Zeki poet

Zeki poet ጌታዬ ጥያቄዬን ከጥመት አትውሰድብኝ
አለማወቄን እወቅብኝ
አንደ ዩኑስ በምህረትህ ድረስብኝ

08/02/2026

የዛ ሰፈር ሴቶች በጣም ቆንጆ ናቸው
መኪና ሲመጣ ታርጋ ይይዛሉ

|ገጣሚ ማንችሎት|
(ግን ታርጋ ይይዛሉ ከምለው ይንጠለጠላሉ ብለውስ?🤔)

08/02/2026
እምነቴ አልጠፋም ...ጭላንጭል አለው የነገ ተስፋዛሬ ብወድቅም ...ዓለም ቢከፋህልሜ አልጠፋም ይከተለኛል ልክ እንደጥላዛሬ ቢደክመኝ ፤ዘወትር ከእራሴ ጋርም ብጣላእምነት እና ህልሜ ፤ከህይወቴ...
07/02/2026

እምነቴ አልጠፋም ...ጭላንጭል አለው የነገ ተስፋ
ዛሬ ብወድቅም ...ዓለም ቢከፋ

ህልሜ አልጠፋም ይከተለኛል ልክ እንደጥላ
ዛሬ ቢደክመኝ ፤ዘወትር ከእራሴ ጋርም ብጣላ

እምነት እና ህልሜ ፤ከህይወቴ እስካልተወገዱ
አንዱ ቢሰናከል እድናለሁ በአንዱ

.....
06/09/2025

.....

በደል ሁሉ በይቅርታ አይታበስ‎አንዳንድ በደል አለ ከሞትም የሚብስ ‎በደል ሁሉ አንድ አይደለም ‎በደል አለ ቢታኘክ የማይልም‎.‎.‎.‎.‎(ይቅር በለኝ አትበይኝ!)‎
05/09/2025

በደል ሁሉ በይቅርታ አይታበስ
‎አንዳንድ በደል አለ ከሞትም የሚብስ
‎በደል ሁሉ አንድ አይደለም
‎በደል አለ ቢታኘክ የማይልም
‎.
‎.
‎.
‎.
‎(ይቅር በለኝ አትበይኝ!)

ትወደው ነበር እኮ ...‎‎ ሰለሞን ይባላል። የአረቄ ምርኮኛ ነው። የሰፈሩ ሰዎች በጣም ጎበዝ አስተማሪ ነው ይላሉ። እኔ ሳውቀው ግን እንዲህ ነው....‎‎ ጠዋት ይነሳል የሙሉ አረቄ ቤት ይ...
04/09/2025

ትወደው ነበር እኮ ...

‎ ሰለሞን ይባላል። የአረቄ ምርኮኛ ነው። የሰፈሩ ሰዎች በጣም ጎበዝ አስተማሪ ነው ይላሉ። እኔ ሳውቀው ግን እንዲህ ነው....

‎ ጠዋት ይነሳል የሙሉ አረቄ ቤት ይሰየማል። አረቄ ሳይቀምስ ማንንም አያገኝም። ጠዋቱ ፈገግ ሲል ወደረፋዱ የተዘረዘረ እንጊሊዝኛ እየቀባጠረ ይመጣል። የሚያወራበት ለዛ ከእንግሊዝኛ ይልቅ ወደ ሱማልያኛ ይሄዳል። ' Good morning ' ሲለን 'ወርያ' የሚለኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ።

‎ ህይወቱን ለማቆየት ብሎ የቆሻሻ ማስወገጃ መኪና ይገፋል። ከእድፋም ልብሱ ውስጥ የሚገርም የማይናቅ ግርማ ሞገስ አለው። ሁሉም ሰው እንደ ክቡር አባት ጎንበስ ቀና ብሎ ነው ሰላም የሚለው።መቆሸሹ አይታየንም።

‎ ሰለሞን ሚስት አገኘ። ሰብለ ትባላለች። 10 አመት አረብ ሀገር ቆይታ ነው የመጣችው። በመጣች በ6 ወራት ውስጥ ቆንጆ ሰካራም ወጣት። በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደዚህ መሆኗን አንዳንዶች አሳዛኝ ታሪክ ሰጥተዋት ሲያዝኑላት አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው በፈጠሩላት ታሪክ ይናደዱባታል። ግን እውነቱን ማንም የሚያውቅ አልነበረም።

‎ ሁለቱም በስካር አለማቸው ላይ በፍቅር በየመንደሩ ሲዘዋወሩ ይውላሉ። ግን የእነሱን ፍቅር ብዙ ሰዎች አይን ላይ እንዲገባ ያደረገው አንድ ትዕይንት ነበራቸው። ብቻ በምን ምክንያት እንደሆነ አላውቅም በየመሀሉ በጥፊ ጭው አድርጎ ይለጋታል። እርሷም ዝም አትልም ...ከአቅሟ በላይ የሆነ፤ እጅ የሚቀጭ ድንጋ ተሸክማ ትዞረዋለች። ግን አትሰነዝርም ነበር።

‎ 'አያቹ ትወደኛለች' ይላል ።

‎'አልወድህም' እያለች ወገቡ ላይ ትጠመጠማለች።ግን አንድ ቀን...

‎ ሰፈር ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው አየው። ግራ በመጋባት ሰዎቹ ወደተሰበሰቡበት አቅጣጫ አምርቼ በሰዎቹ መሀል ተሽሎክሉኬ ስገባ ...ሰለሞን ከእነግርማ ሞገሱ መሬት ተዘርሮ አየሁት። በተከፈተ አፉ ውስጥ የዝንብ መንጋ ሞልቶታል።

‎"ምን ሆኖ ነው ?"

‎"ሞቷል !"

‎"እኮ ምን ሆኖ ነው ?"

‎"ሚስቱ ፈንክታው"

‎"ሰብለ!?"

‎ ለሞት ሰከንድ በቂ ነው ። ለሞት የአንድ ቀን ስህተት በቂ ነው ። ህርሟን አንድ ቀን ብትሰነዝር ፍቅሯን ገደለችው። ማንም ፍቅሯን ለማኖር የቻለችውን ዘላለም አያይም። ይህቺን አንድ ቀን እንጂ....ሰብለስ ? ሰብለስ ?

‎ከ6 ወራት በኃላ ሰብለ ከእስር ቤት የአእምሮ ታማሚ ናት ተብላ ተለቀቀች። ብዙዎች 'አውቃ ነው ከእስር ለማምለጥ ሀቅሏን አታውቅም እንዲሉ አሯን መብላት ጀመረች' እያሉ ያወራሉ። እርሷ ግን በዝምታ ውስጥ የድንጋይ ካብ እየሰራች አቅሟን ስታደክም ትውላለች። ሰብለ አብዳለች። ምክንያቱም ትወደው ነበር እኮ...

30/06/2025

ግጥም እና አጫጭር ልቦለዶች አብረን እናንብብ(እናብብ)

Address

Adama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zeki poet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share