ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts

ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts ኤሎሄ ኪን ELOHE FINE ARTS Is a private company that provides you the Services of Advertising,

TAZMA FINE ART Is a private company that provides you the Services of Advertising, Videography, Photography, Animations, Song and Sound Recording, Wading , Music Producer, TV and Radio Program Production, Printing Media,Lighting, Graphic Design, Event Organizers, TOUR and A Day TRIP Organizers etc...
We Also Provide Art and Computer Science and Media Production.

በስነ-ጥበብ መስክ እና በብዙሃን መገናኛ መስክ ዓለም

አቀፍ በሆነ የስራ ጥራትና ብቃት ትኩረታቸው በማህበረሰብ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የአተኮሩ የስነ-ጥበብ ስራዎችን ይሰራል ፤ ትላንት የነበረውን ዛሬም የአለውን እንዲሁም የወደፊቱን ቀድሞ በመከወን በአንድ ድንጋይ ሶስት ማንነትን አቅፎ አንድ የማህበረሰብ የስነ-ጥበብ ፣ የንባብ እና የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲሁም ባህልን በዚህ የስርዓቱ መደምደሚያ ድረስ የዓላማው ግብ በማድረግ በመስራት ላይ የአለ የግል ኩባንያ ነው፡፡

t.me/tazmafineart

https://youtu.be/XUwDGjCPGYQ
08/02/2026

https://youtu.be/XUwDGjCPGYQ

ለልጆች መድረክ👉🏾⁩ ለሙዚቃ👉🏾⁩ ለትረካ ፡👉🏾⁩ ለግጥም👉🏾⁨⁩ ለመዝናኛና ቁም ነገር ፡👉🏾⁩ ለድራማ👉🏾⁨...

በሪፖርተርነት ለመሥራት ፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትገኙ የተዘጋጀ፡፡ JR26-1👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
03/02/2026

በሪፖርተርነት ለመሥራት ፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትገኙ የተዘጋጀ፡፡ JR26-1
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

https://youtu.be/vVcth11Q5nU
13/01/2026

https://youtu.be/vVcth11Q5nU

ለልጆች መድረክ👉🏾 ለሙዚቃ👉🏾 ለትረካ ፡👉🏾 ለግጥም👉🏾⁨ ለመዝናኛና ቁም ነገር ፡👉🏾 ለድራማ👉🏾⁨ ደራሲ ፡ አውግቸው ...

https://youtu.be/RgXZcHBxbPs
13/01/2026

https://youtu.be/RgXZcHBxbPs

ለልጆች መድረክ👉🏾⁩ ለሙዚቃ👉🏾⁩ ለትረካ ፡👉🏾⁩ ለግጥም👉🏾⁨⁩ ለመዝናኛና ቁም ነገር ፡👉🏾⁩ ለድራማ👉🏾⁨...

ለከያኒያን ፤OPFART26አዲስ ለምንጀምረው ልዩ የቴሌቭዥን የመዝናኛ መሠናዶ ላይ ገጣሚያን ፣ የወግና መጣጥፍ ጻሕት ፣ የዲስኩር ችሎታ ያለው ፣ በመድረክ የመምራት ብቃት ያለው ፣ የውዝዋዜና...
13/01/2026

ለከያኒያን ፤OPFART26
አዲስ ለምንጀምረው ልዩ የቴሌቭዥን የመዝናኛ መሠናዶ ላይ ገጣሚያን ፣ የወግና መጣጥፍ ጻሕት ፣ የዲስኩር ችሎታ ያለው ፣ በመድረክ የመምራት ብቃት ያለው ፣ የውዝዋዜና ዳንስ ችሎታ የአላቹ በሙሉ አብራችሁን እንድትሠሩ እንጋብዛለን፡፡
ምዝገበውን ለማድረግ ፡ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ያላችሁ ያለ ጽዎታ ልዩነት መሣተፍ የምትችሉ ሲሆን ፡ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጭ የምትገኙ መመዝገበብ ትችላላቹ፡፡
ለመመዝገብ ፡
👇👇👇👇
https://tazmaoptf.blogspot.com/2026/01/opfart26.html
በቴሌግራም ይቀላቀሉን
👇👇👇👇
https://t.me/openplatforms

ጥር ፲፰ እስከ ጥር ፳፱/፳፻፲፰ ዓ.ም ድረስ ለሚኖር የቀረጻ ሥራ ላይ ሁለት ተዋናዮችን እንድትሳተፉ እንጋብዛለን ፤ለሴት ፡ ዕድሜ ከ22 እስከ 35 ድረስ ፤ለወንድ ፡ ዕድሜ ከ 27 እስከ 4...
12/01/2026

ጥር ፲፰ እስከ ጥር ፳፱/፳፻፲፰ ዓ.ም ድረስ ለሚኖር የቀረጻ ሥራ ላይ ሁለት ተዋናዮችን እንድትሳተፉ እንጋብዛለን ፤

ለሴት ፡ ዕድሜ ከ22 እስከ 35 ድረስ ፤

ለወንድ ፡ ዕድሜ ከ 27 እስከ 45 ድረስ ፤

ከዕድሜ ውጭ ሌላ ተጨማሪ መሥፈርት አላስቀመጥንም ፡ የትወና ብቃት አለኝ ለምትሉ በሙሉ መሣተፍ ትችላላቹ ፤

ለመሣተፍ የምትፈልጉ ፡ አዲስ አበባ ፤ ሸገር ሲቲ ፤ ደብረዘይት ፤ ናዝሬት ያላቹ በሙሉ መሣተፍ ትችላላቹ፡፡

በዚህ ማስታወቂያ መመዝገብ የምትችሉት ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር ፳፩/፳፻፲፰ ዓ.ም ድረስ ብቻ አስታውሱ እንደተለመደው ምንም ዓይነት ክፍያ በፍጹም አንጠይቅም ፤
ምዝገባ ለማድረግ ይህን ይጫኑ ፡
👇👇👇
https://tazmaoptf.blogspot.com/2026/01/opa26.html
በቴሌግራም ይቀላቀሉን
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/openplatforms

በሪፖርተርነት ለመሥራት ፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትገኙ የተዘጋጀ፡፡ JR26-1👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾https://tazmaoptf.blogspot.com/2025/12/jr26-1.htmlአስታውሱ ፡ ከእኛ...
12/01/2026

በሪፖርተርነት ለመሥራት ፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ለምትገኙ የተዘጋጀ፡፡ JR26-1
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
https://tazmaoptf.blogspot.com/2025/12/jr26-1.html
አስታውሱ ፡ ከእኛ ጋር ለመስራት ምንም ዓይነት ክፍያ { የምዝገባ የመሳሰሉ ጨምሮ } አንጠይቅም ፡ ነገር ግን ብቃታቸውን አስመስክረው ለሚሰሩ ግን ተገቢውን እና ተመጣጣኝ ክፍያ እንከፍላለን።
በቴሌግራም ይቀላቀሉን
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
https://t.me/openplatforms

ለ15 ቀናት መጻሕፍትን በ100 ብር ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ በራፍ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ በኤዞፕ መጻሕፍት መደብር ልዩ ሽያጭ ተዘጋጅቷል ይሸምቱ፣ ያንብቡ!5 መጻሕፍት ለሚ...
19/11/2025

ለ15 ቀናት መጻሕፍትን በ100 ብር ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሕንጻ በራፍ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ በኤዞፕ መጻሕፍት መደብር ልዩ ሽያጭ ተዘጋጅቷል ይሸምቱ፣ ያንብቡ!

5 መጻሕፍት ለሚገዙ ስድስተኛ በነጻ ይጨመራል !

ከጥቂት አመታት በፊት ለቤተሰቦቼ የነበረኝ ቦታ በጣም ዝቅተኛ ነበር ቤት ካለመዋሌ የተነሳ የታመመ ሰው ቢኖር እራሱ አላውቅም ጓደኞቼን አስቀድሜ የእህቶቼን ሰርግ ቀርቻለው ሲወልዱም ልክ እንደ...
11/11/2025

ከጥቂት አመታት በፊት ለቤተሰቦቼ የነበረኝ ቦታ በጣም ዝቅተኛ ነበር ቤት ካለመዋሌ የተነሳ የታመመ ሰው ቢኖር እራሱ አላውቅም ጓደኞቼን አስቀድሜ የእህቶቼን ሰርግ ቀርቻለው ሲወልዱም ልክ እንደ ባዳ በጣም ዘግይቼ ነው የሄድኩት ያልሄድኩትም አለ ብቻ ከጓደኞቼ አይበልጡብኝም ነበር ብዙ ብዙ ነገር አድርጌያቸዋለው 1 ቀን ድንገተኛ ህመም ታመምኩ የ3 ሰው ደም እስከመውሰድ ደረስኩኝ ያኔ ማን ነበረ ከጎኔ ማን አለቀሰልኝ ቤተሰቦቼ።

ተመስገን ዳንኩላቸው በአመቱ ወንድሜ ስለት ሲያስገባልኝ አየሁ💔 ለእነሱ ያለኝ ነገር በትንሹ ተቀየረ ጓደኛም ቀነስኩኝ ትዳር ያዝኩኝ እኔ ሰርግ ለምኔ ብዬ ሸውጄ ብገባም😁 እነሱ ያላቸውን አውጥተው ደግሰው መልስ ጠሩኝ ወለድኩኝ አላረሱኝም😁 አጋጣሚ ወንድሜ አርፎ 💔 ስለነበር አማቾቼ ቤት ታረስኩኝ🙏 ልጄ አደገች የትም ብሄድ ልቤ አርፎ የምቀመጠው ከእነሱ ጋር ስትሆን ብቻ እንደሆነ እንዳረጋግጥ አድርገው ይይዙልኛል🙏❤ ድጋሚ ወለድኩኝ ከስራቸው ከትምህርታቸው ከትዳራቸው ከልጆቻቸው ጊዜ እየተሻሙ እያረሱኝ ነው ለምን ስጋቸው እህታቸው ነኛ እንጂ እኔ አይገባኝም ነበር በየካፌው ስንበላ ስንጠጣ የነበሩት ጓዶች በከፊል ዛሬ የሉም ሻይ ጋብዣቸው የማላውቀው የማልታዘዛቸው ቤተሰቦቼ ግን ዛሬም ከኔ ጋር አሉ ብዙ ነገር አስተምራቹኛል 🙏
እግዘብሔር ያቆይልኝ ብድር መላሽ ያድርገኝ ❤
ፎቶው ከጀለሶች ጋር በምዞርበት ወቅት ነው😜😜😜

{ ከሪቾ }

የ91 ዓመቷ ሄለን እና የ88 ዓመቱ ጆርጅ በትዳር ለ65 ዓመታት አብረው የቆዩ ሲሆን፤ጆርጅ ከባድ የልብ ድካም ህመም ስላለበት በህይወት እንዲቆይ 12 ክኒኖችን በየቀኑ መውሰድ አለበት።ከቅረብ...
10/11/2025

የ91 ዓመቷ ሄለን እና የ88 ዓመቱ ጆርጅ በትዳር ለ65 ዓመታት አብረው የቆዩ ሲሆን፤ጆርጅ ከባድ የልብ ድካም ህመም ስላለበት በህይወት እንዲቆይ 12 ክኒኖችን በየቀኑ መውሰድ አለበት።

ከቅረብ ግዜ ወዲህ ባልና ሚስቶቹ ባላቸው የጤና መድህን መድሃኒቶችን መግዛት አልቻሉም።

አዛውንቶ ሄለን ለባሏ መድሃኒት ለመግዛት ወደ ፋርማሲ ስትሄድ 50 ዶላር የነበረው የመድሃኒት ዋጋ ወደ 940 ዶላር አሻቅቦ ጠበቃት፣

ሄለን ምንም ገንዘብ ስለሌላት ለባሏ ምንም ዓይነት መድሃኒት ሳትገዛ ቦዶ አጇን ወደ ቤት ተመለሰች፤ ባሏ ለሶስት ቀን ያለመድሃኒት በመቆየቱ ሊሞት ደረሰ።

ሄለን በፍረሃት ወደ ፋርማሲው ተመለሰች፤ፋርማሲስቱ ስራ ላይ እያለች የማይታሰብ ነገር አደረገች። እጆቿ እየተንቀጠቀጡ የመድሀኒት ሳጥኖችን ከጠረጴዛው ውስጥ በማውጣት ጠርጋ ወደ ትልቁ ቦርሳዋ ከተተችው(ሰረቀች!)።

የሰረቀችውን መድሃኒቱ ይዛ ልትወጣ ስትል የፋርማሲ አስተዳዳሪው ሲከታተላት ስለነበር አስቆሟት እና ፖሊስ አሰጠራ።

ሄለን በፖሊስ ተይዛ ፣ በሱቅ ዝርፊያ ተወንጅላ በጣብያ እንድትቆይ ተደረገች ፣ ፖሊሶች የሄለንን ሁኔታ ሲመለከቱ የደም ግፊቷ በጣም ከፍ አንዳለ በመጠርጠር አምቡላንስ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ወሰዷት ።

አዛውንቶ ሄለን የሆስፒታል የበሽተኛ ጎዋን ለብሳ በከባድ ስርቆት ወንጀል ተይዛ ዳኛ ፊት ቀርበች።

በጠዋት ከሆስፒታል አልጋዋ ተነስታ በቀጭን ሰማያዊ የበሽተኛ ጎዋን፣ ደካማ አጇ በሰንሰለት ታስሮ ነበር ለፍርድ የቀረበችው።

ሄለን "እንዲህ ያለ ቀን ራሴን አያለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" በማለት ለራሷ ብቻዋን አወራች።

ዳኛው ማርከስ ክሱን እየተመለከተ ፊቱ የሀዘን እየታየበት ካቀረቀረበት ቀና ብሎ በጠንካራ ድምጽ "እነዚህን ሰንሰለቶች ከዚህች ሚስኪን እጅ ላይ ፍቱ " በማለት ትእዛዝ ሰጠ።

አቃቤው ግን "የወንጀል ስርቆት? ለዚች ሴት?" በማለት አጓራ።

ሄለን እያለቀሰች "ባሌ መተንፈስ አቃተው... ምን ማድረግ አለብኝ? እሱ ብቻ ነው ያለኝ ባሌ መድሀኒቱን ብቻ ነው የምፈልገው" አለች::

አዛውንቷ ሄለን በነፃነት ከፍርድ ቤት ወጥታ ወደ ቤቷ ባለቤቷን ልታሰታምም በፍጥነት ሄደች።

10/11/2025

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መግለጫ ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts

አበበ ባልቻ በ1948 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቀበና አካባቢ የተወለደ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮኮበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡ አርቲስት አበበ ባልቻ የመጀመሪያ ዲግሪውን...
10/11/2025

አበበ ባልቻ በ1948 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቀበና አካባቢ የተወለደ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮኮበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡

አርቲስት አበበ ባልቻ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት አግኝቷል፡፡

አበበ ባልቻ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች የነበረ ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን ወደ ትወና አድልቶ በዩኒቨርሲቲው የባህል ማዕከል ውስጥ ይታደም ያዘ፡፡

ከዚያም በኋላ ወደ ቲያትር ትወና በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ "ኦቴሎ" በተሰኘው ቲያትር ላይ በመሪ ተዋናይነት ተጫውቷል፡፡

አበበ ባልቻ ሥራዎቹን በአሜሪካ ፣ በአውሮፓና በአፍሪካ በሚገኙ በተለያዩ ሀገራት ከስመጥር የወቅቱ ተዋንያኖች ጋር በመሆን አሣይቷል፡፡

ከቲያትር ባሻገር አርቲስት አበበ ባልቻ በፊልም እና በተከታታይ ድራማዎችም ላይ ብቃቱን ያሳየና ተወዳጅነትንም ማትረፍ የቻለ አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው።

በሕግ ሙያውም በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ያገለገለው አርቲስት አበበ ባልቻ በሀገራችን የጥበብ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስሙን በጉልህ ማስፈር ችሏል።

አበበ ባልቻ ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል አስከሬኑ ፣ ሔሮሽማ፣ 3 ማዕዘን ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች ደግሞ ባለጉዳይ፣ ሰው ለሰው፣ ዘመን ፣ ግራና ቀኝ፣ በሕግ አምላክ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በተለይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ የነበረው የሰው ለሰው ድራማ “ አስናቀ “ የተሰኘው ገፀ- ባሕርይ በጥበብ አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያስገኘለት እንደነበረ ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ ከመተወን ባለፈ የተለያዩ ድራማዎችን እያዘጋጀ ለዕይታ እያቀረበ ይገኛል፡፡

አርቲስት አበበ ባልቻ የሬዲዮ ትረካዎችንም ይተርካል። በጤና ሚኒስቴር የአእምሮ ጤና የበጐ ፍቃድ አምባሳደር በመሆንም ሰፋፊ ሥራዎችን አከናውኗል።

አበበ ባልቻ የሸገር ሬዲዮ 1ዐ2.1 ሥራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለገለም ይገኛል።

ከአርቲስት አበበ ባልቻ ሥራዎች የቱን አይተዋል ? ቢያጋሩን !

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Establishment

Send a message to ኤሎሄ ኪነ Elohe Fine Arts:

Share