Gech Entertainment

Gech Entertainment I am pharmacist

02/04/2023

በእርግዝና ወቅት ትክክለኛውን አቅጣጫ መርጠሽ ተኚ

በእርግዝና ወቅት በሰውነትሽ ላይ የተለያዮ ለውጦች ይከናወናሉ በዚህም ምክንያት የእንቅልፍ ማጣት ወይም መዘበራረቅና ምቾት ማጣት ይከሰታሉ።

ጥሩ እንቅልፍ ትተኚ ዘንድ በእርግዝና ወቅት የሚመከሩ የአተኛኝት አቅጣጫዎችን ሞክሪያቸው።

በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ሳምንታት በጀርባሽ መተኛት በፍጽም አይመከርም፤ ምክንያቱም የማህፀን ክብደት የደም ቧንቧዎችን በመጫን ወደ ልብ የሚሄደውን የደም ፍሰት ስለሚቀንሰው ነው።

በአብዛኛው የሚመከረው የአተኛኝት አቅጣጫ በግራ በኩል ሲሆን በአኦርታና ቬና ኬቫ (በደም ቅዳና በደም መልስ) ላይ የሚደርስን ጫና ስለሚቀንስ ነው።

ከቆይታ በኋላ ድካምና ቁስለት ሊኖር ስለሚችል ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መገላበጥ አስፈላጊ ይሆናል፤ ይህም በቀኝ በኩል መተኛትን ተመራጭ ያደርገዋል።

ነገር ግን የምቾት ማጣት ስሜት ከተሰማሽ ተመልሰሽ በግራ ጐንሽ ተኚ።

✅ የጥንቃቄ ምክሮች

በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወቅት ጊዜ በቀኝ በኩል መተኛት ጥሩ ነው፤ ነገር ግን በማህፀን መጠን መተለቅ ምክንያት ይበልጥ ተመራጭ (Best Choice) አይደለም።

በቀኝ እጅሽ በኩል በምትተኝበት ወቅት ጉበትሽ ላይ ጫና ይፈጠራል፤ ይህም ጉበት በትክክል ተግባሩን እንዳይወጣ ያደርገዋል።

✅ በእርግዝና ወቅት ትክክለኛ የአተኛኝት አቅጣጫ

👉 ተመራጭ አቅጣጫ

ለእርስዎም ሆነ ለህፃኑ በእርግዝና ወቅት በጐን በኩል ወይም በጐን አቅጣጫ መተኛት በጣም ተመራጭ ነው።

በእርግዝና ወቅት በቀኝ በኩል መተኛት ችግር የለውም ነገር ግን በግራ በኩል በጣም ተመራጭ ነው።

ተመራጭ የሆነበትም ዋና ምክንያት ለህፃኑ አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ለማድረስ የተሻለ የደም ዝውውር ስለሚኖር ነው።

በተጨማሪም በጉበት ላይ የሚደርሰውን የክብደት ጫና ይከላከላል።

👉 ሊያቆሙት የሚገባ የአተኛኝት አቅጣጫ

1️⃣ በጀርባ መተኛት

የእርግዝና ጊዜዎ በጨመረ ቁጥር ይህ አቅጣጫ አመቺ ወይም ተስማሚ አይደለም ምክንያቱም የሆድዎ ክብደት በዋና ዋና የደም ቧንቧዎች ላይ ተጨማሪ ግፊት በመፍጠር፤ ለእርስዎም ሆነ ለህፃኑ ዝቅተኛ የደም ዝውውር እንዲኖር ያደርጋል።

በተጨማሪም በጀርባ መተኛት ከአተነፋፈስ፣ ከምግብ መፈጨት፣ ከክንታሮትና ከጀርባ ህመም ችግር ጋር ይያያዛል።

2️⃣ በሆድ በኩል መተኛት

🅾️ ተጨማሪ ነጥቦች

🔹የትንፋሽ ማጠር ካጋጠምት ደረትዎን ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ ትራስ ይጠቀሙ።

🔹የጀርባ ህመም ስሜት ከተሰማዎት በግራ ወይም ቀኝ ጐንዎ በመተኛት ከሆድዎ ስር ትረስ ያስገቡ ወይም በጉልበትዎ መካከል ትራስ ያስገቡ።

🔹ከጐን ወደ ጀርባ ወይም ወደ ፊት በሚገላበጡበት ወቅት ምንም ስጋት አይግባዎ።

አንዳንድ ጊዜ ለመገላበጥ በየደቂቃው ከመንቃት ይልቅ ሰዉነትዎ ወደሚመቸው አቅጣጫ እንዲገላበጡ መፍቀድ ተመራጭ ነው።

መልካም ጤንነት!!

ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፤

የ YouTube ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://youtube.com/

የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ እና ሸር ያድርጉ:
www.facebook.com/EthioTena

08/06/2022
02/06/2022

Selam

30/04/2020

👇♥
ከዚህ በላይ ምስክርነት የለም
ይሄ መስቀል በሰው እጅ የተቀረፀ አይደለም
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በተኩለሽ ከተማ አካባቢ ድንጋዩ ሲፈነቀል የተገኘ ድንቅ ከድንጋይ ላይ እንደፀሀይ ነፀብራቅ የሚያንፀባርቅ መስቀል ነው።
መስቀሉንም ለህብረተሰቡ የእግዚአብሔርን ተአምሩ በመንገር በክብር ተቀምጧል።
ሼር በማድረግ ይሄን ድንቅ ተአምር ለሁሉም አሳዩ
እግዚአብሔር ይህን እሚያሳየን በእምነታችን ሳንጠራጠር እስከመጨረሻው እንድንዘልቅ ነው።
ቴሌግራም ያልተቀላቀላችሁ የተዋህዶ ልጆች Join አድርጉ
t.me//JOIN_maryam_amalajinet_TELEGRAM
የመስቀሉ ፍቅር የገባው አሜን🙏🙏

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gech Entertainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to Gech Entertainment:

Share