Var Sport

Var Sport Football
(2)

  this channel and u will thank me later
25/02/2026

this channel and u will thank me later

🔥 Daily Shorts 🚔 Crime & Justice Stories 💙 Emotional & Motivational Moments Subscribe and turn on notifications for new videos every day!

21/08/2025

አሰልጣኙ ሳያውቅ ራሱን ቀይሮ የገባው ተጫዋች...ይህ ሰው ዳንኤል አሞካቸ ይባላል። አብዶኛ ናይጄሪያዊ ተጫዋች ነበር። ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቷል። የኤቨርተን ተጫዋች እያለ በ1995 የሰራውን...
01/08/2025

አሰልጣኙ ሳያውቅ ራሱን ቀይሮ የገባው ተጫዋች...
ይህ ሰው ዳንኤል አሞካቸ ይባላል። አብዶኛ ናይጄሪያዊ ተጫዋች ነበር። ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቷል። የኤቨርተን ተጫዋች እያለ በ1995 የሰራውን ስራ ማንም አይረሳውም።
ነገሩ እንዲህ ነበር...
ክለቡ ኤቨርተን ከቶተንሀም ጋር ለኤፍኤካፕ ግማሽ ፍፃሜ እየተጫወተ እያለ የኤቨርተኑ አጥቂ ፓውል ራይዳውት ይጎዳል። ወጌሻዎቹ እሱን ለማከም እየተረባረቡ ነው። አሰልጣኙም በጭንቀት ተውጦ የጉዳቱን መጠን ለማወቅ እየተከታተለ እያለ አሞካቸ አሰልጣኙ ሳያየው ከተቀመጠበት ቤንች ተነስቶ 4ኛውን ዳኛ ተቀይሮ ሊገባ እንደሆነ ያሳውቃል። ዳኛውም ተቀይሮ እንዲገባ የተፈቀድ መስሏቸው ምልክት ያሳዩና እንዲገባ ፈቅዱለት። ገባ። ይህ ሁሉ ሲሆን አሰልጣኙ አላየም ነበር። የራይዳውት ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ወጌሻዎች በወሳንሳ ይዘውት ወጡና ጨዋታው ቀጠለ።
አሰልጣኙ በተጎዳው ተጫዋች ቦታ ማንን ላስገባ ብሎ ወደቤንች ሲያማትር አሞካቸ ቦታው ላይ የለም። ዞሮ ወደጨዋታው ሲመለከት አሞካቸ ሜዳ ውስጥ ገብቶ እየተጫወተ ነው።
ይህኔ አስልጣኙ አበደ። ነገር ግን ነገሮችን ሁሉ የሚቀይር ሁኔታ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኃላ ተከሰተ። አሞካቸ ምርጥ ጎል አገባ። አሰልጣኙም ሳይወድ በግድ በደስታ ዘለለ። ከትንሽ ደቂቃ በኃላም አሞካቸ በድጋሜ አገባ። አሰልጣኙም በድጋሜ ዘለለ። ኤቨርተንም አሸንፎ ወደፍፃሜው አለፈ።
አሞካቸም ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም እንደሚባለው በአሰልጣኙ ሳይወቀስና ሳይቀጣ ቀረ።
ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የነበረውን የዋንጫ ጨዋታም አሸንፈው የኤፍኤካፑን ዋንጫ አነሱት!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Var Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share