴዎች ላይ ፖሊስ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የወረዳው ፖሊስ አስታወቋል።

የሸርቆሌ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል መከላከል ዘርፍ የስራ ሂደት የሆኑት ዋና ሳጅን አብዱረሂም አኑር ጉዳዩን አስመልክተው እንደገለጹት በቅርቡ በብሄረሰብ ምክር ቤቱ የተላለፉ ክልከላዎችን የጣሱ የጫት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

ከህብረተሰቡ እና ከነጋዴዎች ጋር በክልከላው ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ይህን ወደጎን በመተው አንዳንድ ነጋዴዎች ድርጊቱ ሲፈጽሙ በመገኘታቸው እርምጃ መወሰዱን የተናገሩት ዋና ሳጅኑ ሌሎች ነጋዴዎችም ይህን አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቁጥጥር ስር የዋለው ጫትም ፖሊስ እና የወረዳ አመራሩ በተገኘበት ወዲያውኑ በህዝብ ፊት እንዲወገድ መደረጉን ገልጸው የቁጥጥር ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ይስሐቅ የአምላኩን ቃል ሰምቶ በመታዘዝ ባዶውን ምድር እንደ ሰፊ የስራ ዕድል ተመለከተው! እግዚአብሔር አብሮት ያለ ሰው አይሸሽም ይልቁኑ 🤌በችግሩ ላይ መፍትሔ ሆኖ ይገለጣል። ለለውጥ ቀዳሚ ...
16/09/2026

ይስሐቅ የአምላኩን ቃል ሰምቶ በመታዘዝ ባዶውን ምድር እንደ ሰፊ የስራ ዕድል ተመለከተው! እግዚአብሔር አብሮት ያለ ሰው አይሸሽም ይልቁኑ 🤌በችግሩ ላይ መፍትሔ ሆኖ ይገለጣል።

ለለውጥ ቀዳሚ መሆን በአካባቢው ማንም ያልሞከረውን አዲስ ነገር በድርቅ ወቅት መዝራት እብደት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን እውነተኛ ስኬት የሚመጣው የሰዎችን ፍርሃት ጥሶ መውጣት ሲቻል ነው። መቶ እጥፍ ማጨድ የሰዎችን ልማድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚከተሉ ደፋሮች የሚሰጥ ሽልማት ነው!

ይስሐቅ መቶ እጥፍ ሲያፍስ ፍልስጥኤማውያን በቅናት ጉድጓዱን ደፈኑበት። እርሱ ግን አልተናደደም አልተጣላም፤ እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ ቆፈረ።

👉 ብስለት ማለት ከሚያናድዱህ ሰዎች ጋር መታገል ሳይሆን በውስጥህ ያለውን የበረከት ምንጭ ማመን ነው! በቃ!!! ያንተ የሆነውን ማንም ሊቀማህ አይችልም!!! አካባቢህ ሳይሆን አመለካከትህ ነው ታሪክህን የሚወስነው። "ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘራ፥ በዚያችም ዓመት መቶ እጥፍ አጨደ" (ዘፍጥረት 26:12)

ቶጎ የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እንዲከተሉ ጥሪ አቀረበችየቶጎ መንግሥት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የመላው አፍሪካውያንን ታሪካዊና ባህላዊ ማንነት የሚያንፀባርቅ አህ...
13/09/2026

ቶጎ የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እንዲከተሉ ጥሪ አቀረበች

የቶጎ መንግሥት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የመላው አፍሪካውያንን ታሪካዊና ባህላዊ ማንነት የሚያንፀባርቅ አህጉራዊ የአዲስ ዓመት አከባበርና የጊዜ አቆጣጠር እንዲኖራት ጥሪ አቀረበች። ሀገሪቱ ጥሪዋን ባቀረበችበት ወቅት፣ የአውሮፓውያንን የኮሎኒያል የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት በመተው፣ የራሳቸውን ታሪክና ማንነት የሚያጎላ የጊዜ ስሌት መጠቀም ይገባቸዋል ስትል አሳስባለች።

ለዚህም አህጉራዊ አንድነትና የነፃነት ምልክት ለሚሆነው አዲስ የጊዜ አቆጣጠር መፍትሔው መላው አፍሪካውያን የኢትዮጵያን የቀን መቆጠሪያ (ካላንደር) መጠቀም እንደሆነ ቶጎ ገልጻለች። የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነፃነት፣ የጥንታዊ ሥልጣኔና የራስ የመቻል ምሳሌ ተደርጎ ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ፣ የሌሎች አፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እንደ አህጉራዊ ኩራትና ሞዴል አድርገው በሚመለከቱበት በዚህ ወቅት፣ በሀገር ውስጥ የሚስተዋሉ የካላንደር ለውጥ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ቅሬታና ስጋት እያስከተሉ ይገኛሉ።

የሀገሪቱን ጥንታዊ የጊዜ አቆጣጠርና ታሪካዊ ቅርስ ከመጠበቅ ይልቅ በጥቂት ወገኖች የሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ የታሪክ ግንዛቤ ማነስ ውጤት ነው በሚል በህዝቡ ዘንድ ጠንካራ ውግዘት ገጥሞታል። ሀገራዊ እሴትንና ማንነትን አጥብቆ መያዝ በሚገባበት በዚህ ወቅት የሚወሰዱ መሰል እርምጃዎች የሀገሪቱን ታሪካዊ ማዕረግና አንድነት የሚያዳክሙ ናቸው የሚሉ ስጋቶችም እየተነሱ ይገኛሉ።

"ቀን ጣለው ብሎ ወንድሙን ያልካደው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ" ያስተላለፉት የደስታ መልዕክት" ለክርስቲያን ታደለ እና ለተፈቱት ወንድምና እህቶቻችን የቀረበ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንኳን...
12/09/2026

"ቀን ጣለው ብሎ ወንድሙን ያልካደው ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ" ያስተላለፉት የደስታ መልዕክት"

ለክርስቲያን ታደለ እና ለተፈቱት ወንድምና እህቶቻችን የቀረበ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

እንኳን እግዚአብሔር አስፈታህ ክሪስ ወንድሜ! ሌሎችም አብረዋችሁ የተፈታችሁ ወንድሞችና እህቶቻችን፣ ለቤታችሁና ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እግዚአብሔር በሰላም አበቃችሁ።

እስካሁንም በእስር ላይ የሚገኙት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የነፃነት አየር ተንፍሰው፣ በቅርቡ ከሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ አሁንም ጸሎታችንና ምኞታችን ነው ሲል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ መልዕክቱን በሶሻል ሚድያ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

"ቀን ጣለህ ብሎ ወንድሙን ያልካደ፣ በእያንዳንዱ የፓርላማ መድረክ ድምፅ ሆኖ 'ፍቱት!' እያለ ስለ ፍትህ የተከራከረለት የቁርጥ ቀን ወንድሙ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፤ ለተከበረው ወንድሙ ክርስቲያን ታደለ የነፃነት አየር በመተንፈሱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታና የእንኳን አደረሰህ መልዕክት በታላቅ ፍቅርና አክብሮት አስተላልፏል።

ሃላፊዉ ተገደሉ! የደላንታ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ሲሳይ በመንግስት ስራቸዉ ላይ ውለው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ለጊዜዉ ባልታወቀ ሁኔታ ተተኩሶባቸዉ ተገድለዋል።
12/09/2026

ሃላፊዉ ተገደሉ!

የደላንታ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ሲሳይ በመንግስት ስራቸዉ ላይ ውለው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ለጊዜዉ ባልታወቀ ሁኔታ ተተኩሶባቸዉ ተገድለዋል።

አዲስ አመትን አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተዘጋጀው የድሮን ትርዒት ላይ የተወሰደ ምስል
10/09/2026

አዲስ አመትን አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተዘጋጀው የድሮን ትርዒት ላይ የተወሰደ ምስል

ከንቲባዉ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ለችግረኞችና በኮሪደር ልማት ስራ ለተነሱ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የበአል ስጦታ ማዕድ አደረጉ! የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ አዲስ አመትን...
10/09/2026

ከንቲባዉ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ለችግረኞችና በኮሪደር ልማት ስራ ለተነሱ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የበአል ስጦታ ማዕድ አደረጉ!

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለችግረኞችና በኮሪደር ልማት ለተነሱ እንዲሁም ለቀበሌ ቤት ነዋሪ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የበአል ስጦታ ማዕድ አደረጉ!

ከንቲባዉ ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በዓሉን ስናከበር የተቸገሩና ደጋፊ ያጡ ወገኖችን በመደገፍና በመርዳት ሊሆን ይገባል። ሲሉ ገልጸዉ ድጋፉ በዚህ የሚያበቃ እንዳልሆነና የተጀመረው የመኖሪያ ቤት ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ ከጎናቸው በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም አክለው ተናግረዋል።

በዲላ ወጣቱ በፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ተገደለ በቅርቡ ትዳር የመሰረተዉ ይህ ወጣት ዜጋ ዛሬ በዲላ ከጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከፌደራል ጉምሩክና ከፌደራል መከላከያ ሰራዊት እውቅና እና ቁጥጥ...
09/09/2026

በዲላ ወጣቱ በፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ተገደለ

በቅርቡ ትዳር የመሰረተዉ ይህ ወጣት ዜጋ ዛሬ በዲላ ከጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከፌደራል ጉምሩክና ከፌደራል መከላከያ ሰራዊት እውቅና እና ቁጥጥር ውጭ በፖሊሶች በተተኮሰበት ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።

Address

Any Where
Addis Ababa
291

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አደይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share