Kinet Entertainment

Kinet Entertainment Event And Promotion

01/08/2026
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን – “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)  | "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ የህሊና ጥ...
01/08/2026

ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን
– “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ

ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)

| "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ የህሊና ጥሪ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት ማንቂያ እና የሰብአዊነት መልዕክት ነው። ይህ ስራ የአካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያላቸውን ወገኖች በርኅራኄ ከመመልከት ይልቅ፣ እንደ ሙሉ መብት ባለቤቶች እንድናያቸው ያስጠይቃል።

ሙዚቃው የሚያነሳው ዋና ጥያቄ አካል ጉዳተኝነት ሳይሆን፣ እኛ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እጥረት ነው። ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ስራ፣ የህዝብ አገልግሎቶች እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለሁሉም እኩል ተደራሽ ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ በጥልቅ ያቀርባል።

የኅብረት ዜማዎች ሁልጊዜም የዘመናቸውን ማህበራዊ ጉዳይ ያንጸባርቃሉ። "ማለባበስ ይቅር"፣ "ስደት"፣ "ሰላም ለሀገራችን" እና ሌሎችም እንደ ነበሩት ሁሉ፣ "ማንም የላት" ደግሞ የዚህ ዘመን የህሊና ጥሪ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ስራ በስሜት ብቻ የተሞላ አይደለም፤ መፍትሄ የሚፈልግ ጥያቄ ያቀርባል። "ማንም የላት" የሚለውን አባባል "እኛም አለን" በሚል ተግባራዊ መልስ እንድንተካው ይጋብዘናል።

በዚህ ዜማ ላይ የተሳተፉት ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ፣ ድምፃዊት ሀና ግርማ፣ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) እና ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ እያንዳንዳቸው መልዕክቱን በሚመጥን ስሜት አቅርበዋል።

ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸው፣ ዜማውን አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ ቅንብሩን ደግሞ ታምሩ አማረ (ቶሚ) በሙያዊ ብቃት አስውበውታል። የግጥሙ፣ የዜማው፣ የድምፅ አቀራረቡና የቅንብሩ መዋሃድ ሙዚቃውን ከመዝናኛነት በላይ ወደ ማህበራዊ ንቅናቄ አሳድጎታል።

ይህ ዜማ የሚያስታውሰን አንድ እውነት አለ፤ ሰብአዊነት በቃላት ሳይሆን በተግባር ይለካል። አካል ጉዳተኞች ርኅራኄ አይፈልጉም፤ እኩል ዕድል፣ ተደራሽነትና ክብር ይፈልጋሉ።

ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን፤ ለህዝብ የሚያስብ፣ ህሊናን የሚያነቃ እና ማህበረሰብን ወደ በጎ ለውጥ የሚጋብዝ ስራ ስላቀረባችሁ ምስጋና ይገባችኋል። ይህ ዜማ በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እንደ ዜማ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማህበራዊ ጥሪ የሚታወስ ስራ ይሆናል።

አቶ ሳሚ ተድላ ( የተድላ አምቡላንስ መሥራችና ባለቤት ) "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ፕሮውዲሰር ምስጋና ይገባቸዋል።

በተለይም ጥበብንና በጎ አድራጎትን አጣምሮ በመያዝ፣ አቅም የሌላቸውንና ረዳት ያጡ ወገኖችን ድምፅ ለማሰማት ያደረጉት ጥረትና ያወጡት ወጪ የሚወደስ ነው።

በተጨማሪም በተድላ አምቡላንስ በኩል የሚያደርጉት ድገስ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና የሚያሰጣቸው ያደርጋቸዋል። እንደዚህ ያሉ በጎ አድራጊ ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለሌላውም አርአያ የሚሆኑ ናቸው።

🔥🔥ሃና ግርማ 🔥🔥   🔥🔥ንገዛኻ🔥🔥ግጥምን ዜማን ማክ እዝራ ( Mak Ezra )ምውህሃድ ሙዙቃ ኣሰፋ ኣበበ ( Aradion Studio )ሚክሲንግ ማስተሪንግኣሰፋ ኣበበ ( Aradion Stud...
26/07/2026

🔥🔥ሃና ግርማ 🔥🔥
🔥🔥ንገዛኻ🔥🔥

ግጥምን ዜማን
ማክ እዝራ ( Mak Ezra )

ምውህሃድ ሙዙቃ
ኣሰፋ ኣበበ ( Aradion Studio )

ሚክሲንግ ማስተሪንግ
ኣሰፋ ኣበበ ( Aradion Studio )

Fidel Film Production
Director - Hahu Beatz

Producer - Abudi

Assefa Abebe Fidel Production

🙏Thank youfor watching 🙏     2,000.000 viwes    የብዙሐኑን ቀልብ የሳበ በዚህ ሰአት እሱ ብቻ መነጋገሪያ የሆነ ያልሰሙት አጀብ ብለው በጉጉት የጠበቁት የግጥምና የ...
24/07/2026

🙏Thank youfor watching 🙏
2,000.000 viwes

የብዙሐኑን ቀልብ የሳበ በዚህ ሰአት እሱ ብቻ መነጋገሪያ የሆነ ያልሰሙት አጀብ ብለው በጉጉት የጠበቁት
የግጥምና የዜማ ድራሲ ወጣቱ
የአህመድ ተሾመ (ዲምቢ) ሶስተኛ አልበም በናሆም ሬከርድስ አማካኝነት ወደናንተ ደርሷል ሊንኩን እንሆ

https://youtu.be/_ymcY7BGhhc?si=AnkVlxwM_pySN_lj

አዲስ አልበም . . . ዛሬ ምሽት!!የአህመድ ተሾመ (ዲምቢ) ሶስተኛ አልበም ዛሬ ሀምሌ 10 ቀን በናሆም ሬከርድስ !(የናሆም ሬከርድስን የማህበራዊ ሚድያዎችን በመቀላቀል አዳዲስ ስራዎችን ቀ...
17/07/2026

አዲስ አልበም . . . ዛሬ ምሽት!!
የአህመድ ተሾመ (ዲምቢ) ሶስተኛ አልበም ዛሬ ሀምሌ 10 ቀን በናሆም ሬከርድስ !
(የናሆም ሬከርድስን የማህበራዊ ሚድያዎችን በመቀላቀል አዳዲስ ስራዎችን ቀድመው ይመልከቱ 🤩🤩 ሊንክ እዚህ አለ 👇👇
ዩቲዩብ 👇
https://YouTube.com/c/NahomRecordsIncMusic
ቴሌግራም 👉 https://t.me/nahomrecords
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/
https://youtu.be/JzVF6EsQewk

እንኳን ደስ አለክ ክርስቲያን ሰውነት (ጆጆዬ) ፈጣሪ ያሳድግህ እመቤቴ ለወግ ለመዓረግ ታብቃህ በጣም ነው ምወድህ congregation
04/07/2026

እንኳን ደስ አለክ ክርስቲያን ሰውነት (ጆጆዬ)
ፈጣሪ ያሳድግህ እመቤቴ ለወግ ለመዓረግ ታብቃህ በጣም ነው ምወድህ congregation

Address

Addis Ababa
Ababa

Telephone

+251913124617

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kinet Entertainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share