Jay parks

Jay parks Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jay parks, Ethiopia Addis Ababa, .

03/03/2026

ቢል ክሊንተን (ሳዳም ሁሴን - 1998)
የተናገሩት ቃል፦ "የሳዳምን የጦር መሳሪያ አቅም አዳክመናል፤ ለዓለም ሰላም ሰጥተናል።
ሀቁ፦ ሳዳም አልተዳከሙም፣ እንዲያውም በረቱ

ጆርጅ ደብሊው ቡሽ (ሳዳም ሁሴን - ኢራቅ)
የተናገሩት ቃል፦ "ተልዕኮው ተሳክቷል፤ ኢራቅ አሁን ነፃና ሰላማዊ ናት።"
ሀቁ፦ ሀገሪቱ ወደ ማያልቅ የእርስ በርስ ጦርነት ገባች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን ሞቱ፣ አሜሪካም የሃገሪቱን ንብረት ዘረፈች፣

ሮናልድ ሬገን (ጋዳፊ - ሊቢያ 1986)
የተናገሩት ቃል፦ "ይህ ጥቃት ሽብርተኝነትን ይቀንሳል፤ ጋዳፊን ያስቆማል።
ሀቁ፦ ጋዳፊ ይበልጥ ጉልበቱን ጨመረ

ባራክ ኦባማ ( ጋዳፊ - ሊቢያ)
የተናገሩት ቃል፦ "ሊቢያውያን ከጭቆና ነፃ ወጥተዋል፤ የዲሞክራሲ ጭላንጭል ታይቷል።"
ሀቁ፦ ሊቢያ መንግስት አልባ ሀገር (Failed State) ሆነች፣ ንብረቷ በአውሮፓውያን ተዘረፈ፣ ህዝቡ ተጨፈጨፈ።

ሊንደን ጆንሰን (ንጎ ዲን ዲየም - ቬትናም 1963)
የተናገሩት ቃል፦ "ይህ ለቬትናም ዲሞክራሲና መረጋጋት አስፈላጊ እርምጃ ነው።"
ሀቁ፦ ግድያው ለቬትናም ሰላም አላመጣም፤ አሜሪካን ለ10 ዓመታት ወደ ፈጀና በሚሊዮኖች ለተገደሉበት ጦርነት ዳረጋት።

ሪቻርድ ኒክሰን (ሳልቫዶር አሌንዴ - ቺሊ 1973)
የተናገሩት ቃል፦ "ቺሊን ከማርክሲስት አምባገነንነት አድነን ነፃነቷን መርጠናል።"
ሀቁ፦ አሜሪካ በዲሞክራሲ የተመረጡትን መሪ ካስገደለች በኋላ፣ እጅግ ጨካኝ የተባለውን ኦገስቶ ፒኖቼን ስልጣን ላይ አወጣች። ፒኖቼ ለ17 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድሏል፣ አሰቃይቷል።

ጆን ኤፍ ኬኔዲ (ፓትሪስ ሉሙምባ - ኮንጎ 1961)
የተናገሩት ቃል፦ "የኮንጎን ነፃነት እና ከኮሚኒዝም ነፃ መሆን እንደግፋለን።"
ሀቁ፦ አሜሪካ ሉሙምባ እንዲገደሉ በገንዘብና በሴራ ድጋፍ አድርጋለች። ውጤቱም ኮንጎ ለ30 ዓመታት በጨካኙ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ እንድትበዘበዝ እና እስካሁን ወደማያልቅ ጦርነት እንድትገባ አደረጋት።

ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ (ማኑኤል ኖሪጋ - ፓናማ 1989)
የተናገሩት ቃል፦ "አምባገነኑን ለማስወገድና ዲሞክራሲን ለመመለስ እንዲሁም የአሜሪካን ዜጎች ለመጠበቅ የመጣን የሰላም ሃይል ነን።"
ሀቁ፦ በፓናማ ከተማ ድሃ ሰፈሮች ላይ በተደረገ ድብደባ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገደሉ፣ ሀገሪቱ ለዓመታት በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ወደቀች።

ጆን ኤፍ ኬኔዲ (ራፋኤል ትሩጂሎ - ዶሚኒካን ሪፐብሊክ 1961)
የተናገሩት ቃል፦ "አምባገነንነትን አንታገስም፤ ለካሪቢያን ሀገራት ነፃነት እንቆማለን።"
ሀቁ፦ ትሩጂሎ በአሜሪካ ድጋፍ ከተገደሉ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ብጥብጥ ገባች። አሜሪካም በ1965 ዳግም ሀገሪቱን በጦር ሃይል ወርራ የራሷን ታማኝ መንግስት ለመሾም ተገደደች።

ድዋይት አይዘንሃወር (ሙሀመድ ሙሰዲቅ - ኢራን 1953)
የተናገሩት ቃል፦ "ኢራንን ከኮሚኒዝም አድነን ነፃነቷን አስከብረናል።"
ሀቁ፦ በህዝብ የተመረጡ መሪ ተወግደው ንጉሱ (ሻህ) በሃይል ተሾሙ፣ ይህም ለ1979ኙ አብዮትና ለአሁኑ ስርአት መሰረት ሆነ።

ዶናልድ ትራምፕ (ቃሲም ሱለይማኒ - ኢራን)
የተናገሩት ቃል፦ "ጦርነትን ለማቆም እርምጃ ወስደናል፤ ዓለም አሁን ሰላማዊ ሆናለች።"
ሀቁ፦ ግጭቱም ድርድሩም ግድያውም እንደቀጠለ ነው፣ ይባስ ብሎ ቀጠናውም ተቀላቀለ

ዶናልድ ትራምፕ (አያቶላ ካሜኒ - ኢራን)
የተናገሩት ቃል፦ "የሽብርተኝነት ልብ ተመቷል፤ እስራኤልና አሜሪካ ደህንነታቸው ተጠብቋል።"
ሀቁ፦ እያየነው ነው፣ ወደፊትም ውጤት የሌለው እንዳለፉት መሪዎች ንብረት መዝረፍ፣ መንግስት አልባ ማድረግና ህዝብን ከመጨፍጨፍ ውጪ ምንም የሚሰጡት ጥቅም የለውም።

✍️✍️✍️
ምሳሌዎቹ የሚያሳዩት አንድ ተመሳሳይ ሃቅ ነው፦ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች እርምጃቸውን "ነፃነት"፣ "ዲሞክራሲ" ወይም "ሰላም" በሚሉ ቃላት ያስውቡታል። ነገር ግን ውጤቱ ሁልጊዜም ለተጠቂው ሀገር ህዝብ "ትርምስ"፣ "እልቂት" እና "የረጅም ጊዜ ስቃይ" ሆኖ ነው የሚገኘው።
እነዚህ መሪዎች የሚገድሏቸው ሰዎች ለሀገራቸው "ጀግና" ሲሆኑ፣ በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ንግግር ውስጥ ግን "አሸባሪ" ተብለው ይጠራሉ። ይህ በዓለም ፖለቲካ ውስጥ ትልቁ የትርጉም ልዩነት ነው።

06/02/2026

የአለማችን ቁጥር 1ዱ ባለኃብት ፣ #ኤሎን መስክ ሐብቱ 850 ቢሊዮን ዶላር ከደረሰ በኋላ "ገንዘብ ደስታን አይገዛም” ማለት ዛሬ መነጋገሪያ ሆኖአል 😂😂😂 Facebook

11/12/2025

Address

Ethiopia Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jay parks posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment?

Share