09/04/2024
✝️✝️✝️ ለካ ትመጣለህ✝️✝✝️‼️
በእንቅልፍ ማዕበል በባዶ መቃተት:
መኖሬን ዘንግቼ ከቤትህ ርቀት :
የምትቆይ መስሎኝ ደግሞ የማትመጣ:
ከዓለም ባርነት አርነት ሳልውጣ ::
ከበለሰ ሳልማር በዘመን ሰመካ:
ደግሞ አንደ ዓይን ጥቅሻ በሌብነት ዱካ ።
ለካ ትመጣለህ!
ሲያሳስበኝ በባዶ የመኖር አባዜ:
በሀጢያት ስስክር በዓለም ድንዛዜ :
መኖር ፀጋ መስሎኝ በጌጥ አሸብርቆ
በ ከንቱ ነፀብራቅ ተፈጥሮን አድምቆ:
ሠውነቴ ጠፍቶ እኔነቴ ለቆ:
መሸ ነጋ ጠባ ዘመኑ ነጐደ:
በአዳኝ አወሬ ሴራ መንፈሴ ነደደ::
መኖሬን አላውቅም አለሁኝ ? እኔ እንጃ!
ዓለም ስትር ግጠኝ መሆኔ ስጋጃ :
በሀጢያት ከፍታ ዝቅ አልኩኝ ደረጃ ።
ወዬ!. ወዮልኝ አላውቅም እኔ ማንነኝ እና፡
በሰው ተመላላሽ እንደ ሸማ ቃና:
ዓለም ስትጋለበኝ በሀጢያት ለጉማ:
መኖር መሾም መስሎኝ መውጣት ወደ ማማ።
ለካ ትመጣለህ! !
ነግሶብኝ ማንነት የስጋ ዝንጋኤ፡
አለማወቅ ጠምቆኝ ለነገ ተንሳኤ፡
ስዛብር ስባክን ለክብረተ ስጋ :
ተሰማኝ ስትወርድ ነብሴ ስትናጋ፡
ወዬ!
ማን ነኝ እኔ ላንተ ማንስ አልከኝ ከቶ ፡
ዝቅ አድርጌ ስታይ የፅድቄን ቀበቶ :
እኔስ ማን ልሆን ነው ማነው ከቶ ስሜ ?
እያለሁ ባቢሎን ሰዶምን ደግሜ ::
ለካ ትመጣለህ !?
ይነበብ ንገረኝ ኤልሻዳይ ክርስቶስ፡
ወይ ይሁዳ ልባል ባይሆንም ጲላጦስ :
ብቻቻ በቻ በል ንገረኝ ላንተ ማነ ነኝ እኔ ?
ሀጢያት ያላረካኝ ያለሁ በዓለም ጠኔ :
ደግሞ i የገባሁ ሲመስለኝ በደጅህ ማለፌ :
አገልጋይ ስመስል በአትሮንስ መደገፌ:
ግራ በመጋባት አለሁኝ በጥልቁ ፡
ይህ ሲመስለኝ ሂወት የውዝግብ ዚቁ :
እባክህ ንገረኛ ማን ነበረ ሰሜ ?
ዋጋዬ ስ ምንድን ነው? ልማፀን ድጋሜ ?
እባክህ !? ይገለጥ 4ብራናው የህይወት መዝገቤ ፣
ማንነቴ ይጥራ ድንግዝግዝ ምናቤ ፤
ማነነኝ(2) እኔ ላንተ የምን ሀገር ዜጋ ፣
የመስፈርቴ ዝርዝር የስራዬ ዋጋ ፣
ምንድን ነው ነገረኝ አስተምረኝ አባ፣
በታቦር ላይ ሰበህ በምህረትህ አምባ ፤
ረቡኒ ኢየሱስ ! የዓለም መጨረሻ ህ ያንተ ማ ዛሬ ነው
ብለህ አስተምረኝ መምጣቴ አይቀሬ ነው
አሜንን እግዚአብሔር ሆይ የሠራዊት ጌታ
አለፋ እና ኦሜጋ አሜንን ማራናታታ!!!
👉ዝክረ ደ/ዘይት
✍️Aᵐᵇᵉˡˢᵉʷ