22/09/2025
አያጋጥማችሁ 🙏🙏
አሜሪካዊው ኬቨን ስትሪክላንድ ባልፈፀመው ወንጀል 43 አመታትን በእስር ያሳለፈ ሲሆን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ለረዥም አመታት ያለምንም ጥፋት እና ወንጄል በግፍ ከታሰሩት ሰዎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።
ስትሪክላንድ ያለምንም ጥፋት ወንጄል ፈፅመሀል ተብሎ ከአራት አስርት አመታት በላይ በግፍ የታሰረና በጣም ልብ የሚሰብር ታሪክ ያለው ሰው ነው ።ስትሪክላንድ ምንም እንኳን ንፁህ ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም ገና በወጣትነት አፍላ እድሜው ፣በ18 ዓመቱ በካንሳስ ከተማ ፣ሚዙሪ ውስጥ በሦስት እጥፍ የግድያ ወንጄል ተከሶ የእድሜ ልክ አስራት ይፈረድበታል ።
ኬቨን ስትሪክላንድ ወንጀሉን እንደፈፀመ ምስክርነት የተሰጠው ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል በአንዲት ሴት ምስክርነት ላይ ብቻ ነበር የተመሰረተው፤ በኋላ ላይ ወንጀሉን ፈፅሞል ብላ የመሰከረችው ሴት ራሷ የስትሪክላንድእን አስር በመቃወም እና ምስክር የሰጠቸው ማንነቱን እንዲታውቅ ባልተፈለገ ሰው ግፊት እንደተደረገባት ተናግራለች። ስትሪክላንድን ከወንጀሉ ጋር የሚያይዘው ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ ባይኖርም ለ43 አመታት የይቅርታ እድል ሳይኖር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር።
ይህ ሰው ለ43 ዓመታት በእስር ቤት እያለ ንፁህነቱን ለማረጋገጥ ብዙ ትግል ታግሏል። ተሟጋች ቡድኖች፣ ጋዜጠኞች እና አቃብያነ ህጎችም በኋላ የጥፋተኝነት ውሳኔው ስህተት መሆኑን አምነዋል። በመጨረሻም እ.አ.አ በ2021 አንድ ዳኛ ለ43 ዓመታት በስህተት ታስሮ እንደነበር በመግለጽ ስትሪክላንድን ከእስር ነፃ አውጥቶታል።
ኬቨን ስትሪክላንድ በ18 አመት እድሜው ባልፈፀመው ወንጄል 43 አመታት ታስሮ በ62 አመቱ ከእሰር በነፃ ሲወጣ በወጣትነቱ ከሚያውቀው ሙሉ በሙሉ ወደ ተለወጠ አለም ገባ። ስማርት ስልክ ተጠቅሞ አያውቅም፣ ኢንተርኔት አይቶ አያውቅም ነበር፡፡ ብዙ ነገር መስራት የሚችልበት የወጣትነት እና የአዋቂ እድሜ ህይወቱን አጥቷል።
ባልሰራው ወንጀል ከአራት አስርት አመታት በላይ በእስር ቤት ላሳለፈው ለስትሪክላንድ በወቅቱ የነበረው የሚዙሪ ፍርድ ቤትና የነበረው ህግ ካሳ ያልሰጠው የነበረ ሲሆን በትንሽ የገንዘብ ድጋፍ ብቻ ከእስር እዲለቀቅ ነበር የተደረገው።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በእሱ ምክንያት በመላው የዩናይትድ ስቴትስ የተሳሳቱ የጥፋተኝነት ሕጎች እና የማካካሻ ህጎች ማሻሻያን በተመለከተ ከፍተኛ ጩኸት እና ተቃውሞ አስነስቷል፡፡
🙏🙏👉👉👉Via፦ አዳነ ካሳሁን 🙏👉👉 #ሼር
🌷🌷🌷
🙏🌷🌷👇❤❤🙏🙏ይህ መልዕክት 👇👇ይነበብ ይነበብ 🚫🚫ማሳሰቢያ በደንብ ይነበብ🚫🚫👇👇👇
Teamwork IT Solutions የዲጂታል ኢትዮጵያችን ተስፋ ጠቃሚ መረጃዎች ወደ እናንተ እንዲደርስ የክብር ስፖንሰራችን ነው። መረጃን በዲጂታል ለማዘመን ለግልና ለመንግስታዊ ተቋማት መተግበሪያዎችን በማቅረብ ተሸላሚ ተቋም ሲሆን🙏👉 ዋና ቢሮው አዲስ አበባ ቅርጫፎቹ በየክልሉ ዋና ዋና ከተሞች ነው 🙏🙏ለበለጠ
👉👉መረጃ ፦ 0923227081
በመላው የአማራ ክልል ብዙዎቹ ዞኖች ላይ ስኬታማ የሆነ መረጃን በዲጂታል አዘምኖ ለአጠቃቀም ምቹ አድርጎ በማቅረቡ ተሸላሚ ለመሆን የበቃው ተቋም በመላው ኢትዮጵያ ለግልና ለመንግስታዊ ተቋማት መረጃን በዲጂታል የማዘመን አሰራርን በታላቅ የዋጋ ቅናሽ በማቅረብ ላይ በመሆኑ በአጭር የስልክ ጥሪ ሃሎ በማለት የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን።
#ትኩረት #ሚዲያ #ኢትዮጵያ #ሼር #ሠላም #መረጃ